ሲዳማ ቡና ከ ኢትዮጵያ ቡና – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

 FT   ሲዳማ ቡና   3-1  ኢትዮጵያ ቡና 

2′ ትርታዬ ደመቀ፣ 48′ ላኪ ሳኒ፣ 66′ ሰንደይ ሙቱኩ| 43′ አቡበከር ነስሩ


ተጠናቀቀ !!

ጨዋታው በሲዳማ ቡና 3 – 1 አሸናፊነት ተጠናቋል!!  ሲዳማ ቡና ከ2003 ዓ/ም በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮዽያ ፕሪሚየር ሊግ መሪ መሆን ችሏል። 


90′ ተጨማሪ ሰዓት – 4 ደቂቃ


88′ ቢጫ !  ሲዳማ ቡና 

ኤሪክ ሙራዳ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል 


87′ አዲስ ግደይ ብቻውን ግልፅ የሆነ የጎል አጋጣሚ አግኝቶ ሳይጠቀምበት ቀረ።


79′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና 

መስዑድ መሀመድ ወጥቶ አብዱልከሪም ሀሰን ገብቷል ።


76′ የተጫዋች ለውጥ – ሲዳማ ቡና

 ኤሪክ ሙራዳ ገብቶ ላኪ ሳኒ ወጥቷል።


73′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና 

መስዑድ መሀመድ ወጥቶ እሱባለው ጌታሁን ገብቷል።


70′ የተጫዋች ለውጥ – ሲዳማ ቡና

ወሰኑ ማዜ ወጥቶ ግሩም አሰፋ ገብቷል።


66′ ጎል!!!! ሲዳማ ቡና

ከማዕዘን ምት የተሻገረውን ኳስ በግንባሩ ሰንደይ ሙቱክ አስቆጥሮ የሲዳማን ግብ ወደ ሶስት ከፍ አድርጓል።


65′ ሙሉአለም መስፍን በግሩም ሁኔታ የኢትዮጵያ  ቡና ተከላካዮችን አልፎ የመታውን ኳስ ሀሪሰን አውጥቶበታል።


59′ አንተነህ ተስፋዬ ወደ ግብ የመታውን ኳስ ሀሪስን እንደምንም አውጥቶታል።


56′ ትርታዬ ደመቀ ከላኪ ጋር ተቀባብሎ የገባውን ኳስ በመጨረሻ ላኪ አግኝቷት የሲዳማን ግብ ከፍ የሚያደርግ አጋጣሚን ሳይጠቀምበት ቀረ።


52′ አህመድ ረሺድ ላኪ ላይ በሰራው ጥፋት ቢጫ ካርድ ተመልክቷል።


49′ ላኪ ግቧን አስቆጥሮ ልብሱን በማውለቁ ቢጫ ተመልክቷል።


48′ ጎል!!!! ሲዳማ ቡና

ፍፁም ተፈሪ ከመሀል ሜዳ በረጅሙ  የሰጠውን ኳስ ላኪ ሳኒ ተቆጣጥሮ የወንዲፍራው ጌታሁንን ስህተት በመጠቀም ሁለተኛ ግብ ለሲዳማ ቡና አስቆጠረ።


48′ ላኪ ሳኒ በቀጥታ ወደ አምስት ከሃምሳ ውስጥ ገብቶ ወደ ግብ የመታት ኳስ ለጥቂት ወጥታለች።


ሁለተኛው አጋማሽ  በሲዳማ ቡናዉ ላኪ ሳኒ አማካኝነትን ተጀምሯል።


እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡


45′ አዲስ ግደይ ተደጋጋሚ ሙከራዎችን በማድረግ የኢትዮጵያ ቡናን ተከላካይ መስመር እያስጨነቀ ይገኛል፡፡


ቢጫ ካርድ
44′ አዲስ ግደይ የደኛን ውሳኔ በመቃወም የቢጫ ካርድ ተመልክቷል፡፡


ጎልልል!!!! ኢትዮጵያ ቡና
43′ መስኡድ መሀመድ ከማዕዘን ምት ያሻማውን ኳስ የመጀመሪያ የሊግ ጨዋታውን እያደረገ የሚገኘው አቡበከር ነስሩ በግንባሩ በመግጨት አስቆጥሮ ኢትዮጵያ ቡናን አቻ አድርጎል፡፡


የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና
41′ ኤልያስ ማሞ ጉዳት አጋጥምት ተቀይሮ ሲወጣ አክሊሉ ዋለልኝ ተክቶት ወደ ሜዳ ገብቷል፡፡


40′ ወሰኑ ማዜ በረጅሙ  ያሻገረውን ኳስ አዲስ ግደይ በፍጥነት ደርሶ በግንባር  ገጭቶ ቢሞክርም ሀሪስን ይዞበታል፡፡


38′ ላኪ ሳኒ ከወሰኑ ማዜ የተላከለትን ኳስ አገባው ሲባል ኤፍሬም ወንድወሰን በአስደናቂ  ሁኔታ ከኃላው ነጥቆታል፡፡


34′ ኤልያስ ማም እና አህመድ ረሺድ በተመሣሣይ ቦታ ከሲዳማ ቡና ተከላካዮች ጋር ተጋጭተው ጉዳት አጋጥሟቸው ህክምና እርዳታ ከተደረገላቸው በኋላ ጨዋታው ቀጥሏል፡፡


30′ አቡበከር ነስሩ ከርቀት በቀጥታ ወደ ግብ የመታውን ኳስ ለአለም በቀላሉ ይዞበታል፡፡


27′ እያሱ ታምሩ ከመስመር ያሻገረውን በሲዳማ ቡና ተከላካዮች ስትመልስ አብዱልከሪም አግኝቷት አንተነህ ተስፋዬ በድንቅ ሁኔታ ቀምቶታል፡፡


22′ ጨዋታው የተቀዛቀዘ መልክ ይዟል፡፡ ሁለቱም ክለቦች በጥንቃቄ የታጠረ አጨዋወትን እየተከተሉ ይገኛሉ፡፡


15′ ሲዳማ ቡናዎች ተደጋጋሚ ጥቃቶችን በኢትዮጵያ ቡና ላይ እየሰነዘሩ ይገኛል፡፡
4′ አዲስ ግደይ ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ላኪ ሳኒ አግኝቶት ሁለተኛ ግብ የሚሆን አጋጣሚን ሳይጠቀምበት ቀረ፡፡ጎልልል!!!! ሲዳማ ቡና!!!
2′ ትርታዬ ደመቀ ገና ጨዋታው በተጀመረ በ2ኛው ደቂቃ ከላኪ ሳኒ የተሻገረለትን ኳስ ወደ ግብ በመቀየር ሲዳማ ቡናን መሪ አድርጓል


ተጀመረ!
ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡናው ሳሙኤል ሳኑሚ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡


የሲዳማ ቡና አሰላለፍ

24 ለአለም ብርሃኑ

15 ሳውሬል ኦልሪሽ– 21 አበበ ጥላሁን — 4 አንተነህ ተስፋዬ – 22 ወሰኑ ማዜ

20 ሙሉአለም መስፍን — 8 ትርታዬ ደመቀ — 5 ፍፁም ተፈሪ –  32 ሳንደይ ሙቱኩ

14. አዲስ ግደይ — 27 ላኪ ሳኒ


ተጠባባቂዎች

1 ፍቅሩ ወዴሳ

12 ግሩም አሰፋ 

23 ሙጃኢድ መሀመድ

19. አዲስአለም ደበበ

10 አብይ በየነ

13 ኤሪክ ሙራንዳ

29 አዲሱ ተስፋዬ


ኢትዮጵያ ቡና አሰላለፍ

99 ሀሪሰን ሄሱ 

15 አብዱልከሪም መሀመድ – 16 ኤፍሬም ወንድወሰን – 5 ወንድይፍራው ጌታሁን -13  አህመድ ረሺድ

8 አማኑኤል ዩሀንስ – 3 መስኡድ መሀመድ – 9 ኤልያስ ማሞ

14 እያሱ ታምሩ – 10 አቡበከር ናስር 11 ሳሙኤል ሳኑሚ 

ተጠባባቂዎች

50 ጁቤድ ኡመድ

19 አክሊሉ ዋለልኝ

17 አብዱልከሪም ሀሰን 

18 ሣለምላክ ተገኝ 

7 ሳዲቅ ሴቾ 

20 እሱባለው ጌታሁን 

21 አስናቀ ምገስ

08:20 የሁለቱም ክለቦች ደጋፊዎች በስታድየሙ ለክለቦቻቸው ህብረ ዝማሬ እያሰሙ ይገኛል፡፡

ዳኛ

ይህንን ጫወታ ኢንተርናሽናል ዳኛ በላይ ታደሰ ይመሩታል፡፡ 

ደረጃ

ሲዳማ ቡና በ33 ነጥቦች 4ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ኢትዮጵያ ቡና በ32 ነጥቦች 5 ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

ያለፉት 3 ጨዋታዎች አቋም

ሲዳማ ቡና | አሸነፈ | አቻ | ተሸነፈ

ኢትዮጵያ ቡና
| አሸነፈ | አሸነፈ | አቻ

የእርስ በእርስ ግንኙነት

ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ እስካሁን 15 ጊዜ ተገናኝተዋል፡፡ ሲዳማ 6 ጨዋታ በማሸነፍ ቀዳሚ ሲሆን ቡና 5 አሸንፏል፡፡ 5 ግንኙነቶች ደግሞ በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል፡፡ ሲዳማ ቡና 17 ፣ ኢትዮጵያ ቡና 19 ግቦች ሲያስቆጥሩ በመጀመርያው ዙር አአ ስታድየም ላይ ቡና 2-1 አሸንፎ ነበር፡፡

ሰላም ክቡራት እና ክቡራን !

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 20ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሀ ግብር በሲዳማ ቡና እና ኢትዮጵያ ቡና መካከል ሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስታድየም ላይ በ09:00 ይካሄዳል፡፡ ሶከር ኢትዮጵያም የጨዋታውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ወደ እናንተ የምታደርስ ይሆናል፡፡

መልካም ውሎ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር!

11 Comments

  1. የተቃጠለ ነገር ይሸተኛል
    የታባቱ ምድረ ዱርዬ አበደ ዛሬ!!!

    1. ባለፉት ሁለት ጫወታዎች የነበረውን ጭሳጭስ ስናስበው እና ከሙስና ኪሳራ ስናነጻጽረው . . .

  2. Gooooooooooooooooooooooooooooooooooooaaaaaaaaaaaaaaaaaaal Ethiopia Buna . . .

  3. መልካም እድል ፍቅር ለሆነው ክለባችን ኢትዮጵያ ቡናችን!

Leave a Reply