ኢትዮጵያው የኤል ኤንታግ ኤል ሃርቢ የፊት መስመር ተጫዋች ኡመድ ኡኩሪ ግብ ማስቆጠሩን ቀጥሏል፡፡ ከቀናት በፊት በግብፅ ፕሪምየር ሊግ 19ኛ ሳምንት ኤል ሃርቢ ከኢስማኤሊ ጋር 1 አቻ በተለያየበት ጨዋታ ኡመድ ክለቡን አቻ ያደረገች ግብ አስቆጥሯል፡፡ ኤስማኤሊን ቀዳሚ ያደረገች ግብ የቀድሞ የፈርኦኖቹ ኮከብ ሆስኒ አብደራቦ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ኡመድ በሊጉ ያስቆጠረውን የግብ መጠን ወደ አምስት ከፍ ሲያደርግ ሁለት ግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል፡፡ ኡመድ በግሉ ጥሩ ብቃት ላይ የሚገኘ ቢሆንም ክለቡ ኤል ኤንታግ ኤል ሃርቢ በደረጃው መሻሻልን እያሳየ አይገኝም፡፡ ቅዳሜ በ20ኛ ሳምንት ጨዋታ ኤል ኤንታግ ኤር ሃርቢ ከሜዳው ውጪ አረብ ኮንትራክተርስን የሚገጥም ይሆናል፡፡