የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ 15ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታዎች ትላንት እና ዛሬ ሲካሄዱ ሀዋሳ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በ09:00 ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲን የገጠመው ሀዋሳ ከተማ 4-2 በማሸነፍ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን መከተሉን ቀጥሏል፡፡ ሀዋሳ በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ የተሻለ እንቅስቃሴን ማድርግ የቻለ ሲሆን ሮማን ጌታቸው አክርርራ የመታችው ኳስ በቅድስት ማርያሟ ተከላካይ ወለላ ባልቻ ተጨርፎ ቀዳሚ መሆን ችሏል፡፡ ከጎሉ መቆጠር በኋላም ጫና ፈጥረው መጫወት የቻሉት ሀዋሳ ከተማዎች በአይናለም አሳምነው ግሩም ጎል መሪነታቸውን ወደ ሁለት ማስፋት ችለዋል፡፡ መዲና አወል የግብን ልዩነቱን የሚያጠብ ግብ ብታስቆጥርም ምርቃት ፈለቀ ለሀዋሳ አስቆጥራ በሀዋሳ የ3-1 መሪነት መጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል፡፡
ከዕረፍት መልስ ቅድስት ማርያም የተሻለ መንቀሳቀስ ሲችሉ የተሰጠውን የፍጹም ቅጣት ምት አምበሏ ማህሌት ታደሰ አስቆጥራ ቅድስት ማርያምን ወደ ጨዋታው መመለስ ብትችልም አይናለም አሳምነው በ87ኛው ደቂቃ የውድድር ዘመኑ 20ኛ የሊግ ግቧን አስቆጥራ ጨዋታው በሀዋሳ ከተማ 4-2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
[table id=232 /]
[league_table 18073]
በምድብ ሀ ረቡዕ ሊካሄድ ፕሮግራም ወጥቶለት በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ወደ ትላንት ጠዋት የተሸጋገረው የድሬዳዋ ከተማ እና ጥረት ኮርፖሬት ጨዋታ በድሬዳዋ 1-0 አሸናፊነት ተደምድሟል፡፡ ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ በታየበት ጨዋታ ትደግ ፍስሀ በ17ኛው ደቂቃ ያስቆጠረችው ግብ ድሬዳዋን ለድል አብቅቷል፡፡
[table id=242 /]
[league_table 18083]