ካፍ ያዘጋጀው የአፍሪካ እግርኳስ ፎረም ተካሄደ

የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌድሬሽን (ካፍ) ያዘጋጀው የአፍረካ እግርኳስ ፎረም በአፍሪካ ህብረት መሰብሰቢያ አዳራሽ ዕረቡ እለት ተደርጓል፡፡ የካፍ ፕሬዝደትን ኢሳ ሃያቱ፣ የኢትዮጵያ ፌድራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የፊፋ ፕሬዝደንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ እና ጥሪ ተደረገላቸው እንግዶቹ ተገኝተዋል፡፡

በፎረሙ በአራት ክፍሎች ተከፍሎ የፓናል ውይይት ተደርጓል፡፡ በፓናል ውይይቱ ላይ ስለ መንግስት እና የፌድሬሽኖች ግንኙነት፣ ስለሴቶች በስፖርት አመራርነት ላይ ያላቸው ተሳትፎ እንዲሁም የቴሌቪዥን መብት ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል፡፡ የካፍ ፕሬዝድት ኢሳ ሃያቱ ወደ ስፖርት አመራርነቱ የመጡበትን መንገድ በፎረሙ ያካፈሉ ሲሆን የአፍሪካን እግርኳስ ለማሳደግ ከወጣትነታቸው ጀምሮ መጣራቸውን ተናግረዋል፡፡ የአፍሪካ ዋጫ ለምን በየሁለት ዓመቱ ሊሆን እንደቻለም ፕሬዝደንቱ በውይይቱ አስረድተዋል፡፡ የአፍሪካ ዋንጫ በየሁለት ዓመቱ መካሄዱ የአዘጋጅ ሃገራት በመሰረተ ልማትን እንዲያስፋፉ እንደረዳቸው በፓናል ውይይቱ ከነሱ ሀሳቦች መካከል ቀዳሚው ነው፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በበኩላቸው በፓናል ውይይቱ ላይ ፀረ ቅኝ ግዛት እና ፀረ አፓርታይትድ እንቅስቃሴ ላይ የተጫወተችውን ሚና አስረድተዋል፡፡ የሃያቱ አማካሪ የሆኑት ኢትዮጵያዊው እውቅ ጋዜጠኛ ፍቅሩ ኪዳኔ እንዴት ደቡብ አፍሪካን ከካፍ ውድድሮች እንዳገዱ አስረድተዋል፡፡ መንግስታት ለፌድሬሽኖች እና ለታዳጊዎች የሚሰጡትን እገዛ ተመጣጣኝ አለመሆኑ ላይም አቶ ፍቅሩ ሃሳባቸውን ገልፀዋል፡፡

“ፓለቲከኞች በብዛት ወሳኔ ብቻ ነው የሚያሳልፉት፡፡ እግርኳስ ግን በተግባር ለውጥ እያመጣ ነው ለችግሮቻችንም መፍትሄዎችን ሲሰጠን ቆይቷል ከፖለቲከኞች በተሻለ፡፡ መንግስቴች ለታዳጊዎች ውድድር የፋይናንስ አቅም የለንም ይላሉ ግን ብሄራዊ ቡድኖቻቸው ለአለም ዋንጫ ወይም ለትልቅ ውድድር ሲያልፉ ዳጎስ ያለ ገንዘብ ይሰጣሉ፡፡ ይህ መስተካከል አለበት ብለዋል” አቶ ፍቅሩ፡፡

በፓናል ውይይቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የቦርድ ፕሬዝደንት አቶ አብነት ገብረመስቀል ተገኝተው ንግግር ካደረጉ ሰዎች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *