አዳማ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

 FT   አዳማ ከተማ   1-0   ቅዱስ ጊዮርጊስ  

81′ ዳዋ ሁቴሳ


ተጠናቀቀ !!

ጨዋታው በአዳማ ከተማ 1 – 0 አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በተከታታይ ጨዋታዎች ሲሸነፍ አዳማ አሁንም በሜዳው የማይደፈር ሆኗል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 2

89′ ዳዋ ሁቴሳ የጎል መጠናቸውን ሊያሰፋ የሚችልበትን አጋጣሚ አመከነ፡፡

88′ ፈረሰኞቹ የአቻ ጎል ለማግኘት ይህ ነው የሚባል የጎል ሙከራ ማድረግ አልቻሉም፡፡ በአንፃሩ አዳማዎች ጠንካራ መከላከል በማድረግ ውጤታቸውን ለማስጠበቅ እየተጫወቱ ይገኛሉ።

የተጨዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
84′
ዘካርያስ ቱጂ ገብቶ አቡበከር ሳኒ ወጥቷል።

ጎልልልል!! አዳማ ከተማ!!!!
81′ ተቀይሮ የገባው ዳዋ ሁቴሳ በግንባሩ ገጭቶ በቀድሞ ክለቡ ላይ ግሩም ጎል አስቆጠረ፡፡

የተጨዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
77′ አዳነ ግርማ ወጥቶ ያስር ሙገርዋ ገብቷል፡፡

73′ አዳማዎች ከርቀት በሚሞከሩ ኳሶች የጊዮርጊስን በር እየፈተሹ ይገኛሉ፡፡ ጨዋታው በከፍተኛ የደጋፊዎች ያልተቋረጠ ድጋፍ እና በአዳማዎች የበላይነት ቀጥሏል ።

የተጨዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
71′ አቡድልከሪም ኒኪማ ወጥቶ ራምኬሎ ሎክ ገብቷል። 

70′ አዳማዎች እንደምንም ተረባርበው የመቱት ኳስ የግቡ አግዳሚ መልሶባቸዋል። ጨዋታው ተጋግሎ ቀጥሏል ።

የተጨዋች ለውጥ – አዳማ
69′ ታፈሰ ተስፋዬ ወጥቶ ቡልቻ ሹራ ገብቷል፡፡

ቢጫ ካርድ !
ናትናኤል ዘለቀ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

67′  ሱራፌል ዳኛቸው ከርቀት መሬት ለመሬት አክርሮ የመታውን ኳስ ፍሬው ጌታሁን እንደምንም ተወርውሮ አዳነው። አዳማዎች የመሬቱን በዝናብ መራስ ተከትሎ ከርቀት ኳሶችን እየሞከሩ ይገኛሉ።

62′ ከርቀት የተገኘውን ቅጣት ምት ዳዋ ኡቲሳ መተቶ ፍሬው ጌታሁን ተፍቶ አወጣው። አዳማዎች ጫና ፈጥረው እየተጫወቱ ይገኛሉ።

የተጨዋች ለውጥ – አዳማ
59′ ዳዋ ሆቲሳ ገብቶ ሚካኤል ጆርጅ ወጥቷል፡፡

55′ እስካሁን ባለው የሁለቱም ቡድኖች እንቅስቃሴ በቀረው ደቂቃዎች የሚፈጠረው ነገር ባይታወቅም ከሚፈጥሩት የማጥቃት አጨዋወት አንፃር እና ሁለቱም ቡድኖች ካላቸው ጠንካራ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋቾች እንዲሁም የአየር ጠባዩ አስቸጋሪነት አኳያ ጨዋታው በአቻ ውጤት የሚጠናቀቅ ይመስላል።

50′ ለሁለቱም ቡድኖች ሜዳው በዝናብ ምክንያት ኳስ ሲነጥር እያፈጠነ እንደ ልብ አሸራሽሮ ለመጫወት አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል።

ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በከባድ ዝናብ ታግዞ ተጀምሯል ። 


እረፍት !
በመጀመርያው አጋማሽ ያለ ምንም ግብ ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 1

ቢጫ ካርድ!
43′ ሱሌማን ማህመድ አቡዱልከሪሚ ኒኪማ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል።

36′ በአዳማ የቀኝ መስመር በኩል አቡበከር ሳኒ በሚገኘው ቀዳዳ ጎል ለማግባት ጥረት እያደረገ ሲሆን አዳማዎች በግራ መስመር በተደጋጋሚ በሱራፌል ዳኛቸው እና ሱማሌማን መሀመድ አማካኝነት ተጭነው እየተጫወቱ ነው።

32′ አበባው ቡጣቆ ከግራ መስመር ያሻገረውን ምንተስኖት አዳነ በግምባሩ ገጭቶ ጃኮ አዳነበት፡፡ የፈረሰኞቹ የመጀመርያ ለጎል የቀረበ ሙከራ!

31′ በሁለቱም ቡድኖች መካከል ተመጣጣኝ የሆነ እንቅስቃሴ እያደረጉ ቢሆንም በተደጋጋሚ በሚሰሩ ጥፋቶች ጨዋታው እየተቆራረጠ ይገኛል።

ቢጫ ካርድ!
28′
አዳነ ግርማ የጨዋታውን የመጀመርያ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

27′ ሦስት ጨዋታ የተቀጣው ፋሲካ አስፋው እና በጉዳት ያልተሰለፈው ብሩክ ቀልቦሬ አለመኖር የአዳማን የአማካይ ስፍራ ሲያሳሳው በፈረሰኞቹ በኩል የባሀይሉ አሰፋ አለመኖር የማጥቃት አማራጫቸውን ቀንሶታል፡፡

20′  ከቆሙ ኳሶች በሚላኩ ኳሶች አዳማዎች ከሚፈጥሩት የማጥቃት አጋጣሚ ውጭ እንደወሰዱት የጨዋታ ብልጫ ጠንካራ ሙከራ ማድረግ አልቻሉም፡፡ በአንፃሩ ፈረሰኞቹ ባልተረጋጋና ባልተደራጀ የጨዋታ እንቅስቃሴ ኳሶች እየባከኑባቸው ይገኛሉ፡፡

14′ አዳማዎች በሱራፌል ዳኛቸው አማካኝነት በተደጋጋሚ ወደ ጎል በመድረስ ጫና እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡

10′ አዳማዎች ከግራ መስመር ያገኙትን ቅጣት ምት ሱራፌል ዳኛቸው በቀጥታ መትቶ ፍሬው ጌታሁን እንደምንም አወጣው፡፡

5′ በኳስ ቁጥጥሩም ሆነ በጨዋታ እንቅስቃሴ ባለሜዳዎቹ አዳማዎች ብልጫ ወስደው ሲጫወቱ ፈረሰኞቹ በጥንቃቄ ውስጥ የሚገኙ አጋጣሚዎችን ለመጠቀም ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

ተጀመረ !

ጨዋታው በሳላዲን ሰይድ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡


የአዳማ ከተማ አሰላለፍ

1 ጃኮ ፔንዜ

20 ሞገስ ታደሰ – 17 ሙጂብ ቃሲም– 5 ተስፋዬ በቀለ – 11 ሱሌይማን መሀመድ

7 ሱራፌል ዳኛቸው – 21 አዲስ ህንፃ – 22 ደሳለኝ ደባሽ – 13 ሲሳይ ቶሊ

9 ሚካኤል ጆርጅ – 10 ታፈሰ ተስፋዬ

ተጠባባቂዎች

29 ጃፋር ደሊል
6 እሸቱ መና
24 ሱሌይማን ሰሚድ
12 ዳዋ ሁቴሳ
14 በረከት ደስታ
18 ቡልቻ ሹራ


የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ

1 ፍሬው ጌትነት

2 ፍሬዘር ካሳ – 13 ሳላዲን በርጊቾ – 15 አስቻለው ታመነ – 4 አበባው ቡታቆ

26 ናትናኤል ዘለቀ – 23 ምንተስኖት አዳነ

27 አብዱልከሪም ኒኪማ – 19 አዳነ ግርማ – 18 አቡበከር ሳኒ

7 ሳላዲን ሰኢድ

ተጠባባቂዎች

22 ዘሪሁን ታደለ
12 ደጉ ደበበ
21 ተስፋዬ አለባቸው
10 ራምኬል ሎክ
3 መሀሪ መና
24 ያስር ሙገርዋ
20 ዘካርያስ ቱጂ

08:35 የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው ደጋፊ በአበበ በቂላ ስታድየም የታደመ ሲሆን የጥላ ፎቁን ግማሽ ቦታ ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች ላይ የፈረሰኞቹ ደጋፊዎች በብዛት ይገኛሉ

08:30 የሁለቱም ቡድኖች ተጨዋቾችና ዳኞች ወደ ሜዳ በመግባት እያሟሟቁ ይገኛሉ፡፡

የዕለቱ ዳኞች 

ዋና ዳኛ  –ኢንተርናሽናል አርቢቴር አማኑኤል ኃይለስላሴ

ረዳቶች – ተመስገን ሳሙኤል (ኢንተርናሽናል) ፣ ቦጋለ አበራ (ፌዴራል) 

አራተኛ ዳኛ – በፀጋው ሽብሩ  (ፌዴራል)

ኮሚሽነር – ፍስሀ ገብረማርያም 


ጤና ይስጥልን!


የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 20ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ካሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ እየተካሄዱ ይገኛሉ ። ዛሬም በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም 9፡00 ላይ አዳማ ከተማ የሊጉን መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስን የሚያስተናግድ ይሆናል። ይህንን በሊጉ የዋንጫ ፉክክር ላይ ቀጥተኛ ተፅእኖ ያሳድራል ተብሎ የሚጠበቀውን ጨዋታም ሶከር ኢትዮጵያ በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ከአዳማ ታደርስዎታለች፡፡ ጨዋታው እስኪጀምር ድረስ ያዘጋጀነውን ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ እያነበባችሁ እንድትቆዩ እንጋብዛለን፡፡

ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ – በዮናታን ሙሉጌታ


ቦታ
– አዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም

ቀን – ረቡዕ መጋቢት 20 2009ዓ.ም

ሰአት – 09፡00

ዳኛ – ኢንተርናሽናል ዳኛ – አማኑኤል ኃይለስላሴ

ስርጭት – ቀጥታ የጽሁፍ ስርጭት በሶከር ኢትዮጵያ

በመጀመሪያው ዙር ከነበረው አቋም አንፃር አዳማ ከተማ አሁን ላይ በመጠኑ ከዋንጫ ፉክክሩ የራቀ ይመስላል ። ሆኖም ግን አሁንም ቢሆን የሰበሰበው ነጥብ ከሊጉ መሪ እና ከዛሬ ተጋጣሚው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ አራት ብቻ ዝቅ ያለ በመሆኑ ክለቡ አሁንም የሻምፒዮነንት ዕድሉ እጁ ላይ ነው ብሎ መናገር ያስችላል ። በተለይም በዚህ ጨዋታ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ መግጠሙ ለአዳማዎች የጨዋታውን ትርጉም ከፍ ያደርገዋል ። ማሸነፍ ከቻሉም በመሀላቸው ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አንድ ዝቅ ከማድረግ ባለፈም መሪው ያለበት ነጥብ ላይ እንዲቆይ ማድረግ የሚያስችል በመሆኑ ለባለሜዳው ቡድን የዘንድሮ ጉዞ ወሳኝ ነጥብ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል ። 

ባሳለፍነው ሳምንት በኮንጎው ሊዮፓርድስ ላይ ጣፋጭ ድል ባስመዘገበ ማግስት በሊጉ በመከላከያ የተሸነፈው ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ቀሪ ጨዋታ እያለው ሊጉን መምራቱን ቀጥሏል ። ፈረሰኞቹ የዛሬውን ጨዋታ አሸንፈው በቶሎ ወደ ድል መመለስ የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ጨዋታዎች ከመጀመራቸው አስቀድሞ በሊጉ አናት ላይ የሚኖራቸውን ቦታ በማስከበር ከተፎካካሪዎቻቸው ጋር የሚኖራቸውን የነጥብ ልዩነት ለማስፋት የሚረዳቸው ነው የሚሆነው ። ጨዋታውም ከሜዳ ውጪ የሚደረግ እና በቅርብ ርቀት ላይ እየተከተላቸው ካለ ክለብ ጋር የሚያገናኛቸው በመሆኑ ወሳኝነቱን የሚያጎላው ነው የሚሆነው።


የጨዋታ አቀራረብ እና ተጠባቂ ነጥቦች

አዳማ ከተማ ዛሬ ቅዱስ ጊዮርጊስን ያሚያስተናግድበት ጨዋታ በሊጉ በሜዳው የሚያደርገው አስረኛ ጨዋታ ነው። በእስካሁኖቹ ዘጠኝ ጨዋታዎችም ሁለት ጊዜ አቻ ከመውጣቱ በቀር ቀሪዎቹን ሰባት ጨዋታዎች ማሸነፍ ችሏል ። ከዚህም በላይ በዘጠኙ ጨዋታዎች መረቡ የተደፈረው ሶስት ጊዜ ብቻ ነው ። በአጠቃላይ የዘንድሮው ውድድርም አዳማ ዝቅተኛ የግብ መጠን (9) የተቆጠረበት ክለብ መሆኑን ስናስብ እስካሁን ለሰበሰባቸው ነጥቦች የመከላከል ጥንካሬው ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳደረገለት መረዳት ይቻላል ። በተቃራኒው ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ በሊጉ በርካታ ግቦችን በማስቆጠር ቀዳሚው ክለብ ነው ። ቅዱስ ጊዮርጊስ በ 18 ጨዋታዎች 31 ግቦችን ማስቆጠሩ ብቻ ሳይሆን ከአጥቂ ስፍራ ተሰላፊዎች ውጪ ከሌሎቹም ተጨዋቾች ግቦችን ማግኘት መቻሉ ለቡድኑ የዘንድሮ ውጤት አንዱ ጠንካራ ጎን ነው ። በዚህም መስረት የዛሬው ጨዋታ ጠናካራ የትከላካይ መስመር ባለቤት የሆነውን አዳማ ከተማን በርካታ ግቦችን የማስቆጠር አቅም ከተላበሰው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሚያገናኝ ይሆናል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ በቅርብ ጊዜ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ላይ በርከት ያሉ ግቦችን እያስቆጠረ የነበረ መሆኑ የቡድን ወቅታዊ ጥሩ ጎን ቢሆንም ዘንድሮ ወደኋላ  አፈግፍገው በመጠቅጠቅ እና መከላከልን መሰረት በማድረግ የሚጫወቱ ቡድኖች ላይ ግብ ማስቆጠር ሲቸገር ተመልክተነዋል ። ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ዙርበም በተገናኙበት ወቅትም አዳማዎች የቅዱስ ጊዮርጊስን የመስመር ጥቃት ተቋቁመው ግብ ሳይስተናገድባቸው መውጣት ችለው ነበር ። በዛሬውም ጨዋታ ተመሳሳይ ጥንቃቄ በማድረግ እና ከፈረሰኞቹ የመሀል ክፍልም የመጨረሻ ዕድሎች እንዳይፈጠሩ ማድረግን ቅድሚያ የሚሰጡት ስትራቴጂ እንደሚሆን ይጠበቃል ። በሌላው ጎን የአዳማ ከተማ ደካማ የማጥቃት እንቅስቃሴ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጠንካራ የመከላከል መስመር ጋር ይገጥማል ። ጥሩ የተጨዋቾች ስብስብ የያዘው የአዳማዎች የአጥቂ እና የአማካይ ክፍል እስካሁን በሉጉ በጨዋታ አንድ ወይም ሁለት እንጂ ከዛ በላይ ጎሎች ማስቆጠር አልቻለም። በርካታ የግብ ዕድሎችም መፍጠር ሲቸገር ይስተዋላል፡፡


የቅርብ ጊዜ አቋም


አዳማ ከተማ
| ተሸ- አቻ-ተሸ-አሸ-አቻ

አዳማ ከትማ ባለፉት አምስት ጨዋታዎች በአንዱ ብቻ ማሸነፍ መቻሉ የሚያስገርም ነው ። ይህ ደካማ ሪኮርድ ለዋንጫ እየተፎካከረ ከሚገኝ ቡድን የሚጠበቅ ባይሆንም በደረጃ ሰንጠረዡ በጥቂቱ እንዲንሸራተት አደረገው እንጂ ከ ፉክክሩ አላስወጣውም ።በእነዚህ ጨዋታዎች ቡድኑ ግብ ማስቆጠር የቻለው ሁለት ጊዜ ብቻ መሆኑም ሌላው ለክለቡ የቅርብ ጊዜ ደካማ አቋም ማሳያ ነው ። ሆኖም በመጨረሻዎቹ ሁለት ጨዋታዎች ሽንፈትም ሆነ ጎል አለማስተናገዱ ለዛሬው ጨዋታ እንደመልካም መነሳሻነት ሊጠቅመው የሚችል ነጥብ ነው።


ቅዱስ ጊዮርጊስ
 | አቻ-አሸ-አሸ-አሸ-ተሸ

ፈረሰኞቹ የዘንድሮው ውድድር ሲጀምር በተከታታይ ሶስት ጨዋታዎች ላይ ድል ካስመዘገቡ በኋላ ተመሳሳይ የውጤት አካሄድ ያስመዘገቡት በሊጉ የመጀመሪያ ዙር መገባደጃ እና በሁለተኛው ዙር መጀመሪያ ነበር ። በእነዚህ ተከታታይ ሶስት ጨዋታዎችም 12 ግቦችን ማስቆጠራቸው የድሎቹን ዋጋ ከፍ ያደረገ ነበር ። ምንም እንኳን ከነበራቸው ሁለት ቀሪ ጨዋታዎች በአንዱ ሽንፈት ቢገጥማቸውም በመጨረሻዎቹ አምስት ጨዋታዎች የሰበሰቧቸው 10 ነጥቦች አሁን ለሚገኙበት የአንደኝነት ደረጃ ወሳኝ ነበሩ ።

የእርስበርስ ግንኙነት እውነታዎች

ሁለቱ ቡድኖች እስካሁን 31 ጊዜ በሊጉ ተገናኝተዋል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ 17 ድል በማስመዝገብ የበላይ ሲሆን አዳማ ከተማ 6 አሸንፏል፡፡ 8 ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ 43 ሲያስቆጥር አዳማ ከተማ 22 ጎሎች አስቆጥረዋል፡፡ 

አዳማ ላይ በተደረጉ 15 ጨዋታዎች ደግሞ አዳማ ከተማ 6 ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ 4 ድሎች ማስመዝገብ ችለዋል፡፡ 5 ጊዜ አቻ ሲለያዩ አዳማ 16 ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ 11 ጎሎች አስቆጥረዋል፡፡ 

በ2004 የውድድር ዘመን አአ ስታድየም ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ አዳማን 7-0 ያሸነፈበት ውጤት ከፍተኛው ሆኖ ሲመዘገብ ከዚህ ቀደም በ1997 የውድድር ዘመን ልክ እነንደ ዘንድሮው ሁሉ በተመሳሳይ 20ኛ ሳምንት አዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም ላይ ተገናኝተው ቅዱስ ጊዮርጊስ 3-0 አሸንፎ ነበር፡፡

ግምታዊ አሰላለፍ


አዳማ ከተማ (4-3-3)

ጃኮ ፔንዜ

እሸቱ መና – ምኞት ደበበ –  ተስፋዬ በቀለ –  ሲሳይ ቶሊ
አዲስ ህንፃ –  ደሳለኝ ደባሽ –  ፋሲካ አስፋው 

ዳዋ ሁቴሳ – ሚካኤል ጆርጅ –  ሙጂብ ቃሲም 

ቅዱስ ጊዮርጊስ (4-3-3)

ሮበርት ኦዶንካራ

ፍሬዘር ካሳ –  ሳላዲን በርጊቾ –  አስቻለው ታመነ – አበባው ቡታቆ

አብዱልከሪም ኒኪማ – ናትናኤል ዘለቀ –  ምንተስኖት አዳነ    

አቡበከር ሳኒ – ሳላዲን ሰይድ – ፕሪንስ ሰርቪኒሆ

1 Comment

Leave a Reply