አአ ከተማ ሀዋሳ ከተማ ላይ የተጫዋች ተገቢነት ክስ አቀረበ 

አዲስ አበባ ከተማ ትላንት በአበበ በቂላ ስታድየም ከሀዋሳ ከተማ ጋር በተደረገው ጨዋታ ላይ በተሰለፈው መሀመድ ሲይላ ተገቢነት ላይ ያለውን ክስ ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አቅርቧል፡፡

ሀዋሳ ከተማ በውድድር ዘመኑ አጋማሽ ከአል አህሊ ሸንዲ ያስፈረመው መሀመድ ሲይላ የመኖርያ ፍቃድ እና የስራ ፈቃድ ሳይጠናቀቅ በጨዋታው ላይ መሰለፍ አይገባውም በሚል ነው አዲስ አበባ ከተማ ክሱን ያቀረበው፡፡

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በበኩሉ ክሱነ ተቀብሎ ጉዳዩን በመመልከት በነገው እለት ውሳኔውን እንደሚያሳውቅ አስታውቋል፡፡

Leave a Reply