የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የመጀመርያ ዙር አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ

የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የመጀመርያ ዙር አፈጻጸም ግምገማ በዛሬው እለት በቸርችል ሆቴል የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የውድድር አመራሮች እና የክለብ ተወካዮች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የመክፈቻ ንግግር በብሄራዊ ውድድሮች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አበባው ገላጋይ አማካኝነት ከቀረበ በኋላ የ1ኛው ዙር የአፈጻጰም ሪፖርት በ1ኛ ሊግ ምክትል ሰብሳቢ አማካኝነት ቀርቧል፡፡

በሪፖርቱ የውድድሩ አላማ የሆኑትን ሰላም ፣ እድገት እና ወንድማማችነች ከመፍጠር አኳያ የተሰሩ ስራዎች የቀረቡ ሲሆን ያጋጠሙ ችግሮች እና ደካማ ጎኖች ተብራርተዋል፡፡

ከውድድሩ ሪፖርት በመቀጠል የዳኞች ፣ የዲሲፕሊን ፣ የጸጥታ እነና የይግባኝ ሰሚ ኮመሚቴዎች ሪፖርት ተስተናግዶ ወደ ሻይ እረፍት ያመሩ ሲሆን ከእረፍት መልስ የክለብ ተወካዮች ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በክለቦች ከተነሱ ጉዳዮች መካከል:-

*ፌዴሬሽኑ ዳኞችን ከመመደብ አልፎ ብቃተታቸውን ወርዶ መመልከት ይኖርበታል፡፡

* በሁለተኛው ዙር በሚድያ ፣ ሜዳ ፣ ዳኛ እና ኮሚሽነር አመዳደብ እነንዲሁም ኮሚኒኬ ላይ ትኩረት መደረግ ይኖርበታል፡፡

* ዳኛ አንድ ክለብን ከ4 ጊዜ በላይ ይዳኛል፡፡ ይህ ሊስተካከል ይገባል፡፡

* የውድድሩ 2ኛ ዙር መጀመርያ በአንድ ሳምንት ይራዘም

* ለዳኞች አበል የሚወጡ አላስፈላጊ ወጪዎች አሉ፡፡ በተቀራራቢ ቦታ ላይ የሚገኙ ክለቦቸን ከሩቅ አካባቢ የሚመጣ ዳኛ ሲዳኝ ከፍተኛ ወጪ እየዳረገ ይገኛል፡፡

* ፌዴሬሽኑ ለውድድሩ ማማር ከሌሎች አካላት ጋር ያለውን ትስስር ይጠናከር

* በዛሬው ግምገማ የቴክኒክ ኮሚቴ መኖር ነበረበት

* የጸጥታ ጉዳይ ከአአ ወጣ ብሎ በሌሎች ክልሎችም ተደራሽ መሆን አለበት

* ዳኞች ትክክለኛ ውሳኔ ከመወሰን ይልቅ አቻችሎ ለማለፍ ሲሞክሩ የሁከት መንስኤ እየሆኑ ነው፡፡

* በአንዳንድ ሜዳዎች ላይ የመጫወቻ ሜዳውን ከደጋፊ የሚለይ አጥር የለም፡፡ ይህ ለእንግዳ ቡድን እነና ለዳኞች ስጋት እየሆነ ነው፡፡ በደጋፊዎች ዛቻ ምክንያት በስነልቦናው በኩል ይጎዳሉ፡፡

* ኮምሽነሮች ዳኞችን በጨዋታ ላይ ብቻ ሳይሆን ከጨዋታ ውጪም የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ መከታተል አለባቸው፡፡  የመቻቻል ስራ መሆን የለበትም፡፡

* ተጫዋች ፣ ደጋፊ እና ክለብ ይቀጣሉ፡፡ ለዚህ መንስኤ እየሆኑ ያሉት ዳኞች ግን ተቀጥተው አያውቁም፡፡

ከላይ የተዘረዘሩ እና ሌሎች ተያያዥ ስራዎች በግምገማው ወቅት ከክለቦች የተነሱ ሲሆን ከውድድሩ ኮሚቴ ኃላፊዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ የ2ኛው ዙር የመጀመርያ ቀን እንዲራዘም በየተነሳው ሃሳብ ላይ ድምፅ ተሰጥቶበት እንዲራዘም ተደርጓል፡፡ በዚህም መሰረት መጋቢት 16 እና 17 ሊጀመር የነበረው ውድድር በአንድ ሳምንት ተራዝሞ መጋቢት 23 እና 24 እንዲጀመር ተወስኗል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *