ዝውውር | ኄኖክ ካሳሁን ወደ ጅማ አባ ቡና አመራ

በክለቦች መካከል እየተደረገ የሚገኘው የውሰት ዝውውር ዘንድሮ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ጅማ አባ ቡናም ሁለተኛ የውሰት ዝውውሩን በማድረግ የአዳማ ከተማው አማካይ ኄኖክ ካሳሁንን እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ የሚቆይ የውሰት ውል አስፈርሞታል፡፡

በውድድር አመቱ በአማካይ ስፍራ ላይ ክፍተቶች የታዩበት ጅማ አባ ቡና ሁለት አማካይ ተጫዋቾችን ማስፈረም ችሏል፡፡ ከኄኖክ በፊት የኢትዮ ኤሌክትሪኩን አብዱልሀኪም ሱልጣን በተመሳሳይ የውሰት ውለል ማስፈረሙ የሚታወስ ነው፡፡

ኄኖክ ካሳሁን የውሰት ዝውውር ሲያደርግ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ ከዚህ ቀደምም በደደቢት ቆይታው ወደ ዳሽን ቢራ አምርቶ ነበር፡፡ ደደቢትን ለቆ አዳማ ከተማን የተቀላቀለው ዘንድሮ ሲሆን በሊጉ ተቀይሮ በመግባት ጨዋታዎች ማድረግ ችሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *