ኮንፌድሬሽን ዋንጫ፡ ቫይፐርስ፣ ሴፋክሲየን እና ኦንዜ ክሬቸርስ ድል ቀንቷቸዋል

በካፍ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ቅዳሜ በተደረጉ የአንደኛ ዙር ጨዋታዎች በሜዳቸው የተጫወቱ አብዛኞቹ ክለቦች ድል ሲቀናቸው አንድ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡

በኮንፌድሬሽን ዋንጫ የምንግዜም ስኬታማው ክለብ የቱኒዚያው ሴፋክሲየን የካሜሮኑን ዮንግ ስፖርትስ አካዳሚን 5-0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፡፡ ዮንግ ስፖርትስ አካዳሚ የኢትዮጵያውን ተወካይ መከላከያን በድምር ውጤት 2-1 አሸንፎ ወደ አንኛው ዙር ያለፈ ቢሆንም በሴፋክሲየን የደረሰበት ከባድ ሽንፈት በሜዳው ለመቀልበስ ይቸግረዋል፡፡ መሃመድ ዋሊዩ ንዶዬ እና ካሪም አዎዲ ሁለት ሁለት ግቦች ሲያስቆጥሩ አላዲን ማርዞኪ ቀሪዋን አንድ ግብ አክሏል፡፡ የአዎዲ ግቦች በፍፁም ቅጣት ምት የተገኙ ነበሩ፡፡

የሴንት ሜሪ ስታዲየም የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደረገው የዩጋንዳው ቫይፐርስ የደቡብ አፍሪካውን ፕላቲኒየም ስታርስን 1-0 ማሸነፍ ችሏል፡፡ ሚልተን ካሪሳ ሁለተኛው አጋማሽ የመጀመሪያ ደቂቃዎች ላይ የቡድኖች ልዩነት የነበረችውን ብቸኛው ግብ አስቆጥሯል፡፡

ወደ አንጎላ ያቀናው የዚምባቡዌው ንግዚ ፕላቲኒየም ስፖርት በሬክሬቲቮ ሊቦሎ 2-1 ተሸንፏል፡፡ ፋብሪሲዮ የአንጎላውን ክለብ ቀዳሚ ሲያደርግ ቻኮሮማ እንግዶቹን በመጀመሪያው አጋማሽ አቻ አድርጓል፡፡ ብራዚላዊው ፋብሪሲዮ ዳግም ሁለተኛ ግብ አስቆጥሮ ሊቦሎን አሸናፊ አድርጓል፡፡ የንግዚ ተጨዋቾች በሁለተኛው አጋማሽ ያስቆጠሩት የአቻነት ግብ ባለመፅደቁ ከፍተኛ ቅራኔን አስነስቷል፡፡

የማሊው ኦንዜ ክሬቸርስ በሳማኪ ግብ ታግዞ  የሩዋንዳውን ራዮን ስፖርትን 1-0 አሸንፏል፡፡ በሜዳው የአልጄሪያውን ጄኤስ ካቤሌን ያስተናገደው የኮንጎ ሪፐብሊኩ ኤቷል ዱ ኮንጎ ያለግብ አቻ ተለያይቷል፡፡ ኢትዮጵያዊው የመሃል ዳኛ ሃይለየሱስ ባዘዘው በመረው ጨዋታ የዲ.ሪ. ኮንጎው ሳንጋ ባላንዴ የሱዳኑን አል ሂላል ኦባያድን 1-0 ረቷል፡፡ የጊኒው ካሎምም የሞሮኮውን ኢትሃድ ታንገር በተመሳሳይ 1-0 አሸንፏል፡፡

የአንደኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ በሚደረጉ ስደስት ጨዋታዎች ፍፃሚያቸውን ያገኛሉ፡፡

 

አርብ ውጤቶች

ሰሞሃ (ግብፅ) 4-0 ኡሊንዚ ስታርስ (ኬንያ)

ዜስኮ ዩናይትድ (ዛምቢያ) 2-0 ለ ሜሰንጀር ደ ንጎዚ (ብሩንዲ)

ሞሊዲያ ክለብ ደ አልጀር (አልጄሪያ) 2-0 ሬኔሳንስ ዱ ኮንጎ (ዲ.ሪ. ኮንጎ)

 

ቅዳሜ  ውጤቶች

ክለብ ሬክሬቲቮ ዲስፖርቲቮ ዱ ሊቦሎ (አንጎላ) 2-1 ንጌዚ ፕላቲኒየም ስታርስ (ዚምባቡዌ)

ሳንጋ ባላንዴ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) 1-0 አል ሂላል ኦባያድ (ሱዳን)

ኤቷል ዱ ኮንጎ (ኮንጎ ሪፐብሊክ) 0-0 ዩኒየስ ስፖርቲቭ ደ ካቤሌ (አልጄሪያ)

ቫይፐርስ (ዩጋንዳ) 1-0 ፕላቲኒየም ስታርስ (ደቡብ አፍሪካ)

ኤኤስ ካሎም (ጊኒ) 1-0 ኢቲሃድ ታንገር (ሞሮኮ)

ኦንዜ ክሬቸርስ  (ማሊ) 1-0 ራዮን ስፖርት (ሩዋንዳ)

ክለብ ስፖርቲፍ ሴፋክሲየን (ቱኒዚያ) 5-0 ዮንግ ስፖርትስ አካዳሚ (ካሜሮን)

 

እሁድ

16፡00 – ክለብ አፍሪኬን (ቱኒዚያ) ከ ሪፐብሊክ ኦፍ ሴራሊዮን አርምድ ፎርስስ (ሴራሊዮን)

16፡00 – አሴክ ሚሞሳስ (ኮትዲቯር) ከ አፔጄስ ደ ምፎ (ካሜሮን)

17፡00 – ጆሊባ ደ ባማኮ (ማሊ) ከ አለ መስሪ (ግብፅ)

19፡00 – መግረብ ደ ፈስ (ሞሮኮ) ከ ስፖርቲግ ክለብ ደ ጋግኖአ (ኮትዲቯር)

19፡15 – አዛም (ታንዛኒያ) ከ ምባባኔ ስዋሎስ (ስዋዚላንድ)

19፡30 – ኤል አሃሊ ሸንዲ (ሱዳን) ከ ሱፐርስፖርት ዩናይትድ (ደቡብ አፍሪካ)

Leave a Reply