ቻምፒየንስ ሊግ፡ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ዋንጫ የማስጠበቅ ዘመቻውን በድል ጀምሯል

በካፍ 2017 ቻምፒየንስ ሊግ የአንደኛ ዙር ጨዋታዎች አርብ ምሽት ፕሪቶሪያ ላይ በተደረገ ጨዋታ ጀምሯል፡፡ የደቡብ አፍሪካው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ የዩጋንዳው ኬሲሲኤን በጠባብ ውጤት በማሸነፍ የአምና ድሉን የማስጠበቅ ዘመቻውን ጀምሯል፡፡

ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ኬሲሲሴን 2-1 በሆነ ውጤት የረታ ቢሆንም ኬሲሲኤ ከሜዳው ውጪ ያስቆጠረው ግብ ወሳኝ ሆናለች፡፡ በጨዋታው መጀመሪያ አከባቢ ብራዚሎቹ አከታትለው ያስቆጠሩት ሁለት ግቦች አጀማመራቸውን ቢያሳምርላቸውም በሂደት እየተቀዛቀዙ መምጣታቸው ተጨማሪ ግቦችን እንዳያገኙ አግዷቸዋል፡፡ ኮትዲቯራዊው ተከላካይ  ባንጋሊ ሶማሆሮ በግንባር በመግጨት ሰንዳውንስ መሪ ሲያደርግ ከደቂቃዎች በኃላ ብራዚሊያዊው የመስመር ተከላካይ ሪካርዶ ናሽሜንቶ በፍፁም ቅጣት ምት ልዩነቱን ወደ ሁለት አስፍቷል፡፡ ካስትሮ ተጨማሪ ግብ አስቆጥሮ የነበረ ቢሆንም ፐርሲ ታኦ ከጨዋታ ውጪ አቋቋም ላይ ተገኝቷል በሚል የመሃል ዳኛው ግቧን ሽረዋል፡፡

በሁለተኛው አጋማሽም ብራዚሎች የካምላው ክለብ ላይ ጫና ፈጥረው መጫወታቸውን ቀጥለዋል፡፡ ነገር ግን በ69ኛው ደቂቃ ጂኦፍሪ ሴሬንኩማ ወሳኝ የሆነች ግብ በሰንዳውንስ መረብ ላይ አስቆጥሮ በመልሱ ጨዋታ ተስፋ እንዲሰንቅ አስችሏል፡፡

የቻምፒየንስ ሊጉ ጨዋታዎች ዛሬም በተለያዩ የአፍሪካ ከተሞች ቀጥለው ይደረጋሉ፡፡ አምስት ጨዋታዎች ዛሬ ሲደረጉ የሰሜን አፍሪካ ሃያሎቹ አል አሃሊ፣ ዩኤስኤም አልጀር፣ ዋይዳድ ካዛብላንካ እና ኤስፔራንስ በሜዳቸው ይጫወታሉ፡፡ የታንዛኒያው ያንግ አፍሪካንስ የዛምቢያውን ቻምፒዮን ዛናኮን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ከፍተኛ ግምትን ማግኘት ችሏል፡፡

 

ዓርብ ውጤት

ማሜሎዲ ሰንዳውንስ (ደቡብ አፍሪካ) 2-1 ካምፓላ ሲቲ ካውንስል ኦቶሪቲ (ዩጋንዳ)

 

ቅዳሜ

16፡00 – ያንግ አፍሪካንስ (ታንዛኒያ) ከ ዛናኮ (ዛምቢያ)

18፡00 – ኤስፔራንስ ደ ቱኒዝ (ቱኒዚያ) ከ ሆሮያ (ጊኒ)

18፡30 – አል አሃሊ (ግብፅ) ከ ቤድቬስት ዊትስ (ደቡብ አፍሪካ)

19፡00 – ዋይዳድ አትሌቲክ ክለብ (ሞሮኮ) ከ ሞናና (ጋቦን)

20፡30 – ዩኤስኤም አልጀር (አልጄሪያ) ከ ሪያል ክለብ ዱ ካዲዮጎ (ቡርኪናፋሶ)

 

እሁድ

14፡30 – አል አሃሊ ትሪፖሊ (ሊቢያ) ከ ፋት ዩኒየን ስፖርት (ሞሮኮ)

15፡00 – ክለብ ፌሬቫያሮ ደ ቤይራ (ሞዛምቢክ) ከ ባራክ ያንግ ኮንትሮለር (ላይቤሪያ)

15፡30 – ኤሲ ሊዮፓርድስ ደ ዶሊሲ (ኮንጎ ሪፐብሊክ) ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ (ኢትዮጵያ)

15፡30 – ቲፒ ማዜምቤ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) ከ ካፕስ ዩናይትድ (ዚምባቡዌ)

15፡30 – ኮተን ስፖርት (ካሜሮን) ከ ሲኤንኤፒኤስ ስፖርት (ማዳጋስካር)

16፡00 – ሪቨርስ ዩናይትድ (ናይጄሪያ) ከ ኤል ሜሪክ (ሱዳን)

16፡00 – ጋምቢያ ፖርትስ ኦቶሪቲ (ጋምቢያ) ከ ኤኤስ ቪታ ክለብ (ዲ.ሪ. ኮንጎ)

18፡00 – ዛማሌክ (ግብፅ) ከ ኢንጉ ሬንጀርስ ኢንተርናሽናል (ናይጄሪያ)

18፡00 – ኤቷል ደ ሳህል (ቱኒዚያ) ከ ኤኤስ ደ ታንዳ (ኮትዲቯር)

20፡00 – አል ሂላል (ሱዳን) ከ ኤኤስ ፖር ሉዊ 2000 (ሞሪሺየስ)

Leave a Reply