በካፍ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ወደ ኪንሻሳ ተጉዞ ሬኔሳንስ ዱ ኮንጎን የገጠመው የአልጄሪያው ኤምሲ አልጀር በአጠቃላይ ውጤት 3-2 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ የመጨረሻ ማጣሪያ ዙር ማለፉን አረጋግጧል፡፡
ኤምሲ አልጀር በጨዋታው 2-1 ቢሸነፍም ከሳምንት በፈት አልጀርስ ላይ ያስመዘገበው የ2-0 ውጤት ወደ ሁለተኛው ዙር አሳልፎቷል፡፡ ጨዋታውን በተጀመረ በ6ኛ ደቂቃ የአልጀርሱ ክለብ ተከላካይ ካራዊ በራሱ ግብ ላይ አስቆጥሮ ሬኔሳንስ መሪ ሲያደርግ በሁለተኛው አጋማሽ ኤምሲ አልጀር መህዲ ቃሲም አማካኝነት የአቻነት ግብ አግኝቷል፡፡ ጨዋታው ሊጠናቀቅ 10 ደቂቃች ሲቀሩት ግብ አስቆጣሪው ቃሲም የጨረፈው ኳስ ግብ ጠባቂውን ፋውዚ ካውቺን አቅጣጫን አስቶ ሬኔሳንስን የጨዋታውን አሸናፊ አድርጓል፡፡ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኃላ ከተመሰረተ ከገና በለጋነት ላይ ያለው የሬኔሳንስ ደጋፊዎች ወደ ሜዳ በመግባት ደስታቸውን ሲገልፁ ታይተዋል፡፡
ዛሬ 10 ጨዋታዎች በተለያዩ የአፍሪካ ከተሞች ይደረጋሉ፡፡ ፊፋ ማሊን እና ክለቧቿን ከማንኛውም ውድድር በማገዱ ኦንዜ ክሪቸርስ ከራዮን ስፖርት የሚያደርጉት ጨዋታ አይደረግም፡፡ ራዮን ስፖርት በዚህ አጋጣሚ ባማኮ ላይ የደረሰበትን የ1-0 ሽንፈትን መቀልበስ ሳይጠበቅበት በፎርፎ ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያልፍ ይሆናል፡፡
አርብ ውጤት (በቅንፍ የተጠቀሰው የድምር ውጤት ነው)
ሬኔሳንስ ዱ ኮንጎ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) 2-1 ሞሊዲያ ክለብ ደ አልጀር (አልጄሪያ) (3-2
ቅዳሜ
14፡00 – ንጌዚ ፕላቲኒየም ስታርስ (ዚምባቡዌ) ከ ክለብ ሬክሬቲቮ ዲስፖርቲቮ ዱ ሊቦሎ (አንጎላ) [1-2]
15፡00 – ዮንግ ስፖርትስ አካዳሚ (ካሜሮን) ከ ክለብ ስፖርቲፍ ሴፋክሲየን (ቱኒዚያ) [0-5]
15፡00 – ኡሊንዚ ስታርስ (ኬንያ) ከ ሰሞሃ (ግብፅ) [0-4]
15፡00 – ስፖርቲግ ክለብ ደ ጋግኖአ (ኮትዲቯር) ከ መግረብ ደ ፈስ (ሞሮኮ) [1-3]
15፡00 – ለ ሜሰንጀር ደ ንጎዚ (ብሩንዲ) ከ ዜስኮ ዩናይትድ (ዛምቢያ) [2-0]
15፡30 – ራዮን ስፖርት (ሩዋንዳ) ከ ኦንዜ ክሬቸርስ (ማሊ) [0-1] *
17፡00 – ኢቲሃድ ታንገር (ሞሮኮ) ከ ኤኤስ ካሎም (ጊኒ) [0-1]
18፡00 – ዩኒየስ ስፖርቲቭ ደ ካቤሌ (አልጄሪያ) ከ ኤቷል ዱ ኮንጎ (ኮንጎ ሪፐብሊክ) [0-0]
19፡00 – አለ መስሪ (ግብፅ) ከ ጆሊባ ደ ባማኮ (ማሊ) [0-2] *
20፡00 – ፕላቲኒየም ስታርስ (ደቡብ አፍሪካ) ከ ቫይፐርስ (ዩጋንዳ) [0-1]
እሁድ
14፡30 – ሪፐብሊክ ኦፍ ሴራሊዮን አርምድ ፎርስስ (ሴራሊዮን) ከ ክለብ አፍሪኬን (ቱኒዚያ) [1-9]
15፡00- አፔጄስ ደ ምፎ (ካሜሮን) ከ አሴክ ሚሞሳስ (ኮትዲቯር) [0-2]
15፡30 – ምባባኔ ስዋሎስ (ስዋዚላንድ) ከ አዛም (ታንዛኒያ) [0-1]
18፡00 – ሱፐርስፖርት ዩናይትድ ከ ኤል አሃሊ ሸንዲ (ሱዳን) [2-3]
20፡00 – አል ሂላል ኦባያድ (ሱዳን) ከ ሳንጋ ባላንዴ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) [0-1]