ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ደደቢት | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

FT   ቅዱስ ጊዮርጊስ   3-2   ደደቢት  

15′ 50′ ሳላዲን ሰይድ 31′ ምንተስኖት አዳነ | 71′ ጌታነህ ከበደ 72′ አበባውቡጣቆ (OG)


ጨዋታው ተጠናቀቀ ! 

90+1 ደደቢቶች በአጭር ቅብብል ወደተጋጣሚያቸው የግብ ክልል ለመድረስ በመቸገራቸው ከኋላ መስመር ረጅም ኳሶችን ወደ አጥቂዎቹ ለመላክ እየሞከሩ ይገኛሉ ።

90′ ጭማሪ ደቂቃ 5 !

89′ ቅዱስ ጊዮርጊሶች ከራሳቸው ግብ በረጃጅም ኳሶች በመጠቀም ለመውጣት እየሞከሩ ነው ።

87′ ደደቢቶች በሽመክት በቀኝ በሽመክት ጉግሳ በኩል አድልተው እያጠቁ ይገኛሉ ። የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋቾች ሙሉ ለሙሉ በራሳቸው ሜዳ ላይ ሆነው እየተከላከሉ ነው ።

85′ የተጨዋች ለውጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ

አንዳርጋቸው ይላቅ በፕሪንስ ሴቭሪን ተተክቷል

82′ ደደቢቶች የአቻነት ግብ ለማግኘት ወደፊት ገፍተው እየተጫወቱ ነው ። አብዛኛው የጨዋታ እንቅስቃሴ በቅዱስ ጊዮርጊስ ሜዳ ላይ ሆኗል ።

80′ የተጨዋች ለውጥ ደደቢት

አቤል እንዳለ ገብቶ ዳዊት ፍቃዱ ወጥቷል

76 ‘ ቀይ ካርድ ደደቢት ብርሀኑ ቦጋለ

ብርሀኑ ቦጋለ ያስር ሙገርዋን አላግባብ በመናገሩ በሁለተኛ ቢጫ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል ።

74′ የተጨዋች ቅያሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ

በሀይሉ አሰፋ በብሩኖ ኮኔ ተለውጦ ወጥቷል ።

72 ጎል !  ደደቢት አበባው ቡጣቆ (OG)

ከግራ መስመር ሰለሞን ሀብቴ ያሻገረውን ኳስ ሽመክት ሲሞክር በአበባው ቡጣቆ ተጨርፋ ለደደቢት ሁለተኛ ግብ ሆናለች ።

71 ጎል ! ደደቢት ጌታነህ ከበደ

በሳጥኑ ጠርዝ ላይ አስቻለው በጌታነህ ላይ በሰራው ጥፋት የተሰጠውን ቅጣት ምት ራሱ ጌታነህ በቀጥታ አስቆጥሮታል ።

65′ የተጨዋች ቅያሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ

ያስር ሙገርዋ አዳነ ግርማን ተክቶ ወደሜዳ ገብቷል ።

65 ‘ ቢጫ ካርድ ቅዱስ ጊዮርጊስ

ፍሬዘር ካሳ ኤፍሬም አሻሞ ላይ ጥፋት በመስራቱ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል 

64 ‘ ጌታነህ ከነደ ከረጅም ርቀት ከዳዊት የተቀበለውን ኳስ ሞክሩ በግብ ቋሚ ለጥቂት ወጥቶበታል ።

62′ ቢጫ ካርድ ቅዱስ ጊዮርጊስ !

አበባው ቡጣቆ በግራ መስመር በሽመክት ጉግሳ ላይ በሰራው ጥፋት የቢጫ ካርድ ተመክቷል ።

57′ ሰለሞን  ከቀኝ መስመር ያሻማውን የማዕዘን ምት አክሊሉ በግንባሩ በመግጨት ቢሞክርም ኳስ በጎን ወጥታለች ። ደደቢት እስካሁን ከፈጠራቸው ይግብ ዕድሎች የተሻለ አጋጣሚ ነበር ።

53 ‘ ቢጫ ካርዶች ደደቢት !

የደደቢት ተጨዋቾች የተረበሹ ይመስላሉ ። ጌታነህ ከበደ በሀይሉን በክርን በመማታቱ ፣ ሽመክት ጉግሳ አስቻለው ላይ በሰረው ጥፋት እንዲሁም ብርሀኑ ቦጋለ ከዳኛ ጋር በመከራከሩ የቢጫ ካርድ ተመልክተዋል 

50 ጎል ቅዱስ ጊዮርጊስ ሳላዲን ሰይድ

ከግራ መስመር በሀይሉ ያሻማው ቅጣት ምት ክሌመንት በአግባቡ ማውጣት ተስኖት ሳላዲን ባርጌቾ በግንባሩ ሞክሯ ኳሷ የግቡን አግዳሚ ገጭታ ስትመለስ ሳላዲን ሰይድ አግኝቶ ለራሱ ሁለተኛ ለቡድኑ ሶስተኛ ጎል አድርጎታል ።

47′ ከሉውጡ በኋላ ደደቢት ከሶስቱ ተከላካዮች አንዱ የነበረውን ኩዌኩን በስዩም ቦታ ላይ በመቀየር የኋላመስመር ተሰላፊዎቹን ወደ አራት ከፍ አድርጓል ። የቡድኑ ቅርፅ አሁን ላይ ወደ 4 4 2 ቅርፅ የመጣ ይመስላል ። 

46′ የተጨዋች ቅያሪ ደደቢት 

ኤፍሬም አሻሞ ገብቶ ስዩም ተስፋዬ ወጥቷል ።

46′ ሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ በጌታነህ ከበደ አማካይነት ተጀምሯል ።

የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቀቀ ! 

45′ ጭማሪ ደቂቃ 1 !

42′ ደደቢቶች ለፊት መስመር ተሰላፊዎቻቸው የመጨረሻ ኳስ ማድረስ ተስኗቸዋል ። በተጋጣሚያቸው ሜዳ ላይ የሚነጠቋቸው ኳሶችም ለመልሶ መጠቃት እያጋለጣቸው ነው ። 

39′ ፕሪንስ በግራ መስመር ያሻገረለትን ኳስ ሳላዲን በቀጥታ ሞክሮ በግቡ አናት ወጥቶበታል ።

33′ ደደቢቶች ብርሀኑ ቦጋለን ወደመሀል በማስገባት ኤሪክ በነበረበት ቦታ ላይ ከሳምሶን ጥላሁን ጎን እንዲሆን በማድረግ ሰለሞን ሀብቴን የግራ መስመር ተመላላሽነት ቦታ ሰጥተውታል ።

32′ የተጨዋች ለውጥ ደደቢት 

ኤሪክ ኦፖኩ በሰለሞን ሀብቴ ተተክቷል ።


31 ‘ ጎል ቅዱስ ጊዮርጊስ ምንተስኖት አዳነ

በሀይሉ አሰፋ ከቀኝ መስመር ያሻማውን ኳስ ምንተስኖት በግንባሩ አስቆጥሯል ። እንደመጀመሪያው ጎል ሁሉ አሁንም ግብ አግቢው ያለምንም ጫና ብቻውን ነበር ።

29′ የደደቢት የመስመር ተመላላሾች በተሻለ ወደፊት ገፍተው ለመጨጫወት እየሞከሩ ነው ። ያም ሆኖ ቡድኑ እስካሁን ጠንካራ ሙከራ ማድረግ አልቻለም ።

26′ ቢጫ ካርድ

አስቻለው ታመነ በጌታነህ ላይ ከሜዳው አጋማሽ የተወሰኑ ሜትሮች ጠጋ ብሎ በሰራው ጥፋት የጨዋታውን የመጀመሪያ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል ።

20′ ደደቢቶች የሚሰነዝሩት ጥቃት በ ጊዮርጊስ ሜዳ ላይ በቂ ተጨዋቾችን ያሳተፈ ባለመሆኑ በቀላሉ እየተቋረጠ ይገኛል ።

18′ በሜዳው ቁመት በጊዮርጊስ ግብ ትይዩ በግምት ከ 20 ሜትር ጌታነህ የመታውን ቅጣት ምት የጊዮርጊስ ተከላካዮች ተደርበው አውጥተውታል ። በማዕዘን ምት ጨዋታው ቀጥሏል ።

15 ‘ ጎል ቅዱስ ጊዮርጊስ ሳልሀዲን ሰይድ 

ፕሪንስ ከግራ መስመር ያሻገረለትን ኳስ በነፃ አቋቋም ላይ የነበረው ሳላዲን በቀጥታ በመምታት ግብ አድርጎታል ።

10′ ደደቢት በመጀመሪያው ዙር ተደርጎ እንደነበረው ጨዋታ ሁሉ ዛሬም የመሀል ሜዳ የበላይነት ተወስዶበታል ።

8′ በጨዋታው ቅዱስ ጊዮርጊሶች የበላይነቱን ወስደዋል ። በተደጋጋሚ ወደጎል እየደረሱ ከጨዋታ ውጪ እየሆኑ ነው ።

4′ አዳነ ግርማ ከሳጥን ውጪ አክርሮ የሞከረውን ኳስ ዐይናለም ተደርቦ ሲያወጣበት ፕሪንስ አግኝቶ በድጋሜ ቢሞክርም ወደላይ ወጥቶበታል ።

3′ ጌታነህ ከበደ በግምት ከ 25 ሜትር የተገኘውን ቅጣት ምት ሞክሮ ወደላይ ተነስቶበታል ።

1′ ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊሱ ሳላዲን ሰይድ አማካይነት ተጀመረ ።

10 ፡ 02 ተጨዋቾች እና ዳኞች ወደሜዳ ገብተዋል ከደቂቃዎች በኋላ ጨዋታው ይጀምራል ።

የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ

30 ሮበርት ኦዶንካራ

2 ፍሬዘር ካሳ – 13 ሳላዲን በርጊቾ – 15 አስቻለው ታመነ – 4 አበባው ቡታቆ

19 አዳነ ግርማ – 21 ተስፋዬ አለባቸው – 23 ምንተስኖት አዳነ

11 ፕሪንስ ሰቭሬን – 7 ሳላዲን ሰይድ – 16 በሃይሉ አሰፋ

ተጠባባቂዎች

1 ፍሬው ጌታሁን

12 ደጉ ደበበ

25 አንዳርጋቸው ይላቅ

3 መሀሪ መና

18 አቡበከር ሳኒ

24 ያስር ሙገርዋ

17 ብሩኖ ኮኔ

የደደቢት አሰላለፍ

33 ክሌመንት አዞንቶ

 5 ኩዌኩ አንዶህ – 14 አክሊሉ አየነው – 6 አይናለም ኃይለ

7 ስዩም ተስፋዬ – 8 ሳምሶን ጥላሁን – 29  ኤሪክ ኦፖኩ – 10 ብርሃኑ ቦጋለ

 19 ሽመክት ጉግሳ

9 ጌታነህ ከበደ – 17 ዳዊት ፍቃዱ

ተጠባባቂዎች

22 ታሪክ ጌትነት

16 ሰለሞን ሐብቴ

27 እያሱ ተስፋዬ

15 ደስታ ደሙ

18 አቤል እንዳለ

21 ኤፍሬም አሻሞ

12 ሮበን ኦባማ

09፡54 አሁን የሁለቱ ቡድኖች ተጨዋቾች ወደመልበሻ ክፍል ገብተዋል ። በመቀጠል አሰላለፋቸውን ይዘን እንመለሳለን ።

09፡30 ተጨዋቾች እና ዳኞች ወደሜዳ ገብተው ማሟሟቅ ጀምረዋል ።

ዳኛ

የእለቱን ጨዋታ ኢንተርናሽናል አልቢትር በአምላክ ተሳማ የሚመራው ይሆናል ።

ያለፉት 3 ጨዋታዎች ውጤት

ቅዱስ ጊዮርጊስ   | አቻ | አሸነፈ | አሸንፈ

ደደቢት  | ተሸነፈ | አሸነፈ | አቻ

ግንኙነት

ደደቢት በ 2002 ዓ.ም ወደሊጉ ከመጣ ጅምሮ ሁለቱ ቡድኖች 15 ጊዜ ተገናኝተዋል ። ከእነዚህ ጨዋታዎች ውስጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ 10 ጊዜ ማሸነፍ ሲችል 25 ግቦችንም አስቆጥሯል ። ደደቢት በበኩሉ 15 ግቦችን አስቆጥሮ ሶስት ጨዋታዎችን በድል አጠናቋል ። የተቀሩት ሁለት ጨዋታዎች ደግሞ በአቻ ውጤት የተጠናቀቁ ነበሩ ። በዘንድሮው የውድድር አመት ሁለተኛው ሳምንት ላይ ባደረጉት ጨዋታም ቅዱስ ጊዮርጊስ 2 ለ 0 አሸንፎ ነበር ።

ደረጃ

ቅዱስ ጊዮርጊስ 32 ነጥቦችን በመሰብሰብ ሊጉን እየመራ ሲሆን ደደቢት በ4 ነጥቦች ዝቅ ብሎ በ 28 ነጥቦች በሁለተኛነት እየተከተለው ይገኛል ። 

ጤና ይስጥልኝ ክቡራት እና ክቡራን !

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 17ተኛ ሳምንት በሰንጠረዡ አናት ላይ የሚገኙት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ደደቢት የሚፋለሙ ይሆናል ። ዛሬ የካቲት 25 2009 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታድየም ከቀኑ 10 ሰዐት ላይ የሚጀምረውን የዚህን አጓጊ ጨዋታ ዋና ዋና እንቅስቃሴዎች በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ወደ እናንተ እናደርሳለን !

መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር !


Leave a Reply