የአሰልጣኞች አስተያየት | ፋሲል ከተማ 1-0 ወልዲያ

ዘማሪያም ወልደጊዮርጊስ – ፋሲል ከተማ

ስለ ጨዋታው

“ጨዋታው በአጠቃላይ ጥሩ የሚባል ነበር፡፡ በሁለተኛው ዙር በተከታታይ ሶስት ጨዋታዎች በመሸነፋችን ጫናዎች ነበሩብን፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በውስን የቡድን ስብስብ እንጫወት ስለነበር ተጫዋቾቻችን ላይ የተወሰኑ ጫናዎች ነበሩ፡፡ ከተከታይ ሽንፈቶች በኃላ በመሀል የግድቡ ጨዋታ መኖሩ ለቡድናችን ተጫዋቾች እረፍት እንድንሰጥ እድል ሰጥቶናል፡፡ በዛሬው ጨዋታ ላይ ተጋጣሚያችን ኳስን ተቆጣጥሮ በመጫወት ረገድ እንደማይበልጡን ስለሚያውቁ በይበልጥ የሀይል አጨዋወትን በመተግበር ሶስት ተጫዋቾቻችን ላይ ጉዳት ሊያደርሱብን ችለዋል ፤ እንደ አጠቃላይ በጨዋታው ላይ ማሸነፍ ይገባን ነበር፡፡”

በቀጣይ ከፋሲል ከተማ ስለሚጠበቀው ነገር

“የዛሬው ጨዋታ ውጤት የፋሲል ከተማ ለማንሰራራት በሚያደርገው ጥረት እንደ መነሻ የሚሆን ነው፡፡ በቀጣይ በመጀመሪያ ዙር የነበሩብንን ክፍተቶችን አስተካክለው ከዚህ ቀደም ወደ ነበርንበት ተፎካካሪ ቡድኖች ውስጥ በእርግጠኝነት እንቀላቀላለን፡፡”

ንጉሴ ደስታ – ወልዲያ

ስለ ጨዋታው

“የዛሬውን ጨዋታ ሽንፈት ለመቀበል ትንሽ አስቸጋሪ ነው፡፡ በመጀመሪያው አጋማሽ እኛ የተሻልን ነበርን፡፡ ነገርግን ግቦችን ማስቆጠር አልቻልንም፡፡ በሁለተኛው አጋማሽም ጥሩ መንቀሳቀስ ብንችልም በድንገት ባስተናገድናት ግብ ተሸንፈናል፡፡”

በቀጣይ ከወልዲያ ስለሚጠበቀው ነገር

“ቡድናችን በዘንድሮው የውድድር አመት ሊጉን እንመቀላቀሉ በዘንድሮው አመት በእቅዳችን መሠረት በሊጉ ለመቆየት ከፍተኛ ጥረት እናደርጋለን፡፡ በቀጣይ አመት ደግሞ ጠንክረን ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን ጥረት እናደርጋለን፡፡”

1 Comment

Leave a Reply