ዝውውር | አዳማ ከተማ መክብብ ደገፉን አስፈረመ

አዳማ ከተማ የሀዋሳ ከተማው ግብ ጠባቂ መክብብ ደገፉን አስፈርሟል፡፡ አዳማ የቀድሞው የወላይታ ድቻ ግብ ጠባቂን ያስፈረመው እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ በሚቆይ የውሰት ውል ነው፡፡ አዳማ በግብ ጠባቂ ቦታ ላይ ጃኮ ፔንዜ ፣ ሲሳይ ባንጫ እና ጃፋር ደሊልን የያዘ መሆኑ በቦታው በርካታ አማራጭ እንዲኖረው አድርጎታል፡፡

መክብብ ደገፉ ወላይታ ድቻ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ባደገበት 2006 የውድድር ዘመን ግሩም አቋም አሳይቶ የነበረ ቢሆንም ወደ ሀዋሳ ከተማ ከተዛወረ በኋላ የመሰለፍ እድል ባለማግኘቱ ወደ ቀድሞ ክለቡ ተመልሶ ነበር፡፡ ዘንድሮም በሌላ የውሰት ውል ወደ አዳማ ከተማ አምርቷል፡፡

Leave a Reply