የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 15ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜ እና እሁድ ተደርገው በየምድቦቹ አናት ላይ የሚገኙት ክለቦች ወሳኝ ነጥበች ጥለው ወጥተዋል፡፡
ምድብ ሀ
በዚህ ምድብ መሪዎቹ ክለቦች ነጥብ መጣላቸውን ተከትሎ ተከታዮቻቸው ልዩነታቸውን ለማጥበብ ምቱ አጋጣሚ ቢያገኙም ሳይጠቀሙበት ቀርዋል፡፡
ቅዳሜ በ08:00 አ.አ ፓሊስ እና ኢትዮጵያ መድን ያደረጉት ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል። ቀዳሚውን ጎል ያስቆጠረው አ.አ ፓሊስ ሲሆን ኤልያስ መንግስቱ በግሩም ሁኔታ የተጋጣሚውን ተከላካዮች አልፎ የሰጠውን ኳስ ይርጋለም ማሞ ወደ ጎልነት ለወጦታል፡፡ በሻምበል መላኩ አብርሃ የሚመሩት መድኖች የአቻኘት ግብ ለማግኘት የመጨረሻው የጨዋታው ደቂቃ ድረስ ለመጠበቅ ተገደዋል፡፡ ብሩክ ጌታቸው አክርሮ የመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው ጨርፎት ከአግዳሚው ጋር ተጋጭቶ ወደ መሬት ሲነጥር የአአ ፖሊስ ተጫዋች ቢያወጣትም የግቧን መስመር አልፋ ነበር በሚል የመድን የአቻነት ጎል ሆና ተመዝግባለች፡፡ ከግቧ እና ከጨዋታው ፍፃሜ በኋላ አአ ፖሊሶች የግቡ መፅደቅ አግባብ አይደለም በሚል ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡
በቀጣይ አራዳ ክፍለ ከተማ እና ኢትዮ. ውሃ ስፖርትን ያገናኘው የ10:00 ጨዋታ በአራዳ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቆል። ጨዋታው በተጀመረ ገና 57 ሰኮንድ እንዳስቆጠረ አራዳን መሪ ያደረገችዉን ጎል በእስራኤል ፍቅሩ ያገኘ ሲሆን በ18ኛው ደቂቃ አብዱልለጢፍ የአራዳን መሪነት ወደ ሁለት ከፍ አድርጓል፡፡ በማራኪ የኳስ ፍሰት የሚታወቁት ውሃ ስፖርቶች ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረት ቢያደርጉም ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡ በ52ኛው ደቂቃ ቀፀላ ፍቅረማርያም ላይ በተሰራው ጥፋት የተገኘውን ፍፁም ቅጣት ምት ክብረአብ ማቱሳላ ወደ ጎልነት ቀይሮታል፡፡
እሁድ አዲግራት ላይ በትግራይ ደርቢ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና መቀለ ከተማ ተገናኝተው ጨዋታቸውን ያለ ግብ በአቻ ውጤት ፈፅመዋል፡፡ የአቻ ውጤቱ ሁለቱም በደረጃ ሰንጠረዡ አናት እንደመገኘታቸው መልካም የሚባል ባይሆንም የተከታዮቻቸው ነጥብ መጣል ልዩነታቸውን ማስጠበቅ እንዲችሉ አድርጓቸዋል፡፡
ለገጣፎ ላይ በ10፡00 ባህርዳርን ያስተናገደው ለገጣፎ ለገዳዲ 2-1 አሸንፏል፡፡ የሁለቱ ጨዋታ ከወጣለት መርሀ ግብር ለአንድ ሰዓት ዘግይቶ የተጀመረ ሲሆን ይህም የባህርዳር ከተማ መሪዎችና ደጋፊዎችን ቅር አሰኝቷል። በደማቅ የደጋፊ ድጋፍ የተጀመረው ጨዋታ ብዙ ትእይንቶች የታዩበትም ጭምር ነበር፡፡ በመጀመሪያው 20 ደቂቃ ተጭነው ሲጫወቱ የነበሩት ባህርዳሮች መሪ የምታደርጋቸውን ጎል በኪዳኔ ተስፋዬ አማካይነት አግኝተዋል፡፡ ነገር ግን በያሬድ ቶሌራ የሚመሩት ለገጣፎዎች በመመራታቸው ጫና ውስጥ ሳይገቡ በ32ኛው ደቂቃ በልደቱ ለማ አማካኝነት አቻ ሆነዋል፡፡ ከ4 ደቂቃዎች በኋላ ደግሞ ሳዲቅ ተማም በግሩም ሁኔታ የተሻገረለትን ኳስ ወደ ግብነት ቀይሮት ለገጣፎን ወደ ድለ ልመርቶታል፡፡
ለገጣፎዎች በጨዋታው ለረጅም ደቂቃዎች ተጎድቶ ሜዳ ላይ ህክምና ላይ የነበረውን የባህርዳር ግብ ጠባቂ ለመርዳት ያደረጉት ርብርብ ይሁን የሚስብል ነበር፡፡ በተለይም አስልጣኝ ያሬድ ቶሌራ እና ወጌሻው ፍቃዱ ገብሩ ሲያደርጉት የነበሩት እገዛ በሁሉም ዘንድ መለመድ የሚገባው ተግባር ነው፡፡
በደጋፊ ታጅበው የመጡት ባህርዳር ከተማዎች ውጤቱን ተከትሎ በራሳቸው ተጫዋቾች እና በዳኞች ላይ ስሜታዊነት የሚታይበት ተቃውሞውቸውን ሲገልፁ ተስተውሏል፡፡ ይህን መሳይ ድርጊት የክለቡ የበላይ አመራሮች በአትኩሮት ቢመለከቱት ጥሩ ነው።
ሽረ ላይ ሽረ እንዳስላሴ ወሎን ኮምቦልቻን አስተናግዶ 1-0 አሸንፏል። በዚህ ጨዎታ ላይ ፍፁም ደስተኛ ያልነበሩት የወሎ ኮምበልቻ አመራሮች ቅሬታቸውን ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል። “ለዕረፍት በምንወጣበት ጌዜ የሽረ እንድስላሴ ምክትል አሰልጣኝ እና የእኛ ግብ ጠባቂ ሀይለ ቃል ተለወጠው ነበር፡፡ ነገር ግን ነገሩ ወዲያውኑ ረግቦ እኛም የራሳችንን ልጅ መክረን ከዕረፍት ስንመልስ ዳኛው ጨዎታውን ከማስጀመሩ በፊት የሽረ ምክትል አሰልጣኝ እና የእኛን ግብ ጠባቂ በቀይ ካርድ አሰናብቷል” ሲሉ የዳኝነት ውሳኔው እንዳላስደሰታቸው ገልጸዋል።
በሌሎች ጨዋታዎች አክሱም ከተማ ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃንን አስተናግዶ 2-1 ፣ ሰበታ ላይ ሰበታ ከተማ ቡራዩን 1-0 አሸንፈዋል፡፡ የሱሉልታ ከተማ እና ቡራዩ ከተማ ጨዋታ ደግሞ ያለ ግብ ተጠናቋል፡፡
[league_table 18186]
ምድብ ለ
እንደ ምድብ ሀ ሁሉ በዚህም ምድብ በተደረጉ ጨዋታዎች መሪዎቹ ቡድኖች ነጥብ የጣሉባቸው ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡
ሀላባ ከተማ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የነበረው ሀድያ ሆሳዕናን አስተናግዶ 1-0 በማሸነፍ ደረጃውን ማሻሻል ችሏል፡፡ አቦነህ ገነቱ በ68ኛው ደቂቃ የሀላባን የማሸነፊያ ጎል አስቆጥሯል፡፡
ወልቂጤ ከተማ መሪው ጅማን ከተማን አስተናገዶ 1-0 አሸንፏል፡፡ ለወልቂጤ ከተማ የማሸነፊያውን ጎል ብሩክ በየነ በ9ኝው ደቂቃ አስቆጥሯል።
በሌሎች ጨዎታ ሻሸመኔ ከተማ ጅንካ ከተማን 1-0 ሲያሸንፍ መጨረሻ ደረጃ ላይ የነበረው ነቀምት ከተማ 3ኛ ላይ የነበረው ደቡብ ፖሊስን 1-0 ማሸነፍ ችሏል፡፡ ቦንጋ ላይ ፌዴራል ፖሊስን ያስተናገደው ካፋ ቡና 2-1 ተሸንፏል፡፡ በ15ኛው ሳምንት በሜዳው ሽንፈት ያስተናገደ ብቸኛው ቡድንም ሆኗል፡፡ አርቢ ነገሌ ከ ነገሌ ቦረና ያለ ግብ አቻ የተለያዩበት ጨዋታም በሳምንቱ የተደረገ ሌላ ጨዋታ ነበር፡፡
በድሬዳዋ ደርቢ ናሽናል ሴሜንት ከ ድሬዳዋ ፖሊስ እንዲሁም ዲላ ከተማ ከ ስልጤ ወራቤ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ወደ ነገ ተሸጋግረዋል፡፡ ሀሙስ እለት ዲላ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን በተስተካካይ ጨዋታ ገጥሞ 1-0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው፡፡ በዚህ ተስተካካይ ጨዋታ ምክንያትም ሁለቱ ጨዋታዎች ወደ ነገ እንዲገፉ ምክንያት ሆኗል፡፡
[league_table 18205]