የአሰልጣኞች አስተያየት | መከላከያ 2-1 ቅዱስ ጊዮርጊስ

በለጠ ገ/ኪዳን – መከላከያ

ስለ ጨዋታው

“በጨዋታው ላይ ተጫዋቾቼ ባሳዮት ነገር በጣም ረክቻለሁ፡፡ የፍፁም ቅጣት ምቷ ገብታ ቢሆን ኖሮ ጨዋታው ሌላ መልክ ሊይዝ ይችል ነበር፡፡ በተለይም በዛሬው ጨዋታ ተጫዋቾች ላይ ያየሁት የመንፈስ ጥንካሬና ለማሸነፍ የነበረን ፍላጎት ከፍተኛ ስለነበር ጨዋታውን ማሸነፍ ይገባናል፡፡”

ስለ ቀጣይ እቅድ

“ቡድናችን ኳስን ተቆጣጥሮ ለመጫወት የሚጥር ቡድን እንደመሆነ ቡድናችን በተደጋጋሚ ሲቸገር ተስተውሏል፡፡ ስለዚህ በቀጣይ አጨዋወታችን ላይ አጫጭር እና ረጃጅም ኳሶችን በመቀላቀል ለመጠቀም እንሞክራለን፡፡ከዚህ በኃላ በቀሪ ጊዜያት የተሻለ ነገር ለመስራት እንጥራለን፡፡”

ፋሲል ተካልኝ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

ስለ ጨዋታው

“ግቧን ካስቆጠርን በኃላ በነበሩት 10 ደቂቃዎች በነበረብን የትኩረት ማነስ ችግር የተነሳ ሁለት ግቦችን አስተናግደናል፡፡ ምንም እንኳን አጥቅተን ብንጫወትም ግቦቹ ከተቆጠሩብን በኃላ የግብ እድሎችን መፍጠር አልቻልንም፡፡”

ስለ ሮበርት ኦዶንካራና በሀይሉ አሰፋ በቡድኑ ውስጥ አለመኖር

“ሮበርትም ሆነ ሀይሉ አሰፋ ምንም ጥያቄ የለውም የቡድናችን ወሳኝ ተጫዋቾች ናቸው፡፡ እኔ በግሌ ለዛሬው ጨዋታ ሽንፈት ምክንያት የእነሱ አለመኖር ነው ብዬ አላስብም ፤ ለጨዋታው በቂ የሆኑ ተጫዋቾች በሜዳ ውስጥ ነበሩን፡፡ ነገርግን የትኩረት ማነሳችን ዋጋ አስከፍሎናል፡፡”

የዛሬው ሽንፈት በዋንጫ በሚያደርጉት ግስጋሴ ስላለው ተጽዕኖ

“በዛሬው ጨዋታ 3 ነጥብ ብናስመዘግብ ኖሮ በተሻለ ከተከታዮቻችን መራቅ እንችል ነበር፡፡ በውድድሩ ገና በርካታ ቀሪ ጨዋታዎች ስላሉ ክፍተቶችን አርመን በቀጣይ እንቀርባለን፡፡”

1 Comment

Leave a Reply