ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ወልድያ – ቀጥታ የጽሁፍ ስርጭት

​​FTኢት. ንግድ ባንክ 0-0  ወልድያ 


ተጠናቀቀ!
ጨዋታው ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተፈፅሟል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 4

የተጫዋች ለውጥ – ባንክ
77′ አቢኮይ ሻኪሩ ወጥቶ ሳሙኤል ዮሀንስ ገብቷል፡፡

75′ ያሬድ ብርሀኑ ከመስመር ያሻገረውን ኳስ አንዱአለም ንጉሴ ሞክሮ ፋሪስ በጥሩ ሁኔታ አድኖበታል፡፡ ግሩም ሙከራ

የተጫዋች ለውጥ – ወልድያ
73′ ታዬ አስማረ እና ጫላ ድሪባ ወጥተው ያሬድ ብርሀኑ እና ሙሉጌታ ረጋሳ ገብተዋል፡፡

70′ ፒተር ወደ ግብ የመታውን ኳስ ቤሊንጌ ሲመልሰው በቅርብ ርቀት የነበረው ቢንያመም ሞክሮ ቤሊንጌ በድጋሚ አድኖታል፡፡

66′ ከቅጣት ምት የተሻማውን ኳስ ፒተር በግምባር ገጭቶ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

63′ ታድዮስ ወልዴ የመታው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

53′ አንዱአለም ንጉሴ ከርቀት የተሻገረለትን ኳስ በቮሊ ሞክሮ ፋሪስ በቀላሉ ይዞበታል፡፡

ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀመረ፡፡


እረፍት!
የመጀመርያው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ያለ ግብ ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 1

40′ ጨዋታው ፍሰት የሌለው እና በተደጋጋሚ የዳኛ ፊሽካ የሚቆራረጥ እነንቅስቃሴ እየታየበት ነው፡፡

37′ ፍቅረየሱስ በግንባሩ የገጨውን ኳስ ቤሊንጌ አውጥቶበታል፡፡

32′ ፒተር ኑዋዲኬ የመታውን ቅጣት ምት ቤሊንጌ በጥሩ ሁኔታ አውጥቶታል፡፡

ቢጫ ካርድ
28′ ፍቃዱ ደነቀ በኤሪክ ኮልማን ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

22′ ቢንያም በላይ በግሩም አንድ ሁለት ቅብብል ወደ ውስጥ በመግባት የሞከረው ኳስ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

21′ አንዱአለም ንጉሴ የግብ ጠባቂውን አቋቋም ተመልክቶ የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡ ጎል ለመሆን የቀረበ ሙከራ ነበር፡፡

11′ ፒተር ኑዋዲኬ በግንባሩ የገጨውን ኳስ ቤሊንጌ መልሶታል፡፡

5′ ወልድያዎች የግብ ሙከራ ማድረግ ባይችሉም ወደ ጎል በመድረስ የተሻሉ ናቸው፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው በንግድ ባንክ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡

09:55 የሁለቱም ቡድን ተጫዋቾች አሟሙቀው ወደ መልበሻ ክፍል ተመልሰዋል፡፡

09:30 ቡድኖቹ ለማሟሟቅ ወደ ሜዳ ገብተዋል፡፡


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰላለፍ

33 ፋሪስ አለዋ

15 አዲሱ ሰይፉ – 16 ቢኒያም ሲራጅ – 19 ፍቃዱ ደነቀ – 44 አንተነህ ገብረክርስቶስ

88 ታድዮስ ወልዴ – 6 ደረጄ መንግስቱ – 80 ቢኒያም በላይ – 2 ፍቅረየሱስ ተወልደብርሃን
19 ፒተር ንዋድኬ – 13 አቢኮዬ ሻኪሩ

ተጠባባቂዎች
1 ሙሴ ገብረኪዳን
5 ቶክ ጀምስ
12 አቤል አበበ
21 ዮናስ ገረመው
26 ጌቱ ረፌራ
17 ሳሙኤል ዮሃንስ


የወልድያ አሰላለፍ

16 ኤሚክሪል ቢሌንጌ

3 ቢኒያም ዳርሰማ — 14 ያሬድ ዘውድነህ — 25 አዳሙ መሀመድ — 6 ዮሐንስ ኃይሉ

21 ሀብታሙ ሸዋለም – 28 ታዬ አስማረ – 8 ምንያህል ይመር – 29 ኤሪክ ኮልማን

15 ጫላ ድሪባ – 2 አንዱአለም ንጉሴ

ተጠባባቂዎች

64 ዳዊት አሰፋ
5 ያሬድ ሀሰን
12 ያሬድ ብርሃኑ
4 ሙሉነህ ጌታሁን
10 ሙሉጌታ ረጋሳ
19 አለማየው ግርማ
23 ሙሉጌታ ወ/ጊዮርጊስ


ዳኛ
ፌዴራል ዳኛ ይጋለም ወልደጊዮርጊስ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመራል፡፡ ደረጄ ገብሬ 


ያለፉት 3 ጨዋታዎች ውጤት

ኢት. ንግድ ባንክ | ተሸነፈ | ተሸነፈ | ተሸነፈ

ወልድያ | አሸነፈ | አቻ | አቻ


ግንኙነት

ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ ሲገናኙ ይህ ለ4ኛ ጊዜ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በነበራቸው ግንኙነት ሁለቱም አንድ አንድ ሲያሸንፉ ቀሪውን አንድ ጨዋታ በአቻ ውጤት ፈፅመዋል፡፡


ደረጃ
ወልድያ 19 ነጥቦችን በመሰብሰብ 10ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ13 ነጥቦች 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡


ጤና ይስጥልኝ ክቡራት እና ክቡራን!

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እነሆ ከእረፍት ተመልሷል፡፡ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ወልድያ በሚያደርጉት የ16ኛ ሳምንት ጨዋታም ይጀመራል፡፡ ይህንን ጨዋታ በዚህ ገፅ ላይ በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት እናደርሳችኀለን፡፡

መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር!

1 Comment

  1. ምኑ ነው 5-2 ? (ለማንኛውም እየጠበቅን ነው። ግን እባካችሁ የኢትዮጵያ 1ኛ ሊግ ያለፈዉን ሳምንት ውጤት?

Leave a Reply