የእሁድ አጫጭር ዜናዎች

ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኝነት 5 አሰልጣኞች በእጩነት መያዛቸውን የፌዴሬሽኑ የፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘሪሁን ቢያድግልኝ ተናግረዋል፡፡ ኃላፊው የአሰልጣኞቹን ማንነት ከመግለፅ ተቆጥበዋል፡፡

አዲሱ የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ በይፋ ስራ የሚጀምሩበት ቀን በፈረንጆቹ ሜይ 1 (ግንቦት 23) እንደሆነ ቢነገርም እስካሁን ከሃገራቸው እንዳልተመለሱ ተነግሯል፡፡ አሰልጣኙ የአሰልጣኝ ቡድናቸውን እስካሁን አላዋቀሩም፡፡

ጌታነህ ከበደ የሚጫወትበት ቢድቬትስ ዊትስ ለደቡብ አፍሪካ ኔድባንክ ዋንጫ ፍፃሜ አልፏል፡፡ ዊትስ ትላንት ምሽት በግማሽ ፍፃሜው ከካይዘር ቺፍስ ጋር በመደበኛው 90 እና ተጨማሪ ደቂቃዎች 2-2 አቻ ተለያይተው በመለያ ምቶች አሸንፈዋል፡፡ ተቀይሮ የገባው ጌታነህም ከመለያ ምቶች አንዱን መትቶ ወደ ግብነት ቀይሮታል፡፡ ዊትስ በፍፃሜው ከኦርላንዶ ፓያሬትስ ጋር ይፋለማል፡፡

በቀውስ ውስጥ ሲዳክር ቆይቶ በመጨረሻ በባለሃብቶች እጅ የገባው ሐረር ከነማ ከፍተኛ ገንዘብ አግኝቷል፡፡ የቀድሞ የክለቡ አስተዳዳሪ ሐረር ቢራ ፋብሪካ ለ2 አመት የሚሆን 16 ሚሊዮን ብር የለገሰ ሲሆን የከተማው አስተዳደር ደግሞ 10 ሚልዮን ብር (ለ2 አመት) ለክለቡ ሰጥተዋል፡፡ (ፕላኔት ስፖርት)

{jcomments on}

ያጋሩ