የአሰልጣኞች አስተያየት | ደደቢት 1-1 ጅማ አባቡና

አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ – ጅማ አባቡና

ስለ ጨዋታው

“የጨዋታውን ውጤት በሁለታችን በኩል እንፈልገው ስለነበር ጨዋታው የሀይል አጨዋወት የበዛበት ነበር፡፡ ከጨዋታው ወሳኝነት የተነሳ ከፍተኛ ዝግጅት አድርገን ነበር የመጣነው፡፡ ነገርግን እንደነበረው ጨዋታ ቢሆን አሸንፈን መውጣት ይገባን ነበር፡፡ ይህ ውጤት የሚገባን አልነበረም፡፡”

በጨዋታው ስላቀዱትና ስላሳኩት ነገር

“ወደ ጨዋታው ስንገባ ለማሸነፍ ነበር፡፡ ነገርግን ብዙም እዚህ ላይ ሆኖ መግለፁ አስፈላጊ ባይሆንም በጨዋታው ላይ በታየው ድራማ አሸንፈን መውጣት ሲገባን አቻ ለመለያየት ተገደናል፡፡”

አሰልጣኝ ኤልያስ ኢብራሂም – ደደቢት

ስለ ጨዋታው

“በመጀመሪያው አጋማሽ መጠነኛ መዘናጋቶች ነበሩ ፤ በዚህም እንደአጋጣሚ ሆኖ ግብ አስተናግደናል ከዚያ በኃላ የነበረው እንቅስቃሴ አስደሳች አልነበረም፡፡ ጅማ አባቡናዎች አብዛኛውን የጨዋታውን ደቂቃዎች በመውደቅ ሰአት ለመግደል ጥረት ሲያደርጉ ነበር፡፡ ከሞላ ጎደል ጥሩ መንቀሳቀስ ብንችልም ውጤቱ ግን ይህ መሆን አልነበረበትም፡፡”

በጨዋታው ከተቃራኒ ቡድን ይገጥመናል ብለው ስላሰቡት ነገር

“በኛ ልጆች በኩል ከልክ ያለፈ የራስ መተማመን ይታይ ስለነበር በመጀመሪያው አጋማሽ መጠነኛ መዘናጋቶች ነበሩ፡፡ ከእረፍት መልስ እነዚህን ችግሮች ቀርፈን ግብም ማስቆጠር ችለናል፡፡ በተቃራኒ ቡድን በኩል ደግሞ በተደጋጋሚ ሰአት ለማባከን ጥረት ሲያደርጉ ነበር፡፡”

ስለ ዳኝነት

“ዳኛው በተወሰነ መልኩ እራሱን ለማስከበር ሲጥር አይስተዋልም፡፡ የመሀል ዳኛው ውሳኔዎችን በሚያሳልፍ ወቅት ከበባባዎች ይበዙ ነበር በዚህም ወቅት የሚባክኑትን ደቂቃዎች አይዝም ነበር ፤ በብዙ አጋጣሚዎች ዳኛው በተጫዋቾች ይመራ ነበር፡፡”

4 Comments

  1. ድሀ መሆናችን የጎል ቴክኖሎጂ እንዳንጠቀም ስላደረገን ያገባነው ጎል ተሻረብንና በ10 ሰው ተጫውተን አቻ እንድንወጣ ተደረገ

  2. ለካስ ሰዉ ወዶ አይደለም እንግሊዝ ፕሪመየር ሊግ ሚከታተለዉ በኢትዮጵያዉያን ግማታም ዳኞች ተቃጥሎ ነዉ ለካስ

Leave a Reply