ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኮት ድ ኦር | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

FT ቅዱስ ጊዮርጊስ  3-0  ኮት ድ ኦር 

7′ ሳላህዲን ሰዒድ፣ 32′ አስቻለው ታመነ፣  36′ አዳነ ግርማ (P)


ቅዱስ ጊዮርጊሶች ኮት ድ ኦርን በአጠቃላይ ውጤት 5 – 0 በመርታት የኮንጎውን ኤሲ ሊዮፓርድስን ወደሚገጥሙበት ጨዋታ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል ።
90′ ጨዋታው በፈረሰኞቹ የ 3 – 0 ውጤት አሸናፊነት ተጠናቋል ። 

85′ ቅዱስ ጊዮርጊስ በተደጋጋሚ ወደ ግብ ቢደርስም ኮትድኦሮች እየተከላከሉ መሆኑን ተከትሎ ተጨማሪ ግብ ማስቆጠር አልቻለም ።

81′ የተጫዋች ለውጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ 

ናትናኤል ዘለቀ  በተስፋዬ አለባቸው ተተክቷል ።

78′ ፍሬዘር ካሳ በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮ ኳሷ የቀኙን ቋሚ ታካ ወጥታለች ።

76′ የተጫዋች ለውጥ ኮት ድ ኦር

ዴብብ ሪሆሴ ወጥቶ ሆሊ ቢቢ ገባ

74′ የተጫዋች ለውጥ ቅ/ ጊዮርጊስ 

አዳነ ግርማ እና ሳላሀዲን ሰይድ ወጥተው ምንተስኖት አዳነ እና  ቡሩኖ ኮኔ ገብተዋል

72′ ሳላሀዲን ወደ ደግብ የሞከረው ኳስ ሲመለስ አቡበከር ግልፅ የግብ አጋጣሚ አግኝቶ ቢሞክርም ስቶታል አሁንም ኳስ ስትመለስ ሳላሀዲን በድጋሜ አግኝቶ በግንባሩ ሲሞክር ለጥቂት ወጥታለች ፡፡

70′ ኮሊንኢስተር ከማዕዘን ወደ ግብ የሞከራትን ኳስ ሮበርት በአሰደናቂ ሁኔታ አወጣበት ።

65′ ሰላሀዲን ሰይድ ናትናኤል ዘለቀ እና በሀይሉ አሰፋ በድንቅ የኳስ ቅብብል ወደ ሳጥን ገብተው ያገኙትን አጋጣሚ በሀይሉ ሳይጠቀም ቀረ ።

58′ እንደትላንቱ ሁሉ ዛሬም ቅዱስ ጊዮርጊስ በተጋጣሚው ላይ የበላይነት ወስዶ እየተጫወተ ይገኛል ።

55′ ጨዋታው ካቆመበት በኮት ድ ኦሩ ሶስት ቁጥር ጂሚ ራዲፊስን አማካይነት ተጀመረ ።

3:50 የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች አሁንም ክለባቸውን ለመደገፍ በስታዲየሙ ታድመዋል ፡፡ የሁለቱም ክለብ ተጫዋቾች ወደ ሜዳ ገብተዋል፡፡

54′ ሜዳው በቋጠረው ውሀ ምክንያት ኳስ አያጫውትም ብለው ኮት ዲኦሮች ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት ጨዋታው ተቋርጦ ሁለቱም ክለቦች ወደ መልበሻ ክፍል አቅንተዋል።


53′ የሀዋሳ ዓለምአቀፍ ስታዲየም ሜዳ ውሀ በመቋጠሩ ሁለቱም ክለቦች ኳስ ይዘው እንዳይጫወቱ አግዷቸዋል።


49′ አበባው ቡጣቆ ያሻገረውን ኳስ ሳለህዲን ባሪጌቾ ሞክሮ ኳስ የግቡን ቋሚ ታካ ወጥታለች።


46′ የተጫዋች ለውጥ – ኮት ዲኦር 

ዲን ሱዜት ወጥቶ ራያን አንታት ገብቷል።


46′ ሁለተኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀምሯል።


የመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ በቅዱስ ጊዮርጊስ 3-0 መሪነት ተጠናቋል።


45+1′ አበባው ቡጣቆ ከቅጣት ምት በቀጥታ የመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው አወጣበት።


45′ ተጨማሪ ሰዐት – 1 ደቂቃ


44′ አብዱልከሪም ኒኪማ ከመስመር ያሻገረውን ኳስ አዳነ ግርማ መትቶት ግብ ጠባቂው ሲተፋው ሳላህዲን አግኝቶ በግንባሩ ሞክሮ ለጥቂት ወደ ላይ ወጣበት።


41′ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በስታዲየሙ እየጣለ ያለው ዝናብ ሳይበግራቸው ክለባቸውን እያበረታቱ ይገኛሉ፡፡


36′ ጎል!!!! ቅዱስ ጊዮርጊስ

አዳነ ግርማ ፍፁም ቅጣት ምቱን ወደግብ ቀይሮታል።


34′ በሳጥኑ ውስጥ አቡበከር ሳኒ ላይ ጥፋት በመሰራቱ ፍፁም ቅጣት ምት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተሰጥቷል።


32′ ጎል!!!! ቅዱስ ጊዮርጊስ

በሀይሉ አሰፋ ከማዕዘን ምት ያሻማውን ኳስ ተከላካዩ አስቻለው ታመነ በግንባሩ  ገጭቶ የጊዮርጊስን ሁለተኛ ግብ ከመረብ አሳረፈ።


30′ አብዱልከሪም ኒኪማ ዞኮ መሀል ለመሀል አሾልኮ ያቀበለውን ኳስ አዳነ ግርማ ሳይደርስበት  ቀረ፤ የሚያስቆጭ አጋጣሚ፡፡


26′ አቡበከር ሳኒ እየገፋ ወደ ሳጥን ገብቶ ለሳላህዲን ሲያቀብለው የኮት ዲኦሩ ተከላካይ ማርወስ ሮዝ አውጥቶበታል።


20′ ቅዱስ ጊዮርጊስ የተሻሉ የግብ ማግባት እድሎችን እየፈጠረ ነው። ዝናቡም በከባድ ሁኔታ መጣሉን ቀጥሏል፡፡


15′ አቡበከር ሳኒ በሚገርም ሁኔታ አራት ተጫዋቾችን አልፎ ያሻማውን ኳስ በቀላሉ ተከላካዩ ጆንስ ጆውበርት አወጣበት።


9′ ጎል!!!! ቅዱስ ጊዮርጊስ 

ሰላህዲን ሰዒድ ከአዳነ ግርማ የተቀበለውን ኳስ አስቆጥሮ ጊዮርጊስን መሪ አደረገ።


4′ ጨዋታው በከባድ ዝናብ እየተከናወነ ነው።


1′ ጨዋታው በኮት ዲኦር አማካኝነት ተጀምሯል።


9:58 – የሁለቱ ክለቦች ተጫዋቾች ወደ ሜዳ ገብተዋል፡፡ የእለቱ  የክብር እንግዶችም ተጫዋቾቹን እየተዋወቁ ይገኛሉ፡፡


9:51 – ጨዋታው ሳይጀመር ከባድ ዝናብ በስታዲየሙ እየዘነበ ይገኛል፡፡


 9:45 – የክብር እንግዶቹ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ አብነት ገ/መስቀል ጨዋታውን ለመታደም በስታዲየሙ ተገኝተው ስፍራቸውን ይዘዋል፡፡ ዝናባማ የአየር ባህሪም ሀዋሳ እያሳየች ትገኛለች።


9:30 – የሀዋሳ ስታዲየም በሰው ሙላት ባይታጀብም በደጋፊው ህብረ ዜማ ደምቋል፡፡ የስታዲየሙ በሮች ወደ ውስጥ ለመግባት በሚጠበቀው ህዝብ ሰልፍ ተጨናንቀዋል። ሀዋሳም በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ቻምዩንስ ሊግ ጨዋታ ልታስተናግድ ደቂቃዎች ቀርተዋቷል፡፡ 


9:20 – የሁለቱ ቡድኖች ተጫዋቾች  ወደ ሜዳ በመግባት እያሟሟቁ ይገኛሉ።


ከሁለቱ ቡድኖች በድምር ውጤት የሚያሸንፈው ቡድን በቀጣዩ ዙር ከኮንጎው ኤሲ ሊዎፓርድስ እና ከካሜሮኑ ዩ ኤም ኤስ ዴ ሉም አሸናፊ ጋር የሚገናኝ ይሆናል።


ሁለቱ ቡድኖች ከሳምንት በፊት በሲሼልስ ፕራስሊን ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሳላህዲን ሰዒድ ሁለት ግቦች 2-0 ማሸነፍ እንደቻለ ይታወሳል።


ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ አንባቢዎቻችን። በ2017ቱ የቶታል አፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ የኢትዮጵያው ተወካይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሲሼልሱ ኮት ዲኦር ጋር የሚያደርጉትን የመልስ ጨዋታ ቴዎድሮስ ታከለ ከሀዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት  ወደ እናንተ የሚያደርስ ይሆናል።


የመጀመሪያ አሠላለፍ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

30 ሮበርት ኦዶንካራ

2 ፍሬዘር ካሳ — 15 አስቻለው ታመነ — 13 ሳላህዲን ባርጌቾ — 4 አበባው ቡታቆ

27 አብዱልከሪም ዞኮ — ናትናኤል ዘለቀ — 19 አዳነ ግርማ

18 አቡበከር ሳኒ — 7 ሳላህዲን ሰዒድ — 16 በኃይሉ አሰፋ

ተጠባባቂዎች

1 ፍሬው ጌታሁን

12 ደጉ ደበበ

3 መሃሪ መና

11 ፕሪንስ ሰቨሪን

17 ብሩኖ ኮኔ

21 ተስፋዬ አለባቸው

23 ምንተስኖት አዳነ


የመጀመሪያ አሠላለፍ – ኮት ድ ኦር

1 ጄ. ፒ. ሌስፔራንስ

4 ዴቭ ብሪዩት — 30 ጂሚ ራዳፊሰን — 3 ማርውስ ሮዝ — 5 ጆንስ ጆውበርት

15 ጃን ቲጋና — 6 ቤኖይ ማሪ — 14 ኮሊን ኤስተር — 7 ስቲቭ ኤስተር

10 ዲን ሱዜት — 21 ጀርቬይስ ሳሚናዲን

ተጠባባቂዎች

16 ንሶይ ሌስፔራንስ

23 ራያን አንታት

11 ቬሪይ ቢቢ

12 ኦሊቨር ቤንቴ

9 ጄራርድ ባሴት

8 ሻውን ባርቤ

Leave a Reply