ወላይታ ድቻ ተመሰገን ዱባን ከአርባምንጭ ከተማ አስፈርሟል፡፡ ድቻ ተጫዋቹን ያዘዋወረው በዚህ የዝውውር መስኮት እንደተለመደው በውሰት ውል ሳይሆን ሙሉ ለሙሉ በፊርማ ነው፡፡ አሰልጣኝ መሳይ በ3 ተጫዋቾች በሚያዋቅሩት የፊት መስመር ላይ ተመስገን በመስመር እና መሀል አጥቂነት ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡
ፈጣኑ የመስመር አጥቂ ተመስገን በአርባምንጭ የመጀመርያ የውድድር ዘመኑ ድንቅ ጊዜ ቢያሳልፍም ባለፉት ሁለት የውድድር ዘመናት ከቡድኑ የመጀመርያ ተሰላፊነት ውጪ ሆኖ ቆይቷል፡፡
ወላይታ ድቻ የቀሩትን የዝውውር ቀናት ተጠቅሞ ተጨማሪ ተጫዋቾችን ከከፍተኛ ሊግ ክለቦች በማምጣት ክፍተቶችን ለመድፈን እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የገለፁት የቡድኑ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ዝውውሮችነ ካሳኩ ብዙም የማይጠቀሙባቸውን ተጫዋቾች እንደሚያሰናብቱ ተናግረዋል፡፡
ድቻ በዚህ የዝውውር መስኮት ከተመስገን በተጨማሪ አሳምነው አንጀሎን ከድሬዳዋ ከተማ ፣ ፍራኦል መንግስቱን ከኢትዮጵያ ቡና በውሰት ማስፈረሙ የሚታወስ ነው፡፡