አዳማ ከተማ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ሾመ

አዳማ ከተማ በግብ ጠባቂነት ያገለገለው የቀድሞ ተጫዋቹን በግብ ጠባቂ አሰልጣኝነት ሾሟል፡፡

ከዚህ ቀደም አዳማ ከተማን በግብ ጠባቂነት ያገለገለው መስፍን ነጋሽ የክለቡ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ተደርጓል፡፡ የግብ ጠባቂነት ህይወቱን በኪራይ ቤቶች ከጀመረ በኋላ በመቀጠል በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (በቀድሞው አጠራሩ ባንኮች) እና እንዲሁም ደግሞ በአዳማ ከተማ የተጫዋችነት ዘመኑን አሳልፏል፡፡

ከክለብ ባሻገር ለኢትዮጵያ ወጣት እና ዋናው ብሔራዊ ቡድኖች ተሰልፎ ሀገሩን ማገልገል የቻለው መስፍን እግርኳስን ካቆመ በኋላ በአቃቂ ቃሊቲ የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን ደግሞ የኢትዮጵያ መድን የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ሆኖ ቆይታን በማድረግ ግልጋሎት የሰጠ ሲሆን አሁን ደግሞ በተጫዋችነት ያገለገለውን አዳማ ከተማን በግብ ጠባቂ አሰልጣኝነት ለማገልገል ተሹሟል፡፡

ያጋሩ