ቻምፒየንስ ሊግ፡ ወደ ምድብ ለመግባት የሚደረጉ ፍልሚያዎች ዛሬ ይጀመራሉ

በ2017 የካፍ ቶታል ቻምፒየንስ ሊግ የአንደኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ እስከሳምንቱ መጨረሻ በሚደረጉ ጨዋታዎች ቀጥለው ይደረጋሉ፡፡

የአንደኛ ዙር አሸናፊዎች ወደ ምድብ ድልድል በቀጥታ መግባት በመቻላቸው በጨዋታዎቹ ከፍተኛ ፉክክር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በቅድመ ማጣሪያ ዙር በቀጥታ ወደ አንደኛ ዙር ያለፉት የአፍሪካ ሃያል ክለቦችም ውድድሮቻቸውን ማድረግ ስለሚጀምሩ ዙርን የከበደ ያደርገዋል፡፡ ተሸፊዎች ወደ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ የሚወርዱ ይሆናል፡፡

ዛሬ ፕሪቶሪያ ላይ የወቅቱ የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ አሸናፊ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ የዩጋንዳውን ቻምፒዮን ኬሲሲኤን ያስተናግዳል፡፡ ብራዚሎቹ የካፍ ሱፐር ካፕን ቲፒ ማዜምቤ በመርታት ያሸነፉ ሲሆን ዳግም ለሁለተኛ ግዜ የቻምፒየንስ ሊጉን ለማሸነፍ ጉዟቸውን ዛሬ ይጀምራሉ፡፡ ኬሲሲኤ በቅድመ ማጣሪያ ዙር የአንጎላውን ፕሪሜሮ ደ አውጉስቶን በመርታት ማለፍ መቻሉ ይታወሳል፡፡ ኬሲሲኤ የዩጋንዳ አዛም ፕሪምየር ሊግ መሪ መሆኑና የመጀመሪያውን ጨዋታ ከሜዳው ውጪ ማድረጉ በጨዋታው የተለየ ነገር እንደሚያሳይ ተጠብቋል፡፡

ዛሬ ወደ ብራዛቪል ያቀናው የኢትዮጵያው ተወካይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዶሊሲ ላይ ኤሲ ሊዮፓርድስን እሁድ የሚገጥም ይሆናል፡፡ ጨዋታው ለመጫወት አመቺ አይደለም ተብሎ በሚነገርለት የስታደ ዴኒስ ሳሶ ንጎሶ ይካሄዳል፡፡

 

ዓርብ

19፡00 – ማሜሎዲ ሰንዳውንስ (ደቡብ አፍሪካ) ከ ካምፓላ ሲቲ ካውንስ ኦቶሪቲ (ዩጋንዳ)

 

ቅዳሜ

16፡00 – ያንግ አፍሪካንስ (ታንዛኒያ) ከ ዛናኮ (ዛምቢያ)

18፡00 – ኤስፔራንስ ደ ቱኒዝ (ቱኒዚያ) ከ ሆሮያ (ጊኒ)

18፡30 – አል አሃሊ (ግብፅ) ከ ቤድቬስት ዊትስ (ደቡብ አፍሪካ)

19፡00 – ዋይዳድ አትሌቲክ ክለብ (ሞሮኮ) ከ ሞናና (ጋቦን)

20፡30 – ዩኤስኤም አልጀር (አልጄሪያ) ከ ሪያል ክለብ ዱ ካዲዮጎ (ቡርኪናፋሶ)

 

እሁድ

14፡30 – አል አሃሊ ትሪፖሊ (ሊቢያ) ከ ፋት ዩኒየን ስፖርት (ሞሮኮ)

15፡00 – ክለብ ፌሬቫያሮ ደ ቤይራ (ሞዛምቢክ) ከ ባራክ ያንግ ኮንትሮለር (ላይቤሪያ)

15፡30 – ኤሲ ሊዮፓርድስ ደ ዶሊሲ (ኮንጎ ሪፐብሊክ) ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ (ኢትዮጵያ)

15፡30 – ቲፒ ማዜምቤ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) ከ ካፕስ ዩናይትድ (ዚምባቡዌ)

15፡30 – ኮተን ስፖርት (ካሜሮን) ከ ሲኤንኤፒኤስ ስፖርት (ማዳጋስካር)

16፡00 – ሪቨርስ ዩናይትድ (ናይጄሪያ) ከ ኤል ሜሪክ (ሱዳን)

16፡00 – ጋምቢያ ፖርትስ ኦቶሪቲ (ጋምቢያ) ከ ኤኤስ ቪታ ክለብ (ዲ.ሪ. ኮንጎ)

18፡00 – ዛማሌክ (ግብፅ) ከ ኢንጉ ሬንጀርስ ኢንተርናሽናል (ናይጄሪያ)

18፡00 – ኤቷል ደ ሳህል (ቱኒዚያ) ከ ኤኤስ ደ ታንዳ (ኮትዲቯር)

20፡00 – አል ሂላል (ሱዳን) ከ ኤኤስ ፖር ሉዊ 2000 (ሞሪሺየስ)

1 Comment

Leave a Reply