ቻምፒየንስ ሊግ፡ ሃያሎቹ ክለቦች ወደ ምድብ ለመግባት ፈተና ይጠብቃቸዋል

በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ወደ ምድብ ለመግባት የሚደረጉት የአንደኛ ዙር የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ በሚካሄዱ ጨዋታዎች ይጀምራሉ፡፡ ከሳምንት በፊት በመጀመሪያ ጨዋታዎች ሃያሎቹ ክለቦች ያስመዘገቡት ውጤት ጥሩ አለመሆን በዘንድሮው ቻምፒየንስ ሊግ ያልተጠበቁ ቡድኖች ወደ ምድብ እንዲገቡ ያስችላል፡፡

የወቅቱ የአፍሪካ ቻምፒዮን ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ወደ ዩጋንዳ ተጉዞ ኬሲሲኤን ይገጥማል፡፡ ፕሪቶሪያ ላይ 2-1 ያሸነፉት ብራዚሎቹ ካምፓላ ላይ ከበድ ያለ ፈተና ይጠብቃቸዋል፡፡ በሰው ሰራሽ የሳር ሜዳ ላይ ጨዋታው መካሄዱ የሰንዳውንስ ውጤት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊኖረው ይችላል፡፡ ኬሲሲኤ ከሜዳው ውጪ ያስቆጠረው ግብ በመልሱ ጨዋታ የስነ-ልቦና ተነሳሽነትን ፈጥሮለታል፡፡ የካምፓላው ክለብ ጨዋታውን ማሸነፍ ከቻለ አስገራሚም የሳምንቱ ውጤት መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡

የዛምቢያው ዛናኮ በሜዳው የታንዛኒያውን ያንግ አፍሪካንስን ይገጥማል፡፡ ዛማቢያዊው የያንጋ አሰልጣኝ ጆርጅ ሉዋንዲማና ክለቡን ከያዙ በኃላ በትላልቅ ጨዋታዎች ያስመዘገቡት ውጤት ጥሩ አይደለም፡፡ በሜዳቸው ከዛናኮ ጋር አንድ አቻ መውጣቱ በዛሬው ጨዋታን የዛምቢያው ቻምፒዮን ለማለፍ የተሻለ እድል እንዲይዝ አስችሎታል፡፡

የጋቦኑ ሞናና ካዛብላንካ ላይ የደረሰበትን የ1-0 ጠባብ ሽንፈት ቀልብሷ ወደ ምድብ ለመግባት ከዋይዳድ ካዛብላንካ ጋር ተፋጧል፡፡ አል አሃሊ ትሪፖሊም የሞሮኮውን ቻምፒዮን ፉስ ራባትን በሞሮኮ መዲና ይገጥማል፡፡ ፉስ ቱኒዚያ ላይ 2-0 በመሸነፉ የመልሱ ጨዋታ የማሸነፍ ግዴታ ውስጥ ገብቷል፡፡ የሱዳኑ ኤል ሜሪክ ሪቨርስ ዩናይትድን ኦምዱሩማን ላይ ያስተናግዳል፡፡ የናይጄሪያው ሪቨርስ ፖርት ሃርኮት ላይ 3-0 በማሸነፉ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ የሰፋ እድል ይዟል፡፡

የኢትዮጵያው ተወካይ ቅዱስ ጊዮርጊስ የኮንጎ ሪፐብሊኩን ኤሲ ሊዮፓርድስን አዲስ አበባ ላይ ያስተናግዳል፡፡ ፈረሰኞቹ ከሳምንት በፊት ዶሊሲ ላይ ተጉዘው በምንተስኖት አዳነ የመጀመሪያ አጋማሽ ግብ 1-0 አሸንፈዋል፡፡ ወደ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ድልድል የገባ የመጀመሪያው የሃገራችን ክለብ ለመሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ አሁን ላይ የተሻለ እድልን ይዟል፡፡

 

ቅዳሜ

14:30 – ሲኤንኤፒኤስ ስፖርት (ማዳጋስካር) ከ ኮተን ስፖርት (ካሜሮን) [1-0]

15:00 – ዛናኮ (ዛምቢያ) ከ ያንግ አፍሪካንስ (ታንዛኒያ) [1-1]

15:00 – ሞናና (ጋቦን) ከ ዋይዳድ አትሌቲክ ክለብ (ሞሮኮ) [1-0]

15:30 – ሪያል ክለብ ዱ ካዲዮጎ (ቡርኪናፋሶ) ከ ዩኤስኤም አልጀር (አልጄሪያ) [2-0]

16:00 – ካምፓላ ሲቲ ካውንስል ኦቶሪቲ (ዩጋንዳ) ከ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ (ደቡብ አፍሪካ) [2-1]

19:00 – ፋት ዩኒየን ስፖርት (ሞሮኮ) ከ አል አሃሊ ትሪፖሊ (ሊቢያ) [2-0]

20:00 – ኤል ሜሪክ (ሱዳን) ከ ሪቨርስ ዩናይትድ (ናይጄሪያ) [3-0]

 

እሁድ

15:00 – ካፕስ ዩናይትድ (ዚምባቡዌ) ከ ቲፒ ማዜምቤ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) [1-1]

15:00 – ኤኤስ ደ ታንዳ (ኮትዲቯር) ከ ኤቷል ደ ሳህል (ቱኒዚያ) [3-0]

15:15 – ኤኤስ ፖር ሉዊ 2000 (ሞሪሺየስ) ከ አል ሂላል (ሱዳን) [3-0]

15:30 – ኤኤስ ቪታ ክለብ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) ከ ጋምቢያ ፖርትስ ኦቶሪቲ (ጋምቢያ) [1-1]

15:30 – ቤድቬስት ዊትስ (ደቡብ አፍሪካ) ከ አል አሃሊ (ግብፅ) [1-0]

16:00 – ባራክ ያንግ ኮንትሮለር (ላይቤሪያ) ከ ክለብ ፌሬቫያሮ ደ ቤይራ (ሞዛምቢክ) [2-0]

16:00- ቅዱስ ጊዮርጊስ (ኢትዮጵያ) ከ ኤሲ ሊዮፓርድስ ደ ዶሊሲ (ኮንጎ ሪፐብሊክ) [0-1]

16:00 – ሆሮያ (ጊኒ) ከ ኤስፔራንስ ደ ቱኒዝ (ቱኒዚያ) [3-1]

16:00 – ኢንጉ ሬንጀርስ ኢንተርናሽናል (ናይጄሪያ) ከ ዛማሌክ (ግብፅ) [4-1]

 

Leave a Reply