FT ደደቢት 0-0 ኢትዮጵያ ቡና
ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡
90+1 ከሳምሶን ጥላሁን የደረሰውን ኳስ በመጠቀም ጌታነህ ከበደ ከቡናዎች ሳጥን ውስጥ መሬት ለመሬት ቢሞክርም ኳስ በጎን ወጥታለች ።
90′ ጭማሪ ደቂቃ 3!
89′ ደደቢቶች ወደ ቡናዎች የሜዳ ክፍል በመግባት ተጭነው ለመጫወት እየሞከሩ ይገኛሉ ።
86′ ጌታነህ ከበደ በግል ጥረቱ በግራ መስመር በቡና ተከላካዮች መሀል ይዞ የገባውን ኳስ ለሽመክት ወደ ውስጥ ለማሳለፍ ቢሞክርም ኳሷ ሽመክት ጋር ከመድረሷ በፊት ሀሪሰን ይዟታል ።
83 ‘ቢጫ ካርድ ደደቢት !
ከደር ኩኒባሊ ጋቶችን መሀል ሜዳ ላይ ጎትቶ በማስቀረቱ የጨዋታውን የመጀመሪያ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
83’የተጨዋች ለውጥ ኢትዮጵያ ቡና
ያቡን ዊልያም በእያሱ ታምሩ ተተክቷል
81′ የደደቢቶች ጥቃት በኢትዮጵያ ቡና የሜዳ ክፍል ላይ ጎል ለማስቆጠር የሚረዳ ቦታ ላይ ከመድረሱ በፊት በተደጋጋሚ የተቅቋረጠ ይገኛል ።
78′ በደደቢት ሳጥን የቀኝ ክፍል ላይ አስቻለው ከኤልያስ የተቀበለውን ኳስ በፍጥነት ይዞ ለመግባት ሲሞክር ኳሷ ረዝማበት በአግባቡ መቆጣጠር ሳይችል ቀርቶ ወደውጪ ወጥታበታለች ።
76′ የኢትዮጵያ ቡና አማካዮች ተቀራርበው ኳስ በመቀባበል ወደ ደደቢት የግብ ክልል ለመግባት የሚያደርጉት ሙከራ በደደቢት ጠንካራ የመከላከል መስመር እየተመከተባቸው ነው ።
74′ የተጨዋች ለውጥ ኢትዮጵያ ቡና
አክሊሉ ዋለልኝ ወጥቶ አማኑኤል ዮሀንስ ገብቷል ።
71′ የተጨዋች ለውጥ ደደቢት
ሮበን ኦባማ ዳዊት ፍቃዱን በመተካት ወደሜዳ ገብቷል ።
67′ ሳሙኤል ሳኑሚ ከደደቢቶች ሳጥን ጠርዝ ላይ ከኤልያስ ማሞ የተቀበለውን ኳስ አይናለም ኃይለን በማለፍ ከክሌመንት ጋር ብቻውን ተገናኝቶ ቢሞክርም በሚያስገርም ሁኔታ ኢላማውን መጠበቅ ሳይችል ቀርቷል።
65′ ቡናማዎቹ ጫና ፈጥረው እየተጫወቱ ይገኛሉ ። አብዛኛው የጨዋታ እንቅስቃሴም በደደቢቶች ሜዳ ላይ ሆኗል ።
62′ አህመድ ረሻድ በደደቢቶች ፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ከመሀል ተከላካዩ አክሊሉ አያነው የነጠቀውን ኳስ ከቅርብ ርቀት አክርሮ ቢሞክርም ኳሷ የግቡን አግዳሚ ውስጠኛ ክፍል ለትማ ወጥታለች ። ከእስካሁኖቹ ሙከራዎች በጣሙን ለጎል የቀረበ አጋጣሚ !
59′ አህመድ ረሻድ ከግራ መስመር በመነሳት ለአስቻለው ያሳለፈለትን ኳስ አስቻለው ቢሞክርም ኳሷ በአግዳሚው ወደላይ ወጥታለች ።
57′ ኤልያስ እና እያሱ የተቀባበሉት ኳስ ሳኑሚ ጋር ደርሶ አጥቂው ከሳጥን ውጪ ቢሞክርም ክሌመንት ይዞበታል ።
55′ ከመጀመሪያው አጋማሽ ጀምሮ አሁንም የተጨዋቾች ግጭት እየተመለከትን ነው ። አልቢትሩ እስካሁን ካርድ ከማሳየት መቆጠባቸው በተለይ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎችን ደስተኛ አላደረገም ።
52′ የተጨዋች ለውጥ ደደቢት
ኤፍሬም አሻሞ ወጥቶ አቤል ያለው ገብቷል
50′ የሁለተኛው አጋማሽ አጀማመር ከመጀመሪያው በተቃራኒ የተቀዛቀዘ ሆኗል ።
47′ ጋቶች ፓኖም ከእያሱ ታምሩ ጋር መሀል ሜዳ ላይ ተቀባብሎ ወደፊት በመጠጋት ከረጅም ርቀት የሞከራው ኳስ ወደላይ በመነሳት በግቡ አናት ወጥቷል ።
46′ ሁለተኛው አጋማሽ በሳሙኤል ሳኑሚ አማካይነት ተጀምሯል ።
እረፍት!!
የመጀመርያው አጋማሽ ያለ ግብ ተጠናቋል፡፡
45 ‘ ጭማሪ ደቂቃ 2 !
43′ ቡናዎች በቀኝ መስመር የሰነዘሩትን ጥቃት ተከትሎ ሳኑሚ ወደውስጥ የላካትን ኳስ መጠቀም አልቻሉም ።
42′ ሰማያዊዎቹ በኢትዮጵያ ቡና ሜዳ ላይ ጫና ለመፍጠር ቢሞክሩም ከመስመር የሚያሻሟቸው ኳሶች በቀላሉ በሀሪሰን እጆች መሀል እየገቡ ነው ።
40′ አሁን ጨዋታው ሙሉ ለሙሉ በመሀል ሜዳ ላይ እንቅስቃሴ የተገደበ ሆኗል ።
35′ የሁለቱም ቡድኖች የማጥቃት ሂደቶች ሶስተኛው የሜዳ ክፍል ላይ ሲደርሱ እየተቋረጡ ይገኛሉ ።
33′ የግብ ሙከራዎች ቁትር ቢቀንስም ጨዋታው ከፍተኛ የተጨዋቾች ሽኩቻ እያስተናገደ ነው። ኢንተርናሽናል አልቢትር ኃይለየሱስ ባዘዘውም ካርድ ሳይመዙ ተጨዋቾችን በማረጋጋት ጨዋታውን ለመቆጣጠር እየሞከሩ ነው ።
30′ የተጨዋቾች ግጭት በጨዋታው እየተበራከተ ነው ።
27′ መሀል ሜዳ ላይ ከእያሱ የተቀበለውን ኳስ የክሌመንትን መውጣት በማየት ሳኑሚ በረጅሙ ወደጎል ቢሞክርም ኳስ በግቡ ወጥታለች ።
26′ ኤልያስ ማሞ በግራ መስመር የተገኘውን የማዕዘን ምት በአጭሩ ለአስቻለው ግርማ አቀብሎት ። አስቻለው በቀጥታ ሲሞክር ክሌመንት አድኖበታል ።
25 ‘ ኩሊባሊ ተነስቶ ጨዋታው ቀጥሏል ።
24′ ከድር ኩሊባሊ ጉዳት ደርሶበት የህክምና ዕርዳት እየተደረገለት በመሆኑ ጨዋታው ተቋርጧል ።
20′ በሁለቱ ቡድኖች መሀል ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ እየተመለከትን እንገኛለን ።
19′ ሽመክት ጉግሳ ከቀኝ መስመር ያሻማውን ኳስ ጌታነህ ከበደ በግንባሩ በመግጨት ቢሞክርም ሀሪሰን ይዞበታል ።
15′ ጨዋታው ከመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች አንፃር ቀዝቀዝ ያለ ይመስላል ። ኢትዮጵያ ቡናዎችም እንደመጀመሪያው ወደግብ እየተጠጉ አይደለም ። ደደቢቶች ኳስ ተቆጣጥረው በተጋጣሚያቸው ሜዳ ላይ ለመቆየት ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ።
13′ ዳዊት ፍቃዱ ከጌታነህ ከበደ ተነጥሎ እና ለአማካይ ክፍሉ በጣም ቀርቦ እየተጫወተ ይገኛል ። የተጨዋቹ ከወትሮው ቦታው የሚና ለውጥ ማድረጉ የኢትዮጵያ ቡናን የመሀል ክፍል የበላይነት ለመቀነስ የተደረገ ይመስላል ።
10′ እስካሁን ኢትዮጵያ ቡናዎች ዕድሎችን በመፍጠር የተሻሉ ሆነዋል ። የደደቢቶች ጥቃት አደጋ ለመፍጠር አቅም ያነሰው ይመስላል ።
9′ አህመድ ረሻድ ከግራ መስመር ያሻማውን ጥሩ ኳስ በጥሩ አቋቋም ላይ የነበረው ሳሙኤል ሳኑሚ በግንባሩ ቢሞክርም በግቡ አናት ወጥቶበታል ።
6′ ጋቶች ፓኖም ከኤልያስ ማሞ የተቀበለውን ኳስ ከረጅም ርቀት ቢሞክርም ወደላይ ወጥቶበታል ።
4′ ቡናዎች ከራሳቸው ግብ ላይ የነጠቁትን ኳስ በፈጣን መልሶ ማጥቃት ይዘው ወደደቢት የሜዳ ክፍል በአስቻለው ግርማ አማካይነት ይዘው ቢገቡም ከ አስቻለው ወደ አህመድ የተላከችው ኳስ በደደቢቶች ተነጥቃለች ።
1’ ኢትዮጵያ ቡና በቀኝ መስመር በአብዱልከሪም በኩል የሰነዘረው ጥቃት በሳሙኤል ሳኑሚ ወደ ውስጥ ቢሻገርም ኳሱን ለመጠቀም የተዘጋጀ ሰው ባለመኖሩ ውጤታማ መሆን አልቻለም ። ይሄው ጥቃት ቀጥሎም ኤልያስ ማሞ ከደደቢት ሳጥን ጠርዝ ላይ በቀጥታ የሞከረው ኳስ በግቡ ቋሚ ተመልሷል ። አደገኛ አጀማመር !
1′ ጨዋታው በደደቢቱ አጥቂ ጌታነህ ከበደ አማካይነት ተጀምሯል ።
09 ፡ 00 የቡድኖቹ ተጨዋቾች ወደሜዳ ገብተዋል ።
08 ፡ 55 የቡድኖቹ ተጨዋቾች ከመልበሻ ቤት እስኪወጡ በጉጉት እየጠበቁ ያሉት ደጋፊዎች በሕብረዝማሬ ስታድየሙን እያደመቁት ይገኛሉ ።
የኢትዮጵያ ቡና አሰላለፍ
99 ሀሪስን ሄሱ
15 አብዱልከሪም መሀመድ – 16 ኤፍሬም ወንድወሰን – 5 ወንድይፍራው ጌታሁን – 13 አህመድ ረሽድ
9 ኤልያስ ማሞ – 19 አክሊሉ ዋለልኝ – 25 ጋቶች ፓኖም
14 እያሱ ታምሩ – 11 ሳሙኤል ሳኑሚ – 24 አስቻለው ግርማ
ተጠባባቂዎች
29 ዮሃንስ በዛብህ
4 ኤኮ ፌቨር
28 ያቡን ዊልያም
17 አብዱልከሪም ሀሰን
3 መስዑድ መሀመድ
21 አስናቀ ሞገስ
8 አማኑኤል ዮሐንስ
የደደቢት አሰላለፍ
33 ክሌመንት አዞንቶ
15 ደስታ ደሙ – 6 አይናለም ኃይለ – 14 አክሊሉ አየነው – 10 ብርሃኑ ቦጋለ
19 ሽመክት ጉግሳ – 8 ሳምሶን ጥላሁን – 24 ኩሊባሊ ከድር– 21 ኤፍሬም አሻሞ
9 ጌታነህ ከበደ – 17 ዳዊት ፍቃዱ
ተጠባባቂዎች
22 ታሪክ ጌትነት
16 ሰለሞን ሐብቴ
27 እያሱ ተስፋዬ
8 አስራት መገርሳ
18 አቤል እንዳለ
12 ሮበን ኦባማ
5 አንዳህ ኩዌኩ
08 ፡ 45 ተጨዋቾቹ አሟሙቀው በመጨረስ ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል በመቀጠል የሁለቱን ቡድኖች አሰላለፍ ይዘን እንመለሳለን ።
08፡30 ተጨዋቾቹ ሰውነታቸውን ለማማሟቅ ወደ ሜዳ ገብተዋል ።
08 ፡ 20 ጨዋታው ሊጀመር 40 ደቂቃዎች ቢቀሩትም በተለምዶው ካታንጋ እና ዳፍ ትራክ ከሚባሉት ቦታዎች ውጪ የስቴድየሙ አብዛኛው ክፍል በደጋፊዎች ተሞልቷል ።
ዳኛ
የእለቱን ጨዋታ የ2007 የውድድር ዘመን ኮከብ ዳኛ ኢንተርናሽናል አርቢቴር ኃይለየሱስ ባዘዘው ይመራዋል ።
ያለፉት 3 ጨዋታዎች ውጤት
ኢትዮጵያ ቡና | አሸነፈ | አሸነፈ | አቻ
ደደቢት | አቻ | ተሸነፈ | አሸነፈ
ግንኙነት
ሁለቱ ቡድኖች 15 ጊዜ ሲገናኙ ምንም ጊዜ አቻ ውጤት አላስመዘገቡም ። ደደቢት 9ኙን በማሸነፍ ቅድሚያ ሲይዝ ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ በ6ቱ ድል ማድረግ ችሏል ። በነዚህ ግንኙነቶች ደደቢት 29 እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና 23 ግቦችን ማስቆጠር ችለዋል ።
ደረጃ
የኢትዮጵያ ቡና 24 ነጥቦችን በመሰብሰብ 6ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ደደቢት በበኩሉ በ27 ነጥቦች ይዞ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
ጤና ይስጥልኝ ክቡራት እና ክቡራን !
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ሳምንት በጉጉት በሚጠበቀው ታላቅ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡናን ከ ደደቢት የሚያገናኝ ይሆናል ። በአዲስ አበባ ስታድየም ከቀኑ 9 ሰዐት ጀምሮ የሚደረገውን የሁለቱን ቡድኖች ፍልሚያም በቀጥታ የፅሀፍ ስርጭት ልናስነብባችሁ ተዘጋጅተናል !
መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር !