ወልድያ ያሬድ ብርሃኑን ሲያስፈርም ለአሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ ረዳቶች ቀጥሯል

ወልድያ የደደቢቱ አጥቂ ያሬድ ብርሃኑን በውሰት ውል አስፈርሟል፡፡ ክለቡ በአጥቂው  ዙርያ ከደደቢት ጋር ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ስምምነት ላይ የደረሰ ሲሆን በዛሬው እለት በፌዴሬሽን በይፋ አስፈርሞታል፡፡ እስከ ውድድር ዘመኑ መጨረሻም የወልድያ  ማልያ ለብሶ ይጫወታል፡፡ ያሬድ አምና በመቀለ ከተማም የውሰት ጊዜ ማሳለፉ የሚታወሱ ነው፡፡

ከክለቡ ጋር በተያያዘ ዜና ለአሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ ረዳቶች መቅጠሩን ይፋ አድርጓል፡፡ የቀድሞው የኢትዮጵያ መድን ድንቅ ግብ ጠባቂ ይልማ ከበደ የክለቡ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ ሆኖ ሲሾም የቀድሞው የሐረር ቢራ ተጫዋች እና አሰልጣኝ ኃይማኖት ግርማ ምክትል አሰልጣኝ ሆነዋል፡፡

ወልድያ በውድድር ዘመኑ በአሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ ብቻ እየተመራ ጨዋታዎች ሲያደርግ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡

Leave a Reply