በ18ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ባለፈው እሁድ ኢትዮዽያ ቡናን አስተናግዶ 4-1 በሆነ ውጤት የተሸነፈው ፋሲል ከተማ ደጋፊዎቹ በጨዋታው ባሳዩት ያልተገባ ተግባር አንድ ጨዋታ ከሜዳው ውጪ እንዲያደርግ ቅጣት ተላልፎበታል፡፡
በጨዋታው ላይ የፋሲል ከተማ ደጋፊዎች የዳኛን ውሳኔ በመቃወም በተፈጠሩት ግርግር ጨዋታው 36 ደቂቃ ያህል መቋረጡን ተከትሎ የዲሲፒሊን ኮሚቴ ትላናት ማታ ስብሰባ አድርጎ በወሰነው ውሳኔ መሰረት በቀጣይ በሜዳው ከወልድያ ጋር መጋቢት 20 ቀን 2009 ሊያደርገው የነበረውን ጨዋታ በገለልተኛ ሜዳ እንዲያደርግ የተወሰነ ሲሆን ጨዋታው የት ቦታ እንደሚሆን ወደ ፊት እንደሚገለፅ ለማወቅ ችለናል፡፡
ፋሲል ከተማ ሁለተኛው ዙር ከተጀመረ ወዲህ ባደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎች ሁሉንም የተሸነፈ ሲሆን ከነዚህ መካከል ሁለቱ በሜዳው የተረታው ነው፡፡