ፌዴሬሽኑ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ አድርጎ መርጧል

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከቴክኒክ ኮሚቴው የቀረበለትን ሀሳብ በማጽደቅ የአዳማ ከተማው አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን የብሄራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ በዛሬው እለት መምረጡን ሶከር ኢትዮጵያ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮቿ አረጋግጣለች፡፡

የፌዴሬሽኑ ቴክኒክ ኮሚቴ ለብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝነት የወጣውን የቅጥር ማስታወቂያ ተከትሎ ማስረጃቸውን ያስገቡ አሰልጣኞችና  በመመልከት አሰልጣኝ አሸናፊን በከፍተኛ ድመፅ በመምረጥ ለፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ ማስተላለፉ የሚታወስ ነው፡፡ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴውም በዛሬው እለት በኃይሌ ሪዞርት ባደረገው ድንገተኛ ስብሰባ የአሰልጣኝ አሸናፊን አሰልጣኝነት አጽድቋል፡፡ በመጪዎቹ ጊዜያትም ዝርዝር የኮንትራት ድርድሮች በፌዴሬሽኑ እና በአሰልጣኙ መካከል ተደርገው የአሰልጣኝ አሸናፊ ሹመት ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

6 Comments

  1. ጥሩ ውሳኔ ይመስለኛል። ግን የኢንስትራክተር መኮንን ብሩ (የፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ክፍል ዳይሬክተር) መልቀቂያ ማስገባትና ይህም በፌዴሬሽኑ ተቀባይነት ማግኘቱ ‘ከብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ መረጣው ጋር’ ይገናኝ ይሆን????

  2. It is great to hear the news of appointing the head coach of Ethiopia foot ball national team. I hope you will let us to know his profile on the future. I wish him successful work time and transformation for our national foot ball team.

  3. እኔ እንደማስበው ለአሸናፊ የሚሻለው የነበረው ቢያንስ ይህን የውድድር አመት ከአዳማ ጋር ቢጨርስ ነበር። በሀገርውስ ውድድር በዘንድሮ አመት በአንፃራዊ ሁኔታ ወጥ አቋም ያሰየን ቡድን አዳማ ነበር ከዚህ ቡድን ጋር ዋንጫ ለማንሳት ቢታገል ይሻለው ነበር ዋንጫ ባያነሳም ተፎካካሪ ሆኖ ቢጨርስ እንኳን የተሻለ ስኬት ነበር ለእርሱ በቤሔራዊ ቡድን ከሚያመጣው ማንኛውም አይነት ውጤት። ወይስ ከወዲሁ በሀገር ውስጥ ውድድር ሻምፒዮን እንደማይሆን ታወቆት ነው ስልታዊ ማፈግፈግ ማድረጉ ነው? ለማንኛውም መልካም እድል መልካም የስራ ዘመን።

  4. Now we all coaches have to support him on behind..his success is all about us…my friend wish you all the best in coming all your tasks..

    1. ትልቅነት ከዚህ ይጀምራል. . . ብራቮ ስዩሜ. . . Respect!

Leave a Reply