ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ጅማ አባ ቡና | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

FTኢትዮ ኤሌክትሪክ  0-0  ጅማ አባ ቡና 


ጨዋታው ያለግብ ተጠናቋል !

90+1 ኪዳኔ ከግራ መስመር ከረጅም ርቀት የሞከረውን ኳስ ኤቡ አድኖበታል ።

90′ ጭማሪ ደቂቃ 3 !

85′ ፍፁም ገ/ማርያም በግራ መስመር ይዞ የገባውን ኳስ በቀጥታ ቢሞክርም ወደ ላይ ተነስቶበታል ።

የተጫዋች ለውጥ – ጅማ አባ ቡና
80′ ዳዊት ተፈራ ወጥቶ መሀመድ ናስር ገብቷል፡፡

77′ ኄኖክ ኢሳያስ የሞከረውን ኳስ ሱሌይማን በግሩም ሁኔታ አውጥቶታል፡፡

65′ ጨዋታው በጅማ አባ ቡና የሜዳ አጋማሽ ላይ በኢትዮ ኤሌክትሪክ የበላይነት እየተደረገ ይገኛል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ጅማ አባ ቡና
58′ ሱራፌል አወል ወጥቶ ኄኖክ ኢሳይያስ ገብቷል፡፡

55′ በሀይሉ ተሻገር ከሙሉአለም ጋር በአንድ ሁለት ቅብብል ያገኘውን ኳስ ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

54′ ዳዊት እስጢፋኖስ የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ኤሌክትሪክ
ብሩክ አየለ እና ዋለልኝ ገብሬ ወጥተው ሙሉአለም ጥላሁን እና በሃይሉ ተሻገር ገብቷል፡፡


እረፍት!
የመጀመርያው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ያለ ግብ ተጠናቋል፡፡


ተጨማሪ ደቂቃ – 1

ቢጫ ካርድ
44′
ታደለ ምህረቴ በብሩክ አየለ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

43′ ዳዊት ተፈራ ከርቀት የመታውን ኳስ ሱሌይማን ይዞበታል፡፡

38′ አሜ መሀመድ በግራ እግሩ አክርሮ የመታው ኳስ በግቡ ቋሚ መሬት ለመሬት ወጥቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
36′
ዋለልኝ ገብሬ የማስጠንቀቂያ ካርደድ ተመልክቷል፡፡

32′ አሜ መሀመድ ከሳጥኑ ጠርዝ የመታው ኳስ ኢላማውን ሳያገኝ ወጥቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
26′
በረከት ተሰማ አሜ መሀመድ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
23′
ኄኖክ ካሳሁን እና ዳዊት ተፈራ የዳኛ ውሳኔ በመቃወም የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

20′ አሜ መሀመድ ከርቀት አክርሮ የመታው ኳስ በግቡ ቋሚ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡ ግሩም ሙከራ

15′ ሁለቱም ቡድኖች ወደ ግብ ለመቅረብ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

ቢጫ ካርድ
7′
ሲሴይ ሀሰን የጨዋታውን የመጀመሪያ ማስጠንቀቂያ ካርደድ ተመልክቷል፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው በጅማ አባ ቡና አማካኝነት ተጀመረ፡፡


የኢትዮ ኤሌክትሪክ አሰላለፍ

22 ሱሌይማን አቡ

11 አወት ገ/ሚካኤል – 21 በረከት ተሰማ – 26 ሲሴይ ሀሰን – 7 አለምነህ ግርማ

 5 አዲስ ነጋሽ -10 ዳዊት እስጢፋኖስ – 24 ዋለልኝ ገብሬ – 9 ብሩክ አየለ

16 ፍፁም ገ/ማርያም – 4 ኢብራሂም ፎፋኖ

ተጠባባቂዎች
1 ኦኛ ኦሜኛ
19 ደረጄ ሀይሉ
23 አሸናፊ ሽብሩ
12 ተክሉ ተስፋዬ
27 ስንታየሁ ሰለሞን
8 በሃይሉ ተሻገር
18 ሙሉአለም ጥላሁን


የጅማ አባ ቡና አሰላለፍ

1 ሙላት አለማየሁ

5 ጀሚል ያዕቆብ – 12 ቢያድግልኝ ኤልያስ – 21 በኃይሉ በለጠ – 6 ታደለ ምህረቴ

11 ዳዊት ተፈራ – 27 ክሪዚስቶም ንታንቢ – 23 ኄኖክ ካሳሁን – 16 ኪዳኔ አሰፋ

9 አሜ መሀመድ – 8 ሱራፌል አወል

ተጠባባቂዎች

35 በሽር ደሊል
4 ሀይደር ሸረፋ
15 ኄኖክ ኢሳይያስ
14 ሂድር ሙስጠፋ
7 በድሉ መርዕድ
25 መሀመድ ናስር
19 ልደቱ ጌታቸው


ዳኛ
ኢንተርናሽናል ዳኛ በላይ ታደሰ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመራል፡፡

ያለፉት 3 ጨዋታዎች ውጤት

ኢትዮ ኤሌክትሪክ | ተሸነፈ | ተሸነፈ | አሸነፈ

ጅማ አባ ቡና
| ተሸነፈ | አቻ | አሸነፈ

ግንኙነት

ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ ሲገናኙ ይህ ለ2ኛ ጊዜ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በአንደኛው ዙር የመጀመርያ ጨዋታ ተገናኝተው ያለ ግብ ጨዋታቸውን ፈፅመዋል፡፡

ደረጃ
ኤሌክትሪክ15 ነጥቦችን በመሰብሰብ 11ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ጅማ አባ ቡና በ13 ነጥቦች 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

ጤና ይስጥልኝ ክቡራት እና ክቡራን!

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እነሆ ከእረፍት ተመልሷል፡፡ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ጅማ አባ ቡና የሚያደርጉት የ16ኛ ሳምንት ጨዋታን በዚህ ገፅ ላይ በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት እናደርሳችኀለን፡፡

መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር

1 Comment

Leave a Reply