የ2017 ካፍኮንፌድሬሽን ዋንጫ የአንደኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታዎች አርብ በተደረጉ ሶስት ግጥሚያዎች ጀምረዋል፡፡ ዜስኮ ዩናይትድ፣ ኤምሲ አልጀር እና ሰሞሃ በሜዳቸው አሸንፈው የወጡበትን ድል አስመዝግበዋል፡፡
የሰሜን ዛምቢያው ክለብ ዜስኮ ዩናይትድ የቡሩንዲውን ሜሴንጀር ንጎዚን 2-0 መርታት ችሏል፡፡ የንዶላው ክለብ የማሸነፊያ ግቦቹን ጃክሰን ሙዋንዛ እና ኮንዳዋኒ ምቶንጋ አስቆጥረዋል፡፡ ዜስኮ ድሉን ተከትሎ ወደ ሁለተኛ ዙር የማለፍ ተስፋውን አስፍቷል፡፡ በ2016 በቻምፒየንስ ሊግ ረጅም ርቀትን መጓዝ የቻለው ዜስኮ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾችን መያዙ ቡጁምቡራ ላይ በመልስ ጨዋታው እንዳይቸገር ያደርገዋል፡፡
የግብፁ ሰሞሃ ከፍፁም የጨዋታ የበላይነት ጋር ታግዞ የኬንያውን ኡሊንዚ ስታርስን 4-0 ረምርሟል፡፡ የኬንያው የጦር ክለብ መከላከልን መሰረት አድርጎ ለጨዋታው መቅረቡ ዋጋ አስከፍሎታል፡፡ በመጀመሪያው አጋማሽ በአህመድ ራውፍ እና ኢስላም ሞሃሬብ ሁለት ግቦች ሰሞሃ 2-0 መምራት ችሏል፡፡ በሁለተኛው አጋማሽ መሃሙድ አብዱልአዚዝ እና ሞሃሬብ ያስቆጠራቸው ግቦች 4-0 ጨዋታውን እንዲጠናቀቅ አስችለዋል፡፡ የኡሊንዚው ግብ ጠባቂ ሳሩኒ ጥረት እና የሰሞሃ የአጨራረስ ድክመት ሆነ እንጂ የግብ መጠኑ ከዚህም በላይ የመስፋት እድል ነበረው፡፡ ኡሉንዚ ከአንደኛው ዙር የመሰናበት ጋሬጣ ከፊት ተደቅኖበታል፡፡
የአልጄሪያው ኤምሲ አልጀር የዲ.ሪ. ኮንጎውን ሬኔሳንስ ዱ ኮንጎን 2-0 አሸንፏል፡፡ የኪንሻሳው ክለብ በመጀመሪያው አጋማሽ የተጠቀመው የመከላከል አጨዋወት በመጀመሪያው አጋማሽ በእጅጉ ጠቅሞታል፡፡ ባለሜዳዎቹ በመጀመሪያው አጋማሽ የሬኔሳንስን የተከላካይ ስፍራ ሰብረው ለመግባት ተቸግረው አምሽተዋል፡፡ የአዉጅ እና ቦሄና የሁለተኛ 45 ግቦች የአልጄሪ መዲና ክለብን አሸናፊ አድርገዋል፡፡
ጨዋታዎቹ ዛሬም ሲቀጥሉ በተለያዩ የአፍሪካ ከተሞች ሰባት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
አርብ ውጤቶች
ሰሞሃ (ግብፅ) 4-0 ኡሊንዚ ስታርስ (ኬንያ)
ዜስኮ ዩናይትድ (ዛምቢያ) 2-0 ለ ሜሰንጀር ደ ንጎዚ (ብሩንዲ)
ሞሊዲያ ክለብ ደ አልጀር (አልጄሪያ) 2-0 ሬኔሳንስ ዱ ኮንጎ (ዲ.ሪ. ኮንጎ)
ቅዳሜ
15፡00 – ክለብ ሬክሬቲቮ ዲስፖርቲቮ ዱ ሊቦሎ (አንጎላ) ከ ንጌዚ ፕላቲኒየም ስታርስ (ዚምባቡዌ)
15፡30 – ሳንጋ ባላንዴ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) ከ አል ሂላል ኦባያድ (ሱዳን)
15፡30 – ኤቷል ዱ ኮንጎ (ኮንጎ ሪፐብሊክ) ከ ዩኒየስ ስፖርቲቭ ደ ካቤሌ (አልጄሪያ)
16፡00 – ቫይፐርስ (ዩጋንዳ) ከ ፕላቲኒየም ስታርስ (ደቡብ አፍሪካ)
16፡30 – ኤኤስ ካሎም (ጊኒ) ከ ኢቲሃድ ታንገር (ሞሮኮ)
17፡00 – ኦንዜ ክሬቸርስ (ማሊ) ከ ራዮን ስፖርት (ሩዋንዳ)
18፡00 – ክለብ ስፖርቲፍ ሴፋክሲየን (ቱኒዚያ) ከ ዮንግ ስፖርትስ አካዳሚ (ካሜሮን)
እሁድ
16፡00 – ክለብ አፍሪኬን (ቱኒዚያ) ከ ሪፐብሊክ ኦፍ ሴራሊዮን አርምድ ፎርስስ (ሴራሊዮን)
16፡00 – አሴክ ሚሞሳስ (ኮትዲቯር) ከ አፔጄስ ደ ምፎ (ካሜሮን)
17፡00 – ጆሊባ ደ ባማኮ (ማሊ) ከ አለ መስሪ (ግብፅ)
19፡00 – መግረብ ደ ፈስ (ሞሮኮ) ከ ስፖርቲግ ክለብ ደ ጋግኖአ (ኮትዲቯር)
19፡15 – አዛም (ታንዛኒያ) ከ ምባባኔ ስዋሎስ (ስዋዚላንድ)
19፡30 – ኤል አሃሊ ሸንዲ (ሱዳን) ከ ስፑርስፖርት ዩናይትድ (ደቡብ አፍሪካ)