በካፍ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ የአንደኛ ዙር ጨዋታዎች እሁድ በተደረጉ ግጥሚያዎች ተጠናቅቀዋል፡፡ በሜዳቸው የተጫወቱ ሁሉም ክለቦች ድል ቀንቷቸዋል፡፡
ቱኒዝ ላይ የሴራሊዮኑን ሪፐብሊክ ኦፍ ሴራሊዮን አርምድ ፎርስስን ያስተናገደው ክለብ አፍሪኬን 9-1 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ ከወዲሁ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ እድሉን አስፍቷል፡፡ አልጄሪያው የመስመር አማካይ ኢብራሂም ቼኔሂ አራት ግቦችን በማስቆጠር የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ውሏል፡፡ ቀሪዎቹን ግቦች ሳብር ካሊፋ፣ የቀድሞ የኤስፔራንስ ኮከብ ኦሳማ ዳራጂ፣ ጋንድሪ እና ሚኒያዊ ከመረብ አዋህደዋል፡፡
የኮትዲቯሩ ሃያል አሴክ ሚሞሳስ በሜዳው የካሜሮኑን አፔጄስ ደ ሞፎን 2-0 ማሸነፍ ችሏል፡፡ የብሩሪናፋሶው ኢንተርናሽናል አርስቲድ ባንሴ እና ዶሶ ፋብዮስ የሚሞሳስን የድል ግቦች አስቆጥረዋል፡፡
የታንዛኒያው አዛም የስዋዚላንዱን ምባባኔ ስዋሎስ በረመዳን ሲንጋኖ ብቸኛ ግብ ዳሬ ሰላም ላይ 1-0 መርታት ችሏል፡፡
የመልስ ጨዋታዎች በያዝነው ሳምንት ይደረጋሉ፡፡
አርብ ውጤቶች
ሰሞሃ (ግብፅ) 4-0 ኡሊንዚ ስታርስ (ኬንያ)
ዜስኮ ዩናይትድ (ዛምቢያ) 2-0 ለ ሜሰንጀር ደ ንጎዚ (ብሩንዲ)
ሞሊዲያ ክለብ ደ አልጀር (አልጄሪያ) 2-0 ሬኔሳንስ ዱ ኮንጎ (ዲ.ሪ. ኮንጎ)
ቅዳሜ ውጤት
ክለብ ሬክሬቲቮ ዲስፖርቲቮ ዱ ሊቦሎ (አንጎላ) 2-1 ንጌዚ ፕላቲኒየም ስታርስ (ዚምባቡዌ)
ሳንጋ ባላንዴ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) 1-0 አል ሂላል ኦባያድ (ሱዳን)
ኤቷል ዱ ኮንጎ (ኮንጎ ሪፐብሊክ) 0-0 ዩኒየስ ስፖርቲቭ ደ ካቤሌ (አልጄሪያ)
ቫይፐርስ (ዩጋንዳ) 1-0 ፕላቲኒየም ስታርስ (ደቡብ አፍሪካ)
ኤኤስ ካሎም (ጊኒ) 1-0 ኢቲሃድ ታንገር (ሞሮኮ)
ኦንዜ ክሬቸርስ (ማሊ) 1-0 ራዮን ስፖርት (ሩዋንዳ)
ክለብ ስፖርቲፍ ሴፋክሲየን (ቱኒዚያ) 5-0 ዮንግ ስፖርትስ አካዳሚ (ካሜሮን)
እሁድ ውጤቶች
ክለብ አፍሪኬን (ቱኒዚያ) 9-1 ሪፐብሊክ ኦፍ ሴራሊዮን አርምድ ፎርስስ (ሴራሊዮን)
አሴክ ሚሞሳስ (ኮትዲቯር) 2-0 አፔጄስ ደ ምፎ (ካሜሮን)
ጆሊባ ደ ባማኮ (ማሊ) 2-0 አለ መስሪ (ግብፅ)
መግረብ ደ ፈስ (ሞሮኮ) 3-1 ስፖርቲግ ክለብ ደ ጋግኖአ (ኮትዲቯር)
አዛም (ታንዛኒያ) 1-0 ምባባኔ ስዋሎስ (ስዋዚላንድ)
ኤል አሃሊ ሸንዲ (ሱዳን) 3-2 ሱፐርስፖርት ዩናይትድ (ደቡብ አፍሪካ)