ዳሽን ቢራ ሳሙኤል አለባቸውን አስፈረመ

በወራጅ ቀጠና የሚገኘው ዳሽን ቢራ በዝውውር መስኮቱ ተጫዋቾችን ማስፈረሙን ቀጥሎበታል፡፡ ባለፈው ሳምንት የደደቢቱ አጥቂ አሸናፊ አደምን ያስፈረመ ሲሆን አሁን ደግሞ ከመከላከያ ጋር ውዝግብ ውስጥ የነበረውን ሳሙኤል አለባቸውን አስፈርሟል፡፡

ሳሙኤል ከክለቡ ጋር ልምምድ ያደረገ ሲሆን አርብ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ላለው ጨዋታም ሊሰለፍ እንደሚችል የክለቡ የፌስቡክ ገፅ አስነብቧል፡፡

የቀድሞው የመብራት ኃይል ድንቅ የተከላካይ አማካይ በዚህ የውድድር አመት መጀመርያ ልምምድ ላይ ባለመገኘቱ በክለቡ የተቀጣ ሲሆን አብዛኛውን የውድድር ዘመን ሳይጫወት አሳልፏል፡፡ በዚህም ምክንያት በውድድር ዘመኑ አጋማሽ የዝውውር መስኮት ወደ ኢትዮጵያ መድን ይዛወራል ተብሎ ተገምቶ ነበር፡፡ ነገር ግን በውሰት ውሉ ላይ ተጫዋቹ ከመድን ገንዘብ እንዲሰጠው በመጠየቁ ዝውውሩ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

ሳሙኤል አለባቸው ለዝውውሩ ምን ያህል እንደተከፈለው እንዲሁም የዝውውሩ ሁኔታ በግልፅ አልታወቀም፡፡

{jcomments on}

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *