ኢትዮጵያ ቡና ከ አዳማ ከተማ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

 FT  ኢትዮጵያ ቡና   0-0   አዳማ ከተማ 
ተጠናቀቀ!
ጨዋታው ያለግብ በአቻ ውጤት ተፈፅሟል፡፡

ቢጫ ካርድ
90+4′ ያቡን ዊልያም የዳኛ ውሳኔ በመቃወም የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቡና
90+3′ እየያሱ ታምሩ ወጥቶ መሰኡድ መሀመድ ገብቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
90′ አስቻለው ግርማ የዳኛ ውሳኔ በመቃወም የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

82′ በመልሶ ማጥቃት የመጣውን ኳስ ነጻ አቋቋም ላይ የነበረው ተስፋዬ ነጋሽ አግኝቶ ወደ ውጪ ሰዶታል፡፡ የሚያስቆጭ አጋጣሚ!

የተጫዋች ለውጥ – ቡና
81′ ኤልያስ ማሞ ወጥቶ ያቡን ዊልያም ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቡና
78′ አክሊሉ ዋለልኝ ወጥቶ አማኑኤል ዮሃንስ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አዳማ
74′ ሚካኤል ጆርጅ ወጥቶ ተስፋዬ ነጋሽ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አዳማ
67′ ዳዋ ሁቴሳ ወጥቶ ሱራፌል ዳኛቸው ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አዳማ
57′ ተስፋዬ በቀለ ወጥቶ ቡልቻ ሹራ ገብቷል፡፡

49′ አብዱልከሪም ከመስመር ለሳኑሚ ያሻገረውን ኳስ ጃኮ ቀድሞ አውጥቶታል፡፡

ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡

እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ ያለ ግብ ተጠናቋል፡፡

45+3′ እያሱ ታምሩ በፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ከቀኝአቅጣጫ የመታውን ኳስ ጃኮ በቀላሉ ይዞበታል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 4

ሳተ!
35′ ጋቶች ፓኖም የፍጹም ቅጣት ምቱን መትቶ ጃኮ ፔንዜ አድኖበታል፡፡

ፍጹም ቅጣት ምት!
34′ ሲሳይ ቶሊ በአህመድ ረሺድ ላይ በሰራው ጥፋት ለቡና የፍፁም ቅጣት ምት ተሰጥቷል፡፡ ሲሳይ ቢጫ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
28′ እሸቱ መና በአስቻለው ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ አይቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
24′ ጋቶች ፓኖም በፋሲካ አስፋው ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

15’ኤልያስ ማሞ በግምት ከ30 ሜትር ርቀት በቀጥታ የመታውን ቅጣት ምት ጃኮ ፔንዜ አውጥቶታል፡፡ ሙከራውም የግብ ጠባቂው አመላለስም ድንቅ ነበር፡፡

10′ ፋሲካ አስፋው ከርቀት የሞከረውን ኳስ ሀሪሰን በግሩም ቅልጥፍና ወደ ውጪ አውጥቶታል፡፡

3′ ከማዕዘን የተሻገረውን ኳስ ሙጂብ ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

ተጀመረ!

ጨዋታው በሳሙኤል ሳኑሚ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡

በአአ ከተማ ቆሼ አካባቢ በተፈጠረ አደጋ ህይወታቸውን  ያጡ እና ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎቻችንን ለማሰብ የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ቡና አሰላለፍ
99 ሀሪሰን ሄሱ

15 አብዱልከሪም መሀመድ – 5 ወንድይፍራው ጌታሁን – 16 ኤፍሬም ወንድወሰን – 13 አህመድ ረሺድ

25 ጋቶች ፓኖም – 19 አክሊሉ ዋለልኝ – 9 ኤልያስ ማሞ

24 አስቻለው ግርማ – 11 ሳሙኤል ሳኑሚ – 14 እያሱ ታምሩ

ተጠባባቂዎች

50 ጆቤድ ኡመድ

3 መስኡድ መሀመድ

4 ኢኮ ፊቨር

8 አማኑኤል ዮሀሃንስ

17 አብዱልከሪም ሀሰን

21 አስናቀ ሞገስ

28 ያቡን ዊልያም

የአዳማ ከተማ አሰላለፍ 

ጃኮ ፔንዜ

14 እሸቱ መና – 4 ምኞት ደበበ – 5 ተስፋዬ በቀለ – 9 ሲሳይ ቶሊ

21 አዲስ ህንፃ – 20 ደሳለኝ ደባሽ – 2 ፋሲካ አስፋው 

12 ዳዋ ሁቴሳ – 13 ሚካኤል ጆርጅ – 17 ሙጂብ ቃሲም 

ተጠባባቂዎች
30 ጃፋር ደሊል

7 ሱራፌል ዳኛቸው

10 ታፈሰ ተስፋዬ

14 በረከት ደስታ

16 ተስፋዬ ነጋሽ 

18 ቡልቻ ሹራ

23 ቢንያም አየለ

09:55 የሁለቱ ቡድን ተጫዋቶች ወደ ሜዳ ገብተው ሰላምታ  እየተለዋወጡ ይገኛሉ፡፡

09:45 ለቀድሞዋ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና ኢትዮጵያ ቡና አምበል እየሩሳሌም ነጋሽ ህክምና የሚውል ድጋፍ ከተመልካች እየተሰበሰበ ይገኛል፡፡ የዛሬው ጨዋታ ሙሉ የስታድየም ገቢውም ለእየሩሳሌም ነጋሽ ህክምና እንዲውል ኢትዮጵያ ቡና ወስኗል፡፡

09:45 ተጫዋቾች እና ዳኞች አሟሙቀው ወደ መልበሻ ክፍል ተመልሰዋል፡፡

09:25 የሁለቱ ቡድን ተጫዋቾች ሜዳ ገብተው እያሟሟቁ ይገኛል፡፡

ዳኛ 

ኢንተርናሽናል አርቢትር ኃይለየሱስ ባዘዘው ጨዋታውን ይመራዋል፡፡

ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን! 

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 19ኛ ሳምንት ኢትዮጵያ ቡና ከ አዳማ ከተማ የሚያደርጉትን ጨዋታ ሶከር ኢትዮጵያ በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ወደ እናንተ ታደርሳለች፡፡
መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር

Leave a Reply