ቅዱስ ጊዮርጊስ በቶታል ካፍ ቻምፒየንሰ ሊግ 1ኛ ዙር የመጀመርያ ጨዋታ ከኮንጎ ሪፐብሊኩ ኤሲ ሊዮፓርድስ ጋር በመጪው እሁድ ዶሊሴ ከተማ ላይ ያደርጋል፡፡
ፈረሰኞቹ ወደ ኮንጎ ነገ ከማምራታቸው በፊት ዛሬ የመጨረሻ ልምምድ የሰሩ ሲሆን ለጨዋታው የሚጓዙ 18 ተጫዋቾችም ታውቀዋል፡፡
በዚህ ስብስብ በሲሸልሱ ጉዞ ላይ የነበሩት ፍሬው ጌታሁን ፣ ብሩኖ ኮኔ እና አንዳርጋቸው ይላቅ ያልተካተቱ ሲሆን ዘሪሁን ታደለ ፣ ፍሬዘር ካሳ እና ያስር ሙገርዋ ተክተዋቸዋል፡፡
ወደ ዶሊሴ የሚያመራው ቡድን የሚከተለውን ይመስላል፡፡
ግብ ጠባቂዎች
ሮበርት ኦዶንካራ ፣ ዘሪሁን ታደለ
ተከላካዮች
ፍሬዘር ካሳ ፣ ደጉ ደበበ ፣ ሳላዲን ባርጌቾ ፣ አስቻለው ታመነ ፣ አበባው ቡታቆ ፣ መሃሪ መና
አማካዮች
ተስፋዬ አለባቸው ፣ ያስር ሙገርዋ ፣ ናትናኤል ዘለቀ ፣ ምንትስኖት አዳነ ፣ አብዱልከሪም ኒኪማ ፣ በሃይሉ አሰፋ፣ ፕሪንስ ሲቬርኒሆ
አጥቂዎች
አዳነ ግርማ፣ ሳላዲን ሰዒድ፣ አቡበከር ሳኒ
በዛሬው የልምምድ ፕሮግራም ላይ የክለቡ ደጋፊዎች የተገኙ ሲሆን የደጋፊ ተወካዮች የመልካም ምኞት እና የማነቃቂያ ንግግሮችን አድርገዋል፡፡ ኬክ በመቁረስ እና ሻምፓኝ በመክፈትም ቡድኑን ወደ ብራዛቪል ሸኝተዋል፡፡