ማርያኖ ባሬቶ ፊርማቸውን አኖሩ

አሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር የጀመሩትን ድርድር በስኬት አጠናቀዋል፡፡ ዛሬ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በኢሊሌ ሆቴል በተደረገው ስነስርአትም ማርያኖ ባሬቶ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው በይፋ ፊርማቸውን አስቀምጠዋል፡፡ ፖርቱጋላዊው የ57 አመት አሰልጣኝ የ2 አመት ኮንትራት የተፈራረሙ ሲሆን ወርሃዊ ደሞዛቸውም 18 ሺህ የአሜሪካን ዶላር እንዲሆን ተስማምተዋል፡፡

በስምምነታቸው መሰረት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለአሰልጣኙ የመኖርያ ቤት ፣ ተሸከርካሪ እና የነዳጅ ወጪ ይሸፍናል፡፡

ፌዴሬሽኑ እና አሰልጣኙ በአሰልጣኝ ቡድኑ አወቃቀር ላይ ስምምነት የደረሱ ሲሆን በቅርቡም ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው የአካል ብቃት ፣ የግብ ጠባቂ እና ረዳት አሰልጣኝ ይቀጠርላቸዋል፡፡

አሰልጣኝ ባሬቶ ስራቸውን በይፋ የሚጀምሩት ከ1 ሳምንት በኋላ ሚያዝያ 23 ቀን 2006 አም ነው፡፡

{jcomments on}

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *