የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት ዛሬ በተደረጉ ጨዋታዎች ተገባደዋል

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከቅዳሜ ጀምሮ ሲካሄዱ ቆይተው ዛሬ ፍጻሜያቸውን አግኝተዋል፡፡ በዛሬ ጨዋታዎችም ደደቢት ከተከታዩ ያለውን ልዩነት ሲያሰፋ ፣ መከላከያ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል አስመዝግበዋል፡፡

ምድብ ሀ

በ9:00 መከላከያ ከኢትዮጵያ ቡና ባደረጉት ጨዋታ መከላከያ ሙሉ ለሙሉ የጨዋታ የበላይነት በመውሰድ 4-1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፡፡ ከሰሞኑ ድንቅ እንቅስቃሴን እያሳየች የምትገኘው ምስራች ላቀው በ9 እና በ50ኛው ደቂቃ ሁለት ግቦችን ማስቆጠር ስትችል ብሩክታዊት አየለ በ12ኛው እንዲሁም ፍቅርተ ብርሃኑ በ42ኛው ደቂቃ ቀሪዎቹን የመከላከያ ግቦች ማስቆጠር ችለዋል፡፡

በጨዋታው ጥሩ እንቅስቃሴን ማድረግ የቻለችው ምስራች ላቀው በ53ኛው ደቂቃ በሁለተኛ ቢጫ ካርድ ከሜዳ ልትወጣ ችላለች፡፡ በጨዋታው መገባደጃ አካባቢ መከላከያዎች የግብ ልዩነቱን ሊያሰፉበት የሚችሉበትን የፍፁም ቅጣት ምት ሄለን ሰይፉ ሳትጠቀምበት ቀርታለች፡፡

በእለቱ ሁለተኛ መርሃግብር በነበረው ጨዋታ ደደቢቶች በሁለተኛው አጋማሽ ባስቆጠሯቸው አምስት ግቦች ታግዘው ቦሌ ክፍለከተማን 5-0 ማሸነፍ ችለዋል፡፡

ከጨዋታው በፊት የደደቢቱ አሰልጣኝ ጌቱ ለወትሮው በቋሚነት ከሚጠቀምባቸው ተጫዋቾች 8ቱን ተጠባባቂ አድርጎ በጨዋታው በውድድር ዘመኑ እምብዛም የመሰለፍ እድል ላላገኙ ተጫዋቾች በመስጠት ነበር ጨዋታውን መጀመር የቻለው፡፡

በጨዋታው ቡድኑን በአንበልነት እየመራች የገባችው ውብአለም ፀጋዬ በሜዳ ውስጥ መቆየት የቻለችው ለ37 ያክል ሰከንዶች ብቻ ነበር፡፡ ከቦሌዋ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ከሆነችው የቀድሞዋ የደደቢት ተጫዋች ምንትዋብ ዮሀንስ ጋር በመጋጨትዋ ባጋጠማት ጉዳት ተቀይራ ለመውጣት ተገዳለች፡፡

ተመጣጣኝ የሆነ እና ተመልካችን ያዝናና ጥሩ ጨዋታ በታየበት የሁለቱ ቡድኖች የመጀመሪያ አጋማሽ ቦሌዎች ሁለት ጥሩ ግብ የማግባት አጋጣሚዎችን ቢያገኙም የግቡ አግዳሚ እና ቋሚ ሊመልስባቸው ችሏል፡፡ በአንጻሩ ደደቢቶች በቤዛ እና በሰናይት ባሩዳ አማካኝነት የግብ እድሎችን መፍጠር ቢችሉም ሳይጠቀሙባቸው ቀርተዋል፡፡

በሁለተኛው አጋማሽ ጅማሮ የጨዋታውን ውጤት ለመቀየር በማሰብ አሰልጣኝ ጌቱ ተሾመ የቡድኑ ወሳኝ ተጫዋቾች የሆኑትን ሎዛ አበራ ፣ መስከረም ካንኮ እንዲሁም ትዕግስት ዘዉዴን በአንድ ጊዜ ቀይረው በማስገባት የጨዋታውን ውጤት ለመቀየር ችሏል፡፡ ቅያሬውም ፍሬ አፍርቶ ደደቢቶች በሁለተኛው አጋማሽ ከፍፁም የጨዋታ የበላይነት ጋር 5-0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል፡፡ ሰናይት ቦጋለ አንድ እንዲሁም ሎዛ አበራና ሰናይት ባሩዳ ሁለት ሁለት ግቦችን በስማቸው ማስመዝገብም ችለዋል፡፡

በጨዋታው የሁለተኛው አጋማሽ ተቀይራ ወደ ሜዳ የገባችው ሎዛ አበራ በግሏ ሶስተኛና አራተኛውን ግብ ከማስቆጠሯ በተጨማሪ የመጀመሪያዎቹን ሁለት ግቦች እንዲቆጠሩ አመቻችታ ማቀበል ችላለች፡፡

በዚሁ ምድብ በተደረጉ የዚህ ሳምንት ጨዋታዎች ትላንት አበበ ቢቂላ ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ንፋስ ስልክ ላፍቶን 1-0 ሲያሸንፍ ድሬዳዋ ላይ በወቅታዊ ምርጥ አቋም ላይ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ ኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚን በትደግ ፍስሀ (ሁለት) እና ቅድሰት መርሻ ጎለሎች 3-1 መርታት ችሏል፡፡ ቅዳሜ አዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም ላይ ጥረትን ያስተናገደው አዳማ ከተማ ደግሞ 2-1 ተሸንፏል፡፡

[table “236” not found /]

የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ – ምድብ ሀ

#ክለብተጫአሸአቻተሸአስተቆልዩነጥብ
11817107366752
218123330131739
31811342418636
418102629171232
5188462926328
6187472724325
71852111632-1617
81843112245-2315
91813141141-306
10180513847-395

ምድብ ለ

ዛሬ ወደ አርባምንጭ አቅንቶ አርባምንጭ ከተማን የገጠመው ቅዱስ ጊዮርጊስ 2-0 ማሸነፍ ችሏል፡፡ ሜሮን አብዶ የቅዱስ ጊዮርጊስን ሁለት የድል ግቦች ያስቆጠረች ተጫዋች ናት፡፡

ትላንት ሀዋሳ ላይ አዲስ አበባ ከተማን ያስተናገደው ሀዋሳ ከተማ የሳምንቱን ከፍተኛ ድል በማስመዝገብ 6-0 አሸንፏል፡፡ ግብ አነፍናፊዋ አይናለም አሳምነው 5 ጎሎች በማስቆጠር በዘንድሮው የውድድር ዘመን በአንድ ጨዋታ ከፍተኛ ግብ የማስቆጠር ሪኮርዱን ስትጨብጥ ነጻነት መና ቀሪዋን ግብ አክላለች፡፡ አይናለም (ከላይ በፎቶው ላይ የምትታየው) የግቧን  መጠን ወደ 18 በማድረስ ሎዛ አበራን የተከተለቻት ትገኛለች፡፡

በተመሳሳይ ትላንት አበበ ቢቂላ ላይ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማን የገጠመው ልደታ ክፍለ ከተማ 2-0 ሲያሸንፍ እሁድ ወደ ይርጋለም ያመራው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲዳማ ቡናን በህይወት ደንጊሶ እና ብዙነሽ ሲሳይ ግቦች  2-0 አሸንፏል፡፡ ዲላ ላይ ደግሞ ጌዲኦ ዲላ ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲን 3-2 አሸንፏል፡፡

[table “240” not found /]

የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ – ምድብ ለ

#ክለብተጫአሸአቻተሸአስተቆልዩነጥብ
11815124974246
21814044774042
31810262524132
4189452318531
5188642213930
6189272521429
71861111933-1419
91822141544-298
101821151354-417

የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች

1 ሎዛ አበራ (ደደቢት) – 22 

2 አይናለም አሳምነው (ሀዋሳ ከተማ) -18

3 ትደግ ፍስሀ (ድሬዳዋ ከተማ) – 12 

3 Comments

  1. ye loza gib amerachnet yemigerm new amna ke hamsa belay behulum wededroch askotralech zendrom 22 dersalech yemigerm bekat new. tilk bota dersa enayat yihonal berchiln Loza.

  2. በመጨረሻው አንቀፅ ሁለተኛ መስመር ላት ኢትዮጵያ ሲዳማ ቡናን የሚለው ቢስተካከል እንዲሁም ውብአለም ፀጋዬ ከምን ደርሳለች በአንቡላንስ ወደ ሆስፒታል ከሄደች በሗላ የጉደት መጡ ምን ያህል ነው?
    በጣም እናመሰግናለን።

Leave a Reply