አርባምንጭ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

 2ኛ አርባምንጭ ከተማ  1-4  ቅዱስ ጊዮርጊስ 

89′ ታደለ መንገሻ || 43′ በኃይሉ አሰፋ፣ 65′ 71′ አዳነ ግርማ፣ 90+1′ ብራሂማ ብሩኖ ኮኔ


በስቴዲዮሙ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ረብሻ ተነስቷል።


ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ 4-1 አሸናፊነት ተጠናቋል።


90+1′ ጎልልል!! ቅዱስ ጊዮርጊስ

ብራሂማ ኮኔ ተጨማሪ ግብ ለፈረሰኞቹ አስቆጥሯል።


90′ ተጨማሪ ሰዐት – 4 ደቂቃ


89′ ጎልልል!! አርባምንጭ ከተማ

ታደለ መንገሻ በቅጣት ምት ግሩም ጎል አስቆጠረ።


88′ ቢጫ – ቅዱስ ጊዮርጊስ 

አስቻለው ታመነ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል።


87′ ቀይ ካርድ – አርባምንጭ ከተማ

በረከት ቦጋለ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።


85′ ከመጨረሻው ጎል መቆጠር በኀላ ፈረሰኞቹ ብልጫ ወስደው ሲጫወቱ አርባምንጮች በተቃራኒው ተቀዛቅዘዋል።


78′ የተጫዋች ለውጥ – አርባምንጭ ከነማ 

አስጨናቂ ፀጋዬ ገብቶ ፀጋዬ አበራ ወጥቷል።


75′ የተጨዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

አዳነ ግርማ ወጥቶ ብራሂማ ኮኔ ገብቷል።


71′ ጎልልልል!! ቅዱስ ጊዮርጊስ

ተቀይሮ የገባው ፕሪንስ ከግራ መስመር ያሻገረለትን አዳነ ግርማ በግንባሩ ገጭቶ ግሩም ጎል አስቆጠረ።


70′ የተጨዋች ለውጥ አርባምንጭ 

እንዳለ ከበደ ገብቶ ገ/ሚካኤል ያዕቆብ ወጥቷል።


68′ በስቴዲዮሙ የሚገኘው ተመልካች በውጤቱ አዝኖ እየወጣ ይገኛል።


65′ ጎልልልል!  ቅዱስ ጊዮርጊስ

አዳነ ግርማ ፈረሰኞችን በሁለት ጎል ልዩነት እንዲመሩ ያስቻለች ግብ አስቆጥሯል።


63′ የተጨዋች ለውጥ – አርባምንጭ 

አማኑኤል ጎበና ወጥቶ አመለ ሚልኪያስ ገብቷል።


60′ አስፈሪው የፈረሰኞቹ የመልሶ ማጠቃት አጨዋወት የአርባምንጭ ከነማ  ተከላካይ መስመር ተጨዋቾችን  እየረበሸ ይገኛል። 


55′ አርባምንጭ ከተማ ወደ ጨዋታው የሚመልሰውን አጋጣሚ ለመፍጠር ጥረት በማድረግ ላይ ቢሆንም ጠንካራውን የፈረሰኞችን ተከላካይ ሰብሮ መግባት አልቻለም።


51′ ቢጫ – ቅዱስ ጊዮርጊስ 

ምንተስኖት አዳነ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል።


48′ ምንተስኖት አዳነ የማይታመን ግልፅ የጎል እድል አመከነ። የሚያስቆጭ አጋጣሚ! 


ተጀመረ!

ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአርባምንጭ ከተማ አማካኝነት ተጀምሯል!!


እረፍት!

የመጀመርያው አጋማሽ የጨዋታው ክፍለ ጊዜ በፈረሰኞቹ 1 – 0 መሪነት ተጠናቋል ።


45′ ተጨማሪ ሰዓት – 2 ደቂቃ


43′ ጎልልልል!!

በሀይሉ አሰፋ ፈረሰኞቹን ቀዳሚ ያደረገች ግብ አስቆጥሯል።


39′ ቢጫ – ቅዱስ ጊዮርጊስ 

ናትናኤል ዘለቀ የዳኛን ውሳኔ በመቃወም የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል።


33′ ታደለ መንገሻ ጥሩ የሚባል የግብ አጋጣሚ አግኝቶ ሳይጠቀምበት ቀርቷል።


32′ በስቴዲየሙ ለታደመው በርካታ ተመልካች የማይመጥን ያልተደራጀ እና ውበት የሌለው  የጨዋታ እንቅስቃሴ እየተመለከትን እንገኛለን።


29′ የጨዋታው የመጀመርያ ዒላማውን የጠበቀ ሙከራ –  ምንተስኖት አዳነ ከሳጥን ውጭ ወደግብ አክርሮ የመታውን ኳስ አንተነህ መሳ አድኖበታል።


28′ የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ 

አቡበከር ሳኒ በጉዳት ተቀይሮ ሲወጣ ፕሪንስ ሲቨሪን እሱን ተክቶ ገብቷል።


20′ በስቴዲዮሙ የተገኛው በርካታ ተመልካች ከሚያሳየው ውበት ያለው ድጋፍ ውጭ ጨዋታው እንደተጠበቀው ውበት ያለው እንቅስቃሴ እያስመለከተን አይደለም።


15′ ጨዋታው አንዴ ሞቅ አንዴ ቀዝቀዝ እያለ በሁለቱም በኩል በመሀል ሜዳ ላይ በሚደረግ እንቅስቃሴ ተገድቦ ቀጥሏል።


10′ አርባምንጭ ከተማ ይህ ነው የተባለ ግልፅ የግብ ሙከራ ባያደርግም በኳስ ቁጥጥሩ ብልጫ በመውሰድ ተጭኖ እየተጫወተ ይገኛል ።


5′ በሁለቱም በኩል ተመጣጣኝ በሆነ ወደ ጎል ለመቅረብ በሚደረግ ጥረት ጨዋታው ቀጥሏል።


ተጀመረ ! 

ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ አማካኝነት ተጀምሯል! 


ሁለቱ ቡድኖች በእለቱ ዳኞች እየተመሩ ወደ ሜዳ በመግባት ለስፖርት ቤተሰቡ የክብር ሰላምታ በማቅረብ ሰላምታ እየተለዋወጡ ይገኛሉ።


የአርባምንጭ ከነማ ደጋፊዎች ምንተስኖት አበራን የወሩ ኮከብ ተጨዋች በማድረግ የአርባምንጭ መገለጫ የሆነ በአሳ ቅርፅ የተሰራ ሽልማት ሲያበረክቱለት ፣ ለቀድሞ የአርባምንጭ ከነማ ተጨዋቾች ለታሪኩ ተስፋዬ እና ስለሺ ሽብሩ ደግሞ የክብር ሽልማት አበርክተዋል።


ሁለቱም ቡድኖች የቅድመ ጨዋታ ልምምዳቸውን አጠናቀው ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።


የአርባምንጭ ከተማ አሰላለፍ

1 አንተነህ መሳ

14 ወርቅይታደል አበበ – 5 አንድነት አዳነ – 16 በረከት ቦጋለ – 2 ተካልኝ ደጀኔ

10 ወንድሜነህ ዘሪሁን – 4 ምንተስኖት አበራ – 8 አማኑኤል ጎበና -17 ታደለ መንገሻ

22 ጸጋዬ አበራ – 19 ገብረሚካኤል ያዕቆብ

ተጠባባቂዎች

99 ጃክሰን ፊጣ
3 ታገል አበበ
7 እንዳለ ከበደ
15 ተመስገን ካስትሮ
12 አመለ ሚልኪያስ
25 አለልኝ አዘነ
18 አስጨናቂ ፀጋዬ


የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ

30 ሮበርት ኦዶንካራ

2 ፍሬዘር ካሳ – 13 ሳላዲን በርጊቾ – 15 አስቻለው ታመነ – 4 አበባው ቡታቆ

24 ያስር ሙገርዋ – 26 ናትናኤል ዘለቀ – 23 ምንተስኖት አዳነ

18 አቡበከር ሳኒ – 19 አዳነ ግርማ – 16 በሃይሉ አሰፋ

ተጠባባቂዎች
22 ዘሪሁን ታደለ
20 ዘካርያስ ቱጂ
21 ተስፋዬ በቀለ
11 ፕሪንስ ሰቨሪን
25 አንዳርጋቸው ይላቅ
3 መሀሪ መና
17 ብሩኖ ኮኔ


 08:40 ቁጥራቸው ከሃምሳ በላይ የሆኑ የቅዱስ ጊዮርጊስ የልብ ደጋፊዎች አምስት መቶ ኪሎ ሜትር አቋርጠው ክለባቸውን ለመደገፍ በስቴዲዮሙ ተገኝተዋል።


08: 35 በርካታ ቁጥር ያለው ተመልካች የአርባምንጭ ከፍተኛ ሙቀት ሳይበግረው በስቴዲዮሙ የታደመ ሲሆን ወደ ስቴዲዮም ለመግባት ከውጭ ረጃጅም ሰልፎች ይታያሉ።


08:30 ሁለቱም ቡድኖች ለማሟሟቅ ወደ ሜዳ ገብተዋል፡፡


ዳኛ
ኢንተርናሽናል ዳኛ ለሚ ንጉሴ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመራል፡፡


ያለፉት 3 ጨዋታዎች ውጤት

አርባምንጭ ከተማ | አሸነፈ | አቻ | አቻ

ቅዱስ ጊዮርጊስ
| አቻ | አቻ | አሸነፈ


ግንኙነት

ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ ሲገናኙ ይህ ለ12ኛ ጊዜ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም 11 ጊዜ ተገናኝተው ቅዱስ ጊዮርጊስ 8 ሲያሸንፍ አርባምንጭ 1 አሸንፏል፡፡ 2 ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል፡፡


ደረጃ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በ29 ነጥብ የሊጉ መሪ ሲሆን አርባምንጭ ከተማ በ22 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡


ጤና ይስጥልኝ ክቡራት እና ክቡራን!

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዙር የመጀመርያ ሳምንት ጨዋታዎች እየተካሄዱ ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም መካከል በዚህ ገጽ ላይ አርባምንጭ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያደርጉትን ጨዋታ በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ወደ እናንተ እናደርሳለን፡፡

መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር!

Leave a Reply