አርቢትር አሸብር ሰቦቃ ቅጣት ተላለፈባቸው

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ባለፈው ሀሙስ ቀትር ላይ በተደረገው ጨዋታ ዳሸን ቢራ ላይ አላግባብ የፍፁም ቅጣት ምት ሰጥተዋል ያላቸውን አርቢትር አሸንር ሰቦቃን የ6 ወራት ቅጣት ጥሎባቸዋል፡፡

ሀሙስ ሚያዝያ 23 ቀን 2006 አም በ9 ሰአት በሊጉ የመጨረሻ ደረጃ ላይ የሚገኘው ኢትዮጵያ መድን ከሌላው በወራጅ ቀጠና ከሚገኘው ዳሽን ቢራ ጋር ያደረጉት ጨዋታ ዳሽን ቢራ ኤርሚያስ ኃይሉ ባስቆጠረው ግብ 1-0 ሲመራ ቆይቶ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሊጠናቀቅ ሁለት ደቂቃዎች ሲቀሩት ከግራ መስመር የተነሳችውን ኳስ አምበሉ አይናለም ኃይለ በእጁ ነክቷል በሚል የእለቱ አርቢትር አሸብር ሰቦቃ የፍፁም ቅጣት ምት መስጠታቸውን ተከትሎ ዳሽን ቢራ ለማሸነፍ የተቃረበውን ጨዋታ በአቻ ውጤት አጠናቋል፡፡

ከጨዋታው ፍፃሜ በኋላ የአርቢትሩ ውሳኔ አነጋጋሪ ሆኖ ሲዘልቅ ፌዴሬሽኑም ከጨዋታው ኮሚሽነር በደረሰው ሪፖርት መሰረት የቅጣት ውሳኔ አሳልፏል፡፡ በውሳኔውም መሰረት አርቢትር አሸብር ሰቦቃ ከማንኛውም የእግርኳስ እንቅስቃሴ ለ6 ወር ታግደዋል፡፡

ሁለቱ በወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኙት ክለቦች ጨዋታ ከማድረጋቸው በፊት የጎንደሩ ክለብ አርቢትር አሸብር ሰቦቃ ከሐረር የመጡ በመሆናቸውና ሐረር ከነማም ላለመውረድ በሚደረገው ፉክክር ተሳታፊ በመሆኑ ጨዋታው ላይ ተፅእኖ ይፈጥራል በሚል ለአርቢትር ኮሚቴው ጥያቄ አቅርበናል ያሉ ሲሆን የኮሚቴው ሰብሳቢ የቀድሞው ረዳት አርቢትር ልኡል ሰገድ በጋሻው ዳሽኖች ጥያቄ እንዳላቀረቡ ተናግረዋል፡፡

ልኡልሰገድ ትላንት በኤፍ.ኤም 97.1 የስፖርት ፕሮግራም ላይ በስልክ በሰጡት አስተያየት ‹‹ ጥያቄ አቅርበን ያሉት ነገር ሀሰት ነው፡፡ ጥያቄው ቢነሳ ኖሮ በአሰራራችን መሰረት ከኮሚሽነሩ ሪፖርት ይደርሰን ነበር፡፡ በተጨማሪም ፌዴሬሽኑ ለጨዋታዎች ዳኖች የሚመድበው በብቃት እንጂ የክልል ተዋፅኦን መሰረት በማድረግ አይደለም፡፡ ›› ብለዋል፡፡

{jcomments on}

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *