ደደቢት ከ ወልድያ | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

FT   ደደቢት   1-0   ወልድያ  

50′ ጌታነህ ከበደ


ተጠናቀቀ!
ጨዋታው በደደቢት 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

90′ በድሩ ኑርሁሴን በግምባሩ የገጨውን ኳስ የግቡ አግዳሚ ገጭቶ ሲመለስ አንዱአለም ንጉሴ መትቶ ኩሊባሊ ከመስመር አውጥቶታል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 4

የተጫዋች ለውጥ – ደደቢት
85′ ጌታነህ ከበደ ወጥቶ የአብስራ ተስፋዬ ገብቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
85′ ጌታነህ ከበደ በእጁ ተጠቅሞ ጎል ለማስቆጠር በመሞከሩ ቢጫ ካርድ ተመልክቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ወልድያ
81′ ያሬድ ብርሃኑ ወጥቶ በድሩ ኑርሁሴን ገብቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
77′ ዮሃንስ ሃይሉ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ደደቢት
76′ ዳዊት ፍቃዱ ወጥቶ ሮበን ኦባማ ገብቷል፡፡

75′ ወልድያ ጫና ፈጥሮ እየተንቀሳቀሰ ይገኛሉ፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ወልድያ

61′ ኤሪክ ኮልማን እና ቢንያም ዳርሰማ ወጥተው ሙሉጌታ ረጋሳ እና ሙሉነህ ጌታሁን ገብተዋል፡

59′ ያሬድ ብርሀሃኑ የሞከረውን ኳስ ታሪክ ጌትነት እንደምንም አውጥቶበታል፡፡

54‘ ከግቡ ጥቂት ርቀት ያሬድ ብርሃኑ ግልፅ የማግባት አጋጣሚ አግኝቶ በግቡ አናት ወደ ውጪ ሰዶታል፡፡ የሚያስቆጭ አጋጣሚ !

52′ ጌታነህ ከበደ በድጋሚ ከርቀት የመታውን ኳስ ቤሊንጌ አውጥቶታል፡፡ ደደቢት በተደጋጋሚ ወደ ወልድያ የግብ ክልል እየደረሱ ነው፡፡

ጎልልል!!! ደደቢት

50′ ጌታነህ ከበደ ከሳጥኑ ጠርዝ የመታው ኳስ በግሩም ሁኔታ በወልድያ መረብ ላይ አርፏል፡፡

ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀመረ፡፡

እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ ያለግብ ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 2

37′ ያሬድ ብርሃኑ ከርቀት የሞከረው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወጥቷል፡፡

30′ ያሬድ ሀሰን ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ታሪክ ቀድሞ ይዞታል፡፡

28′ ሽመክት ጉግሳ ከመስመር ያሻገረውን ኳስ በጥሩ አቋቋም ላይ የነበረው ዳዊት ሞክሮ በግቡ አናት ወደ ውጪ ሰዶታል፡፡

20′ ዳዊት ፍቃዱ የሞከረው ኳስ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

20′ ጨዋታው ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ እየታየበት ነው፡፡

13′ ዳዊት በጥሩ ቅብብል የደረሰውን ኳስ ሞክሮ ቤሊንጌ በቀላሉ ይዞበታል፡፡

5′ ጌታነህ ከበደ የመታው ቅጣት ምት ቤሊንጌ ሲመልሰው ቋሚውን ገጭቶ ወጥቷል፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው በጌታነህ ከበደ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡


የደደቢት አሰላለፍ

22 ታሪክ ጌትነት

15 ደስታ ደሙ- 5 ኩዌኩ አንዶህ – 6 አይናለም ኃይለ – 16 ሰለሞን ሐብቴ

21 ኤፍሬም አሻሞ – 24 ካድር ኩሊባሊ -18 አቤል እንዳለ – 19 ሽመክት ጉግሳ

9 ጌታነህ ከበደ – 17 ዳዊት ፍቃዱ

ተጠባባቂዎች

30 ሶፎንያስ ሰይፉ

27 እያሱ ተስፋዬ

12 ሮበን ኦባማ

25 ብርሃኑ አሻሞ

2 ኄኖክ መርሻ

20 የአብስራ ተስፋዬ

29 ኤሪክ ኦፖኩ


የወልድያ አሰላለፍ

16 ኤሚክሪል ቢሌንጌ

3 ቢኒያም ዳርሰማ — 14 ያሬድ ዘውድነህ — 25 አዳሙ መሀመድ — 6 ዮሐንስ ኃይሉ

21 ሀብታሙ ሸዋለም – 28 ታዬ አስማረ – 9 ያሬድ ሀሰን – 29 ኤሪክ ኮልማን

24 ያሬድ ብርሃኑ – 2 አንዱአለም ንጉሴ

ተጠባባቂዎች

64 ዳዊት አሰፋ

4 ሙሉነህ ጌታሁን

10 ሙሉጌታ ረጋሳ

19 አለማየው ግርማ

23 ሙሉጌታ ወ/ጊዮርጊስ

15 ጫላ ድሪባ

11 በድሩ ኑርሁሴን

09፡54 አሁን የሁለቱ ቡድኖች ተጨዋቾች ወደመልበሻ ክፍል ገብተዋል ።

09፡30 ተጨዋቾች እና ዳኞች ወደሜዳ ገብተው ማሟሟቅ ጀምረዋል ።

ዳኛ

የእለቱን ጨዋታ ፌዴራል አርቢትር ደረጄ ገብሬ በዋና ዳኝነት የሚመራው ይሆናል ።

ያለፉት 3 ጨዋታዎች ውጤት


ደደቢት
 አሸነፈ | አቻ |ተሸነፈ

ወልድያ አሸነፈ | አቻ | አቻ

ግንኙነት

ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ ቀደም በፕሪምየር ሊጉ 3 ጊዜ ሲገናኙ ደደቢት ሁለቱን አሸንፎ በአንዱ አቻ ተለያይተዋል፡፡ ደደቢት 7 ሲያስቆጥር ወልድያ 1 አስቆጥሯል፡፡ 

ወልድያ በታሪኩ የመጀመርያ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ያደረገው በ2007 ከደደቢት ጋር እንደነበር የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ 6-1 በሆነ ሰፊ ውጤት ተሸንፎ ነበር፡፡ የአሁኑ የወልድያ አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታም የደደቢት አሰልጣኝ ነበሩ፡፡


ደረጃ

ደደቢት በ28 ነጥብ እና 8 የግብ ልዩነት 2ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ወልድያ በ21ነጥቦች እና ያለምንም ጎል ልዩነት 8ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡

ጤና ይስጥልኝ ክቡራት እና ክቡራን !

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 18ኛ ሳምንት ደደቢት ከ ወልድያ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀምራል። ዛሬ መጋቢት 2 ቀን 2009 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታድየም ከቀኑ 10:00 ላይ የሚጀምረውን የዚህን ጨዋታ ዋና ዋና እንቅስቃሴዎች በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ወደ እናንተ እናደርሳለን፡፡


መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *