የ2015 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ድልድል ዛሬ ይወጣል

በሞሮኮ አስተናጋጅነት ለማለፍ የሚደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የእጣ አወጣጥ ስነ-ስርአት ዛሬ በካፍ መቀመጫ ካይሮ ቀትር ላይ ይከናወናል፡፡ ካፍ ባሳወቀው የምድብ ፎርማት መሰረት 28 ሃገራት በ4 ቋት በመክፈል በ7 ምድቦች ውስጥ የሚካተቱ ሲሆን ከየምድባቸው 1ኛ እና 2ኛ ሆነው የሚያልፉ 14 ቡድኖች እንዲሁም በጥሩ 3ኛነት የሚያጠናቅቅ 1 ሃገር ከአስተናጋጇ ሞሮኮ ጋር በመሆን 16ቱ የ2015 አፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊዎች ይለያሉ፡፡

ኢትዮጵያ ለዘመናት በቅድመ ማጣርያ ውድድሮች ተሳትፋ ወደ ምድብ ማጣርያ ስትቀላቀል ብትኖርም በቅርብ ጊዜያት በአህጉራዊ ውድድሮች ያስመዘገበችውን ውጤት ተከትሎ ደረጃዋን አሳድጋ በቀጥታ ወደ ምድብ ማጣርያ ድልድል ገብታለች፡፡ ዋልያዎቹ በቋት 3 ውስጥ በመደልደላቸው ከ2 ታላላቅ የአፍሪካ ብሄራዊ ቡድኖች ጋር የመጋፈጥ ፈተና ሊገጠምት ይችላል፡፡

በአራት ቋት የተከፈሉት ሃገራት የሚከተሉት ናቸው፡፡ (በአንድ ቋት የሚገኙ ሃገራት እርስ በእርስ አይጫወቱም ፡፡ ቋት 1 ውስጥ የሚገኙት የምድብ አባት ናቸው )

ቋት 1 – ናይጄርያ ፣ ኮት ዲቯር ፣ ጋና ፣ ዛምቢያ ፣ ማሊ ፣ ቡርኪናፋሶ ፣ ቱኒዚያ

ቋት 2 – አልጄርያ ፣ አንጎላ ፣ ኬፕ ቬርዲ ፣ ካሜሩን ፣ ደቡብ አፍሪካ ፣ ግብፅ እና ቶጎ

ቋት 3 – ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ፣ ሴኔጋል ፣ ኢትዮጵያ ፣ ሱዳን ፣ ኒጀር ፣ ጊኒ እና ጋቦን

ቋት 4 – በቅድመ ማጣርያው የሚያልፉ 4 ሃገራት (28 ሃገራት በቅድመ ማጣርያ ተፋልመው 4 ይቀራሉ)

የ2015 አፍሪካ ዋንጫ ከጃንዋሪ 17 እስከ ፌብሪወሪ 8 በሞሮኮ ይካሄዳል፡፡

አጫጭር ዜናዎች

ዛሬ ከቀኑ በ10 ሰአት የኢትዮጵ ከ2 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን የሲሸልስ አቻውን አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ያስተናግዳል፡፡ በመጀመርያው ጨዋታ ሲሸልስ ላይ የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን 2-0 አሸንፎ መመለሱ ይታወሳል፡፡

የቀድሞው የደደቢት አምበል መንግስቱ አሰፋ ለመብራት ኃይል ፈርሟል፡፡ መብራት ኃይል ወላይታ ድቻን ባሸነፈበት ጨዋታ ተጎድቶ የወጣው አምበሉ አልሳዲቅ አልማሃን ክፍተት በቶሎ ይደፍናል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

የቀድሞው የዋልያዎቹ አለቃ በአዲሱ አሰልጣኝ ዙር ለመጀመርያ ጊዜ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ ‹‹ የሰውየውን ችሎታ ስለማላውቀው በሱ ዙርያ አስተያየት ለመስጠት ገና ነው፡፡ ከፍተኛ ገንዘብ ስለወጣ ብቻ ውጤት ለማግኘት ዋስትና አይሆንም፡፡ ሰውየው በቋንቋ በኩል ስለሚቸገር በፍጥነት ለውጥ ያመጣል የሚል እምነት የለኝም፡፡ በእኔ አመለካከት ለቦታው የሚመጥኑ ኢትዮጵያውያን ነበሩ፡፡ ›› ሰውነት ለኢትዮጵካ ሊንክ ከተናገሯቸው መካከል ዋና ዋናዎቹ ነበሩ፡፡

የዛሬውን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ድልድል ዩ-ቲዩብ በቀጥታ መከታተል ለምትፈልጉ ካፍ በዩቲዩብ ቻናሉ (ካፍ ሚድያ) ያስተላልፋል፡፡

{jcomments on}

ያጋሩ