ፋሲል ከተማ ከ ወልድያ | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

​​ FT   ፋሲል ከተማ   1-0   ወልድያ  

47′ ይስሀቅ መኩርያ


ተጠናቀቀ!
ጨዋታው በፋሲል ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ፋሲል ከተማ
90+1′
ኤርሚያስ ኃይሉ ወጥቶ ሙሉቀን ታሪኩ ገብቷል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 3

የተጫዋች ለውጥ – ፋሲል
81′
አብዱልራህማን ሙባረክ በጉዳት ወጥቶ ናትናኤል ጋንጂላ ገብቷል፡፡

80′ ዳንኤል ደምሴ የመታው ቅጣት ምት በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

75′ ጨዋታው መሀል ሜዳ ላይ የተገደበ እንቅስቃሴ እየታየበት ይገኛል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ወልድያ
66′
አዳሙ መሀመድ ወጥቶ አለማየሁ ግርማ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ወልድያ
61′
ኤሪክ ኮልማን እና ሐብታሙ ሸዋለም ወጥተው ሙሉጌታ ወልደጊዮርጊስ እና ጫላ ድሪባ ገብተዋል

60′ የወልድያ ደጋፊዎች በመሀል ዳኛው ለሚ ንጉሴ ውሳኔዎች ላይ ቁጣቸውን እየገለፁ ይገኛሉ፡፡

54′ ኤርሚያስ ኃይሉ ከግብ ጠባቂው ጋር አንድ ለአንድ ተገናኝቶ የሚያስቆጭ አጋጣሚ አምክኗል፡፡

ቢጫ ካርድ
51′
ኤዶም ሆሶሮውቪ በአዳሙ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ጎልልል!!!! ፋሲል
47′ ይስሀቅ መኩርያ ከቅጣት ምት የተሻገረውን ኳስ በግንባሩ በመግጨት አስቆጥሯል፡፡ ወልድያዎች ይስሀቅ ከጨዋታ ውጪ አቋቋም ላይ ነበር በሚል ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡

ተጀመረ
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡

እረፍት!
የመጀመርያው አጋማሽ ያለ ግብ ተጠናቀቀ::

35′ በግብ ሙከራዎች መታጀብ ባይችልም ፈጣን እንቅስቃሴ እየታየ ይገኛል፡፡

34′ አንዱአለም ንጉሴ ከዮሃንስ ኃይሉ የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ ገጭቶ በግቡ አናት ሰዶታል፡፡ 

22′ ሐብታሙ ሸዋለም ከያሬድ ሀሰን የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ በመግጨት ሞክሮበግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

20′ የፋሲል ከተማ ደጋፊዎች (ካታንጋ) እና የወልድያ ደጋፊዎች (ግራ ከማን አንሼ) የስታድየሙን ጥቂት ቢሸፍኑም እጅግ አስገራሚ በሆነ ህብረት ስታድየሙን በዝማሬ እያደመቁት ይገኛሉ፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ፋሲል
15′
ሰለሞን ገብረመድህን በጉዳት ምክንያት ወጥቶ ኤፍሬመም አለሙ ተክቶት ገብቷል፡፡

9′ ኤሪክ ኮልማን ከመስመር የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ ገጭቶ ዮሃንስ ሽኩር አድኖበታል፡፡

6′ ከኄኖክ ገምተሳ የተሻገረውን ኳስ ኤዶም ሞክሮ የግቡ ቋሚን ገጭታ ወጥታለች፡፡

5′ ጨዋታው በሁለቱም ክለብ ደጋፊዎች ደማቅ ህብረ ዜማ ሞቅ ብሎ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ፋሲሎች ወደ ወልድያ የግብ ክልል በፈጣን እንቅስቃሴ እየተጠጉ ይገኛሉ፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው በፋሲል ከተማው ኤዶም ሆሶሮውቪ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡


የፋሲል ከተማ አሰላለፍ

93 ዮሀንስ ሽኩር

13 ሰኢድ ሁሴን – 14 ከድር ኸይረዲን – 16 ያሬድ ባየህ – 21 አምሳሉ ጥላሁን

26 ኄኖክ ገምቴሳ – 17 ይስሀቅ መኩርያ – 27 ሰለሞን ገብረመድህን

99 ኤርሚያስ ኃይሉ – 9 ኤዶም ኮድዞ – 18 አብዱራህማን ሙባረክ

ተጠባባቂዎች

31 ቴዎድሮስ ጌትነት

7 ፍጹም ከበደ

20 ናትናኤል ጋንጂላ

10 ሙሉቀን ታሪኩ

25 ኤፍሬም አለሙ

3 ሱሌማን አህመድ

8 ሙሉቀን አቡሀይ


የወልድያ አሰላለፍ

16 ኤሚክሪል ቢሌንጌ

3 ቢኒያም ዳርሰማ — 14 ያሬድ ዘውድነህ — 25 አዳሙ መሀመድ — 6 ዮሐንስ ኃይሉ

21 ሀብታሙ ሸዋለም – 18 ዳንኤል ደምሴ – 9 ያሬድ ሀሰን – 29 ኤሪክ ኮልማን

24 ያሬድ ብርሃኑ – 2 አንዱአለም ንጉሴ

ተጠባባቂዎች

64 ዳዊት አሰፋ

28 ታዬ አስማረ

10 ሙሉጌታ ረጋሳ

19 አለማየው ግርማ

23 ሙሉጌታ ወ/ጊዮርጊስ

15 ጫላ ድሪባ

11 በድሩ ኑርሁሴን

08:55 ተጫዋቾች አሟሙቀው ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡

08፡30 ተጨዋቾች እና ዳኞች ወደሜዳ ገብተው ማሟሟቅ ጀምረዋል ።

ያለፉት 3 ጨዋታዎች ውጤት

ፋሲል  ተሸነፈ | ተሸነፈ |ተሸነፈ
ወልድያ አቻ | ተሸነፈ | አሸነፈ

ግንኙነት

ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ ቀደም በፕሪምየር ሊጉ 1 ጊዜ ሲገናኙ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

ደረጃ

ፋሲል ከተማ በ26 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ወልድያ በ24 ነጥቦች 8ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡

ጤና ይስጥልኝ ክቡራት እና ክቡራን !

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 20ኛ ሳምንት ፋሲል ከተማ ከ ወልድያ የሚያደርጉት ጨዋታ ከአዲስ አበባ ስታድየም በቀጥታ ወደ እናንተ እናደርሳለን፡፡

መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *