አዳማ ከተማ ተገኔ ነጋሽን በዋና አሰልጣኝነት ሾሟል

አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ የኢትዮዽያ ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ ከአዳማ ከተማ ጋር የሚለያዩ በመሆኑ ክለቡ ቀጣዩን አሰልጣኝ ከወዲሁ ሾሟል፡፡

የአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ረዳት ሆነው ሲሰሩ የቆዩት ተገኔ ነጋሽን ቡድኑን በዋና አሰልጣኝነት እንዲመሩ ሀላፊነት ሰጥቷል፡፡ አሽቻለው ኃይለሚካኤል ደግሞ የተገኔ ነጋሽ ረዳት ሆነው እንዲሰሩ ሾሟቸዋል፡፡

ክለቡ የአሰልጣኝ ሹመቱን ዝርዝር ይፋ ያላደረገ ሲሆን እስከ አመቱ መጨረሻ ወይስ በቋሚነት እንደተሾሙ ወደፊት እንደሚገለጽ ከክለቡ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ላለፉት 3 አመታት ክለቡን በዋና አሰልጣኝነት የመሩት አሸናፊ በቀለ በ16ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አዳማ ከተማ ከሜዳው ውጪ ድሬዳዋን በሚገጥምበት ጨዋታ ቡድናቸውን ለመጨረሻ ጊዜ ይመራሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *