አዲስ አበባ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

 FT  አዲስ አበባ ከተማ   1-1  አርባምንጭ ከተማ 

63′ ዳዊት ማሞ 65′ ገ/ሚካኤል ያዕቆብ


ጨዋታው በ1 ለ 1 አቻ ውጤት ተጠናቀቀ !

90′ ጭማሪ ደቂቃ 4 !

88′ የተጨዋች ቅያሪ አርባ ምንጭ ከተማ

ገ/ሚካኤል ያዕቆብ እና ታደለ መንገሻ ወጥተው ወንድሜነህ ዘሪሁን እና ታሪኩጎጀሌ ገብተዋል።

88′ ጀምስ ኩዋሜ በግራ መስመር ሰብሮ በመግባት ከላከው ኳስ ባማነሳት ዳዊት ማሞ ከሳጥኑ ጠርዝ ላይ አክሮ ቢመታም ጃክሰን ፊጣ በሚገርም ቅልጥፍና አድኖበታል ።

86′ ተቀይሮ የገባው ጀምስ ኩዋሜ በግባሩ ያሞከረው ኳስ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል ።

80′ ከብርሀኑ አዳሙ የተሞከረውን ኳስ ትክለማርያ ሲተፋው ገ/ሚካኤል ከቅርብ ርቀት አግኝቶ አገባው ሲባል ወደላይ ሰዶታል ።

79′ የተጨዋች ለውጥ አዲስ አበባ ከተማ 

ፍቃዱ አለሙ በምንያምር ጴጥሮስ እንዲሁም እንዲሁም ዳንኤል አባተ በጀምስ ኩዋሜ ተቀይረው ወጥተዋል ።

76′ ዳንኤል አባተ ከ አዲስ አበባ የመጃመሪያውን የቢጫ ካርድ ታመልክቷል ።

75′ ከግራመስመር የተገኘውን ቅጣት ምት ፍቃዱ አለሙ ሲመታ በአርባምጭ ተከላካዮች ተጨርፎ ወደግብ ክልል ቢያመራም የአዲስ አበባ ተጨዋቾች ዕድሉን መጠቀም አልቻሉም ።

68′ የተጨዋች ለውጦች

አዲስ አበባ ከተማ

እንየው ካሳሁን አሊ አያናን ተክቶ ወደ ሜዳ ገብቷል ።

አርባምንጭ ከተማ
ዐመለ ሚልኪያስ በ ብርሀኑ አዳሙ ተቀይሮ ወጥቷል ።

65′ ጎል አርባምንጭ ከተማ ገ/ሚካኤል ያዕቆብ !

ከመስመር የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ በመግጨት የፊት አጥቂው ገ/ሚካኤል አርባምንጭን አቻ አድርጓል ።

63′ ጎል አዲስ አበባ ከተማ ዳዊት ማሞ !

ፍቃዱ አለሙ ከግብ ጠባቂው ጋር ተገናኝቶ ከግራ በኩል መሀል ላይ ለሚገኘው ኃይሌ እሸቱ የላከውን ኳስ ተከላካዮች በአግባቡ ሳያወጡት ቀርተው ዳዊት አግኝቶ በቀጥታ በመምታት የመጀመሪያውን ጎል አስቆጥሯል ።

59′ አርባ ምንጮች በቀኝ መስመር የሰነዘሩት ጥቃት ወደግራ መስመር አምርቶ ከግራ በኩል ታደለ መንገሻ ያሻማውን ኳስ ዐመለ ሚልኪያስ በግንባሩ ቢገጪም ለጥቂት ወደውጪ ወጥቶበታል ።

47′ ታደለ መንገሻ ሳጥን ውስጥ ገብቶ የሞከረውን ኳስ ተክለማርያም ይዞበታል፡፡ የመጀመርያ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ

ተጀመረ
ሁለተኛው አጋማሽ ተጀምሯል፡፡

ዕረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ ያለ ግብ ተጠናቋል

40′ ሙሀጅር መኪ ከቅጣት ምት የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

36′ አመለ ሚልኪያስ ከቀኝ መስመር አክርሮ የመታው ኳስ በግቡ ቋሚ ለጥቂት ወጥቷል፡፡

30′ ጨዋታው በመሀል ሜዳ የተገደበ እና ወጥነት የሌለው ቅብብል ያመዘነበት እንቅስቃሴ እያስተናገደ ይገኛል፡፡

20′ አርባምንጭ በኳስ ቁጥጥር የበላይ ቢሆንም የግብ እድል መፍጠር አልቻሉም፡፡

15′ ከማዕዘን ምት የተሻማውን ኳስ ገብረሚካኤል በግንባሩ ገጭቶ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡ አርባምንጭ ከተማዎች የተሻለ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡

13′ ታደለ መንገሻ ከግራ መስመር ሳጥን ጠርዝ የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

*የአርባምንጭ ከተማ ደጋፊዎች በካታንጋ ሰብሰብ ብለው ቡድናቸውን እያበረታቱ ይገኛሉ፡፡

ተጀመረ
ጨዋታው በአርባምንጭ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡

አዲስ አበባ ከተማ አሰላለፍ

1 ተክለማርያም ሻንቆ

27 ዳንኤል አባተ – 20 ሰይፈ መገርሳ – 6 ጊት ጋትኮች – 80 አዳነ በላይነህ

 13 ዘሪሁን ብርሃኑ 

70 አሊ አያና – 30 መሀጅር መኪ – 40 ዳዊት ማሞ 

24 ፍቃዱ አለሙ – 8 ኃይሌ እሸቱ

ተጠባባቂዎች

98 ደረጄ አለሙ

7 ምንያምር ጴጥሮስ

77 አማረ በቀለ

50 ከንአን ማርክነህ

83 ፀጋ አለማየሁ

10 ጀምስ ኩዋሜ

2 እንየው ካሳሁን

የአርባምንጭ ከተማ አሰላለፍ

99 ጃክሰን ፊጣ

14 ወርቅይታደል አበበ – 5 አንድነት አዳነ – 15 ተመስገን ካስትሮ – 2 ተካልኝ ደጀኔ

7 እንዳለ ከበደ – 8 አማኑኤል ጎበና – 20 ወንድወሰን ሚልኪያስ – 17 ታደለ መንገሻ

12 አመለ ሚልኪያስ – 19 ገብረሚካኤል ያዕቆብ

ተጠባባቂዎች

70 ፅዮን መርዓድ

6 ታሪኩ ጎጀሌ

4 ምንተስኖት አበራ

10 ወንድሜነህ ዘሪሁን

25 አለልኝ አዘነ

16 ታሪኩ ኮራት

29 ብርሀኑ አዳሙ

10:00 ተጫዋቾች አሟሙቀው ወደ መልበሻ ክፍል ተመልሰዋል፡፡

09:30 በአሁኑ ሰአት ሜዳው የከፍተኛ ሊግ ጨዋታ እየተካሄደበት በመሆኑ የሁለቱም ቡድን ተጫዋቾች በሜዳው ጠርዝ እየያሟሟቁ ይገኛሉ፡፡

ደረጃ
አዲስ አበባ ከተማ በ15 ነጥቦች 15ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ አርባምንጭ ከተማ በ28 ነጥቦች 7ኛ ላይ ተቀምጧል፡፡

ያለፉት 3 ጨዋታዎች አቋም
አአ ከተማ | አቻ | አቻ | አሸነፈ
አርባምንጭ ከተማ | አቻ | አቻ | አሸነፈ

የእርስ በእርስ ግንኙነት
ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ አንድ ጊዜ ብቻ ተገናኝተው አርባምንጭ ከተማ በሜዳው 3-1 አሸንፏል፡፡

ሰላም ክቡራት እና ክቡራን !
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 21ኛ ሳምንት የመጀመርያ መርሀ ግብር አዲስ አበባ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ አዲስ አበባ ስታድየም ላይ በ10:00 ይካሄዳል፡፡ ሶከር ኢትዮጵያም የጨዋታውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ወደ እናንተ የምታደርስ ይሆናል፡፡

መልካም ውሎ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *