የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 12ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬም መደረጋቸውን ቀጥለው አርባምንጭ ከተማ ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋ ከተማ ድል አስመዝግበዋል፡፡
08:00 አበበ ቢቂላ ላይ አርባምንጭ ከተማን ያስተናገደው ቅድስት ማርያም 3-1 ተሸንፏል፡፡ ጨዋታው የአርባምንጭ ፍፁም የጨዋታ ብልጫ በታየበት ሲሆን 1-0 ከመመራት አንሰራርቶ ድል መጨበጥ ችሏል፡፡
ቅድስት ማርያሞች በመዲና አወል ጎል አማካኝነት ቀዳሚ ሆነው የመጀመርያው አጋማሽ ሲጠናቀቅ ከእረፍት መልስ አርባምንጮች የእንቅስቃሴ የበላይነቱን በመውሰድ በዕለቱ ድንቅ ብቃቷን በማሳየት ለቡድኗ አሸንፎ መውጣት ከፍተኛ ሚና ስትወጣ በነበረው ትዝታ ፈጠነ ሁለት እና በልደት ቶሎአ ጎሎች 3-1 ማሸነፍ ችለዋል፡፡
ቀጥሎ በተካሄደው ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጌዲዮ ዲላን 4-1 በሆነ ውጤት አሸንፎ መሪነቱን አጠናክሯል፡፡ በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የመጀመርያ አመት ተሳትፏቸው አስገራሚ እንቅስቃሴ እያደረጉ ያሉት ጌዲዮ ዲላዎች በቤተል ጢባ ጎል በማስቆጠር ቀዳሚ ቢሆኑም ንግድ ባንኮች በፍጥነት ወደ ጨዋታው በመመለስ በረሂማ ዘርጋው ሁለት ፣ በብዙሃን እንዳለ እና ህይወት ደንጊሶ አማካኝነት በተቆጠሩ ግቦች 4-1 ማሰነፍ ችለዋል፡፡ በጨዋታው ረሂማ ዘርጋው ከረጅም ጊዜያት በኋላ ወደ ግብ አስቆጣሪነት ስትመለስ ህይወት ደንጊሶ ከተከላካይ አማካይ ስፍራ በመነሳት ዘንድሮ ያስቆጠረችውን የጎል መጠን ወደ 4 ከፍ ማድረግ ችላለች፡፡
በአዲስ አበባ ስታድየም 09:00 ላይ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማን የገጠመው ድሬዳዋ ከተማ በቀላሉ 6-1 በማሸነፍ ደረጃውንና ወደ ሶስተኛ ከፍ ማድረግ ችለዋል፡፡ ለድሬዳዋ ይታገሱ ተገኝወርቅ እና ማህደር ጀማነህ ሁለት ሁለት ሲያስቆጥሩ ትደግ ፍስሃ እና እድላዊት ተመስገን ቀሪዎቹን ጎሎች አስቆጥረዋል፡፡ ለንፋስ ስልክ ደግሞ በግሏ ጥሩ የተንቀሳቀሰችው እየሩሳሌም ብርሃኑ አስቆጥራለች፡፡
ድሬዳዋ ከተማዎች በሁሉም ረገድ የተሻሉ በነበሩበት ጨዋታ በተለይም በማጥቃት እንቅስቃሴ ላይ የሚሳተፉት ተጫዋቾች በአንድ ሁለት ቅብብል ወደ ሳጥን የሚገቡበት መንገድ ለተመልካች አዝናኝ ነበር፡፡
11:30 ላይ የተካሄደው የአዲስ አበባ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ጨዋታ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡ ሲዳማ ቡና በምህረት ታፈሰ ጎል ቀዳሚ ሆኖ ወደ መልበሻ ክፍል ሲያመሩ ሁለተኛው አጋማሽ እንደተጀመረ በመጀመርያው የማጥቃት እንቅስቃሴ ተራማጅ ተስፋዬ አዲስ አበባ ከተማን አቻ ያደረገ ጎል አስቆጥራለች፡፡ ሲዳማን ለቃ አአ ከተማን ዘንድሮ የተቀላቀለችው ተራማጅ በቀድሞ ክለቧ ላይ በሁለቱም ዙር ጨዋታዎች ግብ ማስቆጠር ችላለች፡፡
ከአቻነት ጎሉ በኋላ ተመልካችን ቁጭ ብድግ ያደረገ እንቅስቃሴ የታየበት ሲሆን ሲዳማ ቡና በተደጋጋሚ የግብ አጋጣሚዎችን መፍጠር ችለው ነበር፡፡ በአጠቃላይ በርካታ ለሊጉ አዲስ የሆኑ ተጫዋቾችን የሰበሰበው የፍሬው ኃይለገብርኤል ሲዳማ ቡና በስፍራው የተገኘውን ተመልካች አድናቆት ያገኘ እንቅስቃሴ አድርጓል፡፡
ምድብ ሀ
[table id=231 /]
[league_table 18073]
ምድብ ለ
[table id=239 /]
[league_table 18083]
ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች