ዝውውር | ዳንኤል ራህመቶ ወደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አምርቷል

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ዳንኤል ራህመቶን በውሰት ውል ከኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት አስፈርሟል፡፡ እስከ ውድድር ዘመኑ መጨረሻም በቀዮቹ ቤት ይቆያል፡፡

የግራ መስመር ተከላካይ የሆነው ዳንኤል አዲስ አበባ ፖሊስን ለቆ ወደ ኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት የተዛወረው በዘንድሮው የውድድር ዘመን መጀመርያ ነበር፡፡

ዳንኤል በ2008 (አምና) የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን አባል የነበረ ሲሆን ከሶማልያ ጋር በተደረገው የአፍሪካ ከ20 አመት በታች ዋንጫ ቅድመ ጨዋታ ላይ ኢትዮጵያን በአምበልነት መምራቱ የሚታወስ ነው፡፡

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ባለፈው ሳምንት አጥቂው ተክሉ ተስፋዬን ማስፈረሙ የሚታወስ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *