በሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሀዋሳ ከተማ እና መከላከያ አሸንፈዋል

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን መርሃግብር ዛሬ በአዲስአበባ ስታድየም ቀጥሎ ሲውል ሀዋሳ ከተማ  መከላከያ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡

በቅድሚያ 9፡00 ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ መካከል የተደረገው ጨዋታ በሀዋሳ ከተማ 3-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ በአቃቂ ቃሊቲ የሜዳ አጋማሽ አመዝኖ በተካሄደው የመጀመሪያው አጋማሽ ሀዋሳ ከተማዎች በ13ኛው ደቂቃ አይናለም አሳምነው እንዲሁም በ39ኛው ደቂቃ ተከላካይዋ ቅድስት ዘለቀ ባስቆጠረችው ግሩም የግንባር ኳስ የመጀመሪያውን አጋማሽ በ2-0 መሪነት ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡

በሁለተኛው አጋማሽ ሁለቱ ቡድኖች ከመጀመሪያው በተሻለ ተመጣጣኝ ፉክክር ማድረግ የቻሉ ሲሆን በዚሁ አጋማሽ ተቀይራ ወደ ሜዳ የገባችው ቅድስት ቄይ የቡድኗን የማሳረጊያ ግብ አስቆጥሯ ጨዋታው በሀዋሳ ከተማ የ3-0 የበላይነት ተጠናቋል፡፡

[table “231” not found /]

የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ – ምድብ ሀ

በሁለተኛው የእለቱ መርሃግብር 11:30 ላይ መከላከያ ኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚን ገጥሞ 2-1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ሙሉ ለሙሉ በሚያስችል መልኩ በጨዋታው መከላከያዎች ተሽለው በታዩበት በዚሁ ጨዋታ በተለይም በመጀመሪያው አጋማሽ መከላከያዎች የፈጠሯቸውን እጅግ በርካታ ግብ የማግባት አጋጣሚዎች ሳይጠቀሙባቸው ቀርተዋል፡፡ በአንጻሩ የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፓርት አካዳሚ ተጫዋቾች በተለይም ግብጠባቂዋ ከንባቴ ከተሌ እንዲሁም ተከላካይዋ ሁድራ ጀማል ጥሩ መንቀሳቀስ ችለዋል፡፡

በዚሁ ጨዋታ የግብ ማግባቱን ቅድሚያ ወስደው የነበሩት አካዳሚዎች ነበሩ፡፡ አማካይዋ ነፃነት ሰዋገኝ ከረጅም ርቀት አክርራ የመታችው ኳስ የመከላከያዋ ግብ ጠባቂ ማርታ በቀለ ስህተት ታክሎበት አካዳሚን መሪ አድርጓል፡፡ ነገርግን መከላከያዎች በደቂቃዎች ልዩነት ወደ ጨዋታው የተመለሱበትን ግብ በመስመር በኩል ጥሩ ስትንቀሳቀስ የነበረችው የምስራች ላቀው ባስቆጠረችው ግሩም ግብ አማካኝነት  የመጀመርያውን አጋማሽ 1-1 ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡

በሁለተኛው አጋማሽ 64ኛው ደቂቃ ላይ ሄለን እሸቱን ቀይራ የገባችው ሄለን ሰይፉ ከማዕዘን የተሻማውን ጎል አስቆጥራ መከላከያ 2-1 ማሸነፍ ችሏል፡፡

[table “239” not found /]

የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ – ምድብ ለ

#ክለብተጫአሸአቻተሸአስተቆልዩነጥብ
11815124974246
21814044774042
31810262524132
4189452318531
5188642213930
6189272521429
71861111933-1419
91822141544-298
101821151354-417


Leave a Reply