የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ጥሎ ማለፍ ውድድር ድልድል ይፋ ሆኗል

የ2009 የኢትዮዽያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ክለቦች የጥሎ ማለፍ ውድድር ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡

ዛሬ በኢትዮዽያ ሆቴል በተካሄደው የ2009 ከ20 ዓመት በታች የፕሪሚየር ሊግ የ1ኛ ዙር ውድድር አፈፃፀም ሪፖርት ላይ በወጣው ድልድል መሰረት ሁሉም ክለቦች ተሳታፊ የሚሆኑ ሲሆን በወጣው ዕጣ መሰረት ኢትዮዽያ ቡና ፣ ደደቢት ፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ እና መከላከያ በቀጥታ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅሏል፡፡

የመጀመርያውን የማጣሪያ ጨዋታ እንዲያከናውኑ የተደለደሉት 8 ቡድኖች ሲሆኑ የወጣው እጣ የሚከተለውን ይመስላል፡-

መጋቢት 3 ቀን 2009

ድሬደዋ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ

አዳማ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ

ኢትዮዽያ ንግድ ባንክ ከ ኢትዮጵያ መድን

በአንደኛው ዙር የሚያልፉት ክለቦች በቀጥታ ካለፉት ጋር በሩብ ፍፃሜው የሚፋለሙ ሲሆን

የድሬዳዋ ከተማ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ አሸናፊ ከ ኢትዮዽያ ቡና ፤ የሀዋሳ ከተማ እና የኤሌክትሪክ አሸናፊ ከደደቢት ፤ የአዳማ ከተማ እና የወላይታ ድቻ አሸናፊ ከወጣቶች አካዳሚ ፤ የንግድ ባንክ እና የመድን አሸናፊ ከመከላከያ የሚጫወቱ ይሆናል፡፡

የሩብ ፍፃሜ ጨዋታው ቀንና ቦታ ወደ ፊት የሚገለፅ ይሆናል፡፡

Leave a Reply