ቻምፒየንስ ሊግ፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ኤል ሜሪክ እና ኮተን ስፖርት ድል ቀንቷቸዋል

የካፍ ቶታል ቻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታዎች ቅዳሜ መደረግ ጀምረዋል፡፡ በመጀመሪያው ዙር ጥሩ ውጤት ይዘው የወጡ ቡድኖች በቀላሉ የማጣሪያ ዙሩን ሲያልፉ ተስተውሏል፡፡

በዩኤምኤስ ደ ሎም 2-1 የተረታው የኮንጎ ሪፐብሊኩ ሊዮፓርድስ ቀጣዩ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚ ይሆናል፡፡ በሞሮኮ መዲና ራባት ላይ የሴራሊዮኑን ዮሃንሰንን ያስተናገደው ፉስ ራባት 3-0 በማሸነፍ ወደ አንደኛው ዙር አልፏል፡፡ የዛምቢያው ዛናኮ አማሆሮ ስታዲየም ላይ ኤፒአርን  ባልተጠበቀ መልኩ 1-0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ የማጣሪያ ዙር መሻገር ችሏል፡፡ የደቡብ አፍሪካው ቤድቬስት ዊትስ የሪዩኒየን ደሴቱን ሴንት ሊዊዘንን 3-1 አሸንፎ ከሳምንት በፊት የደረሰበትን የ2-1 ሽንፈት ቀልብሷል፡፡ አምና የኬንያ ሃያሉን ጎር ማሂያን ከውድድር ያስወጣው የማዳጋስካሩ ሲኤንኤፒኤስ አሁን ደግሞ የቦትዋናውን ታውንሺፕ ሮለርን ከውድድር በግዜ እንዲወጣ አድርጓል፡፡ ኤል ሜሪክ እና ኮተን ስፖርት ተጋጣሚዎቻቸውን ሶኒ ንጉማ እና አትላባራን በተመሳሳይ ውጤት 4-1 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር በቀላሉ ማለፍ ችሏል፡፡

የቅድመ ማጣሪያ ዙር ጨዋታዎች

(በቅንፍ የተጠቀሱት የድምር ውጤቶች ናቸው)

ቅዳሜ ውጤቶች

ኤፒአር ኤፍሲ (ሩዋንዳ) 0-1 ዛናኮ (ዛምቢያ) (0-1)

ኤኤስ ፋን (ኒጀር) 3-1 ኤኤስ ታንዳ (ኮትዲቯር) (3-4)

ያንግ አፍሪካንስ (ታንዛኒያ) 1-1 ንጋያ ክለብ (ኮሞሮስ) (6-2)

ታውንሺፕ ሮለርስ (ቦትስዋና) 3-2 ሲኤንኤፒኤስ ስፖርት (ማዳጋስካር) (4-4) (ሲኤንኤፒኤስ ከሜዳው ውጪ ባስቆጠረው ግብ አልፏል)

አትላባራ (ደቡብ ሱዳን) 1-4 ኮተን ስፖርት (ካሜሮን) (1-6)

ቤድቬስት ዊትስ (ደቡብ አፍሪካ) 3-1 ሴንት ሊዊዘን (ሪዩኒየን ደሴት) (4-3)

ፋት ዩኒየን ስፖርት (ሞሮኮ) 3-0 ኤፍሲ ዮሃንሰን (ሴራሊዮን) (4-1)

ኤል-ሜሪክ (ሱዳን) 4-1 ሶኒ ደ ኤላ ንጉማ (ኤኳቶሪያል ጊኒ) (5-1)

እሁድ ውጤቶች

አል አሃሊ ትሪፖሊ (ሊቢያ) 2-0 ዋ ኦል ስታርስ (ጋና) (5-1) (ስታደ ኦሎምፒክ ሜንዝ)

ቪታሎ (ብሩንዲ) 0-1 ሲኤፍ ሞናና (ጋቦን) (0-3) (ፕሪንስ ሉዊ ራዋጋሶሬ)

ካፕስ ዩናይትድ (ዚምባቡዌ) 2-1 ሊኦሊ (ሌሶቶ) (2-1)

ክለብ ፌሮቪአሪዮ ደ ቤራ (ሞዛምቢክ) 3-1 ዚማማቶ (ዛንዚባር) (4-3)

ኤኤስ ፖርት ሉዊ (ሞሪሽየስ) 2-1 ተስካር (ኬንያ) (3-2)

ሰዌ ስፖርት (ኮትዲቯር) 0-0 ጋምቢያ ፖርትስ ኦቶሪቲ (0-1)

ዲያብልስ ኖይርስ (ኮንጎ ሪፐብሊክ) 1-0 ሪያል ክለብ ዱ ካዲዮጎ (ቡርኪናፋሶ) (1-3)

ዩኤምኤስ ደ ሎም (ካሜሮን) 2-1 ኤሲ ሊዮፓርድስ (ኮንጎ ሪፐብሊክ) (2-2) (ሊዮፓርድስ ከሜዳው ውጪ ባስቆጠረው ግብ አልፏል)

ኤኤስ ቪታ ክለብ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) 3-1 ሮያል ሊዮፓርድስ (ስዋዚላንድ) (4-1)

ኢንጉ ሬንጀርስ ኢንርናሽናል (ናይጄሪያ) 0-0 ጄኤስ ሳዎራ (አልጄሪያ) (1-1)

ሪቨርስ ዩናይትድ (ናይጄሪያ) 4-0 ኤኤስ ሪያል ደ ባማኮ (ማሊ) (4-0)

ቅዱስ ጊዮርጊስ (ኢትዮጵያ) 3-0 ኮት ደኦር (ሲሸልስ) (5-0)

ክለብ ዴስፖርቲቮ ደ አውጉስቶ (አንጎላ) 2-1 ካምፓላ ሲቲ ካውንስል ኦቶሪቲ (ዩጋንዳ) (2-2) (ኬሲሲኤ ከሜዳው ውጪ ባስቆጠረው ግብ አልፏል)

ሆሮያ (ጊኒ) 2-1 ዩኤስ ጎርን (ሴኔጋል) (2-1)

ስታደ ማሊያን (ማሊ) 1-0 ባራክ ያንግ ኮንትሮለር (ላይቤሪያ) (1-1) (ኮንትሮለር በመለያ ምት 7-6 አሸንፎ አልፏል)

Leave a Reply