በኮንፌድሬሽን ዋንጫው ወደ ተከታዩ ዙር ያለፉ ክለቦች ታውቀዋል

የካፍ ኮንፌዴሬሽን ንጫ የቅድመ ማጣርያ ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ ሲካሄዱ የኢትዮጵያው ተወካይ መከላከያ ዱዋላ ላይ በካሜሩኑ ዮንግ ስፖርትስ አካዳሚ ተሸንፎ ከካፍ 2017 ቶታል ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ተሰናብቷል፡፡ ባለሜዳዎቹ በጦሩ ላይ ከጨዋታው መጀመር አንስቶ ከፍተኛ ጫናን ፈጥረው ለመጫወት መቻላቸው ለአሸናፊነት አብቅቷቸዋል፡፡

ዮንግ ስፖርትስ ኒሲያ ናሳንጉዌ ግብ ቡድኖቹ ወደ መልበሻ ክፍል ከማምራተቸው አስቀድሞ የአጠቃላይ ውጤቱን 1 አቻ ማድረግ ችሏል፡፡ በሁለተኛው አጋማሽ የዮንግ ስፖርትስ ጥንካሬ ቀጥሎ ታይቷል፡፡ በ80ኛው ደቂቃ ቶምቤ ንጉሜ የቅጣት ምት ግብ አስቆጥሮ መከላከያን ከውድድር በድምር ውጤት ተሸንፎ እንዲወጣ አስችሏል፡፡ የካሜሩኑ ተወካይ የፍፁም ቅጣት ምት አግኝቶ የነበረ ቢሆንም አጥቂው ፌስተስ አሳንጎ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡ መከላከያ በሜዳው 1-0 ከሳምንት በፊት ማሸነፉ የሚታወስ ነው፡፡ ዮንግ ስፖርት በአንደኛው ዙር የቱኒዚያው ሲኤፍ ሴፋክሲየንን ይገጥማል፡፡

ጦሩ የቅድመ ማጣሪያ ዙሩን ለማለፍ እየተሳነው ይገኛል፡፡ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ውድድር በኬንያው ኤኤፍሲ  ሊዮፓርድስ እና በግብፁ ምስር ኤል ማቃሳ ተሸንፎ ከውድድር ተሰናብቷል፡፡

የቅድመ ማጣሪያ ዙር ጨዋታዎች

(በቅንፍ የተገለፁት የአጠቃላይ ውጤቶች ናቸው)

የአርብ ውጤት

ሬኔሳንስ ዱ ኮንጎ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) 1-0 አካንዳ (ጋቦን) (1-0)

ቅዳሜ ውጤቶች

ቮልካን ክለብ ደ ሞሮኒ (ኮሞሮስ) 1-1 ቫይፐርስ (ዩጋንዳ) (1-1) (ቫይፐርስ ከሜዳ ውጪ ባገባው ግብ አልፏል)

ሜሰጀር  ንጎዚ (ብሩንዲ) 3-0 ኬቪዚ (ዛንዚባር) (4-2)

ኡሊንዚ ስታርስ (ኬንያ) 1-0 አል ሂላል ቤንጋዚ (ሊቢያ) (1-1) (ኡሊንዚ በመለያ ምት 5-4 አሸንፏል)

ንጌዚ ፕላቲኒየም ስታርስ (ዚምባቡዌ) 1-0 ፓምፕልማውስስ (ሞሪሽየስ) (2-1)

ካራ (ኮንጎ ሪፐብሊክ) 2-0 መግረብ ደ ፌስ (ሞሮኮ) (2-3)

ዮንግ ስፖርትስ አካዳሚ (ካሜሮን) 2-0 መከላከያ (ኢትዮጵያ) (2-1)

ስፖርቲግ ክለብ ደ ጋግኖአ (ኮትዲቯር) 3-0 ሳንአብል (ቡርኪናፋሶ) (3-0)

ምባባኔ ስዋሎስ (ስዋዚላንድ) 3- 2 ኦራፓ ዮናይትድ (ቦትስዋና) (4-2)

ኒያሪ ታሊ (ሴኔጋል) 2-1 አፔጄስ ደ ሞፎ (ካሜሮን) (2-2) (አፔጀስ ከሜዳው ውጪ ባስቆጠረው ግብ አልፏል)

ሴንት ሚሼል (ሲሸልስ) 0-1 አል ሂላል ኦባያድ (ሱዳን) (0-3)

ዩኒዮ ዴስፖርቲቫ ዶ ሶንጎ (ሞዛምቢክ) 0-1 ፕላቲኒየም ስታርስ (ደቡብ አፍሪካ) (0-2)

ሞሊዲያ ክለብ ደ አልጀር (አልጄሪያ) 4-1 ቤቸም ዩናይትድ (ጋና) (5-3)

የእሁድ ውጤቶች

ሬሲንግ ሚኮሚሴንግ (ኤኳቶሪያል ጊኒ) 0-1 ኤቷል ዱ ኮንጎ (ኮንጎ ሪፐብሊክ) (0-3)

ራዮን ስፖርትስ (ሩዋንዳ) 2-0 አል ሳላም ዋኡ (ደቡብ ሰዱን) (6-0)

ሱፐርስፖርት ዮናይትድ (ደቡብ አፍሪካ) 2-1 ኤልጌኮ ፕላስ (ማዳጋስካር) (2-1)

ዊኪ ቱሪስትስ (ናይጄሪያ) 1-0 አርኤስኤልኤኤፍ (ሴራሊዮን) (1-2)

ዩኒየስ ስርቲቭ ደ ካቤሌ (አልጄሪያ) 4-0 ሞኖሮቪያ ክለብ ቤርዌሪስ (ላይቤሪያ) (4-3)

አል መስሪ (ግብፅ) 1-0 ኢፊያኒ ኡባ (ናይጄሪያ) (1-1) (አል መስሪ በመለያ ምት 3-0 አሸንፏል)

ኢትሃድ ደ ታንገር (ሞሮኮ) 1-0 ኤኤስ ዶነስ (ኒጀር) (3-1)

Leave a Reply