FT ቅዱስ ጊዮርጊስ 1-0 ሲዳማ ቡና
90+2 ሳላዲን ሰይድ
ጨዋታው ተጠናቀቀ ! የሳላዲን ሰይድ ጎል ቅዱስ ጊዮርጊስን ከሁለት ተከታታይ ሽንፈት በኋላ ወደድል እና ወደሊጉ መሪነት መልሳለች ።
90+3 ራምኬል ሎክ ጉዳት አስተናግዶ ከሜዳ ወጥቷል
90+2 ጎል ቅዱስ ጊዮርጊስ ሳላዲን ሰይድ !
የሲዳማ ቡና ተከላካዮችን ስህተት በመጠቀም ሳላዲን ሰይድ ባለቀ ሰዐት ከሳጥን ውስጥ ባገኘው ዕድል ድንቅ ግብ ማስቆጠር ችሏል ።
90′ ጭማሪ ደቂቃ 3 !
87′ አበባው ቡጣቆ ለመሀል ሜዳ የቀረበውን የቅጣት ምት በቀጥታ አክርሮ ሞክሮ ለጥቂት ወደውጪ ወጥቶበታል ። ግሩም ሙከራ !
83′ አዲስ ግዳይ እንደ አንተነህ ሁሉ ሌላ ደካማ ኳስ ከረጅም ርቀት ሞክሮ ሮበርት ቀለል አርጎ ይዞበታል ። አዲስ ለላኪ ሳኒ ማቀበል የሚችልበት አማራጭ ነበረው ።
81′ የተጨዋች ለውጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ያስር ሙገርዋ ምንተስኖት አዳናን ተክቶ ወደሜዳ ገብቷል ።
80′ ጊዮርጊሶች ከቀኝ መስመር ተደጋጋሚ ኳሶችን እየጣሉ ዕድል ለመፍጠር እየጣሩ ይገኛሉ ። ሲዳማዎች አሁንም ረጃጅም ኳሶችን ለላኪ ሳኒ መላካቸውን ቀጥለዋል ።
77′ ሲዳማዎች ካገኙትን ጥሩ የማጥቃት አጋጥሚ በመነሳት ሙሉአለም መስፍን በግራ በኩል ይገኝ ለነበረው አንተነህ ተስፋዬ አሳልፎለት አንተነህ ወደአጥቂዎቹ አቀብለ ተብሎ ሲጠበቀ በርቀት የሞከረውን ደካማ ኳስ ሮበርት በቀላሉ ይዞበታል ።
75′ የተጨዋች ለውጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ
አቡበከር ሳኒ ወጥቶ ራምኬል ሎክ ገብቷል ። ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታውን የጀመረባቸውን ሁለቱንም የመስመር አጥቂዎቹን ቀይሮ አስወጥቷል ።
71′ ከመሀል ሜዳ በጥቂቱ ወደ ሲዳማዎች ክልል ወደ ግራ አድልቶ የተሰጠውን የቅጣት ምት አበባው ሲያሻማ ለዐለም ለመያዝ ሞክሮ ቢተፋውም የጊዮርጊስ አጥቂዎች ሳይደርሱበት ቀድሞ መቆጣጠር ችሏል ። በዚህ መሀልም ቀላል ጉዳት አስተናግዶ የህክምና ዕርድታ ከተደረገለት በኋላ ጨዋታው ቀጥሏል ።
66′ ሲዳማዎች በባለሜዳዎቹ ሜዳ ላይ ጫና ፈጥረው እየተጫወቱ ይገኛሉ ። ተደጋጋሚ የቆሙ ኳሶችንም እያገኙ ነው ።
65′ ፍሬዘር ካሳ በአዲስ ግዳይ ላይ በሰራው ጥፋት የቢጫ ካርድ ተመልክቷል ።
64′ የተጨዋች ቅያሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ
አዳነ ግርማ በፕሪንስ ሰርቪንሆ ተቀይሮ ወደሜዳ ገብቷል ። ቅያሪውን ተከትሎ አብዱልከሪም ኒኪማ የፕሪንስን የግራ መስመር ሲይዝ አዳነ እና ምንተስኖት መሀል ሜዳ ላይ ተጣምረዋል ።
60′ ጨዋታው ተቋርጦ ከጀመረ በኋላ ቅዱስ ጊዮርጊስ አቡበከር በሚገኝበት የቀኝ መስመር አድልቶ ሲዳማ በበኩሉ ረጃጅም ኳሶችን ለላኪ እና አዲስ በማድረስ ለማጥቃት እየሞከሩ ነው ።
57′ አበባው ቡጣቆ በትርታዬ ደመቀ ላይ በገባው ከባድ ሸርተቴ ምክንያት የቢጫ ካርድ ተመልክቷል ።
55′ አዲስ ግዳይ በረጅሙ የተላከውን ኳስ ይዞ እና ግማሹን የሜዳ ክፍል አቋርጦ ሮበርት ጋር ቢደርስም ፈጥኖ መሞከር ባለመቻሉ ሮበርት አድኖበታል ።
ጨዋታው ካቆመበት ቀጥሏል ሮበርት በረጅሙ በመለጋት ጀምሮታል !!
* የስታድየሙ ፓውዛዎች ሙሉ በሙሉ መስራት ጀምረዋል ። ጨዋታውም በደቂቃዎች ውስጥ የሚጀመር ይመስላል ።
*በሚስማር ተራ በኩል ያለው ፓውዛ በከፊል በርቷል ሆኖም ሌሎቹ እንደጠፉ በመሆናቸው ጨዋታው መቀጠል አልቻለም ። ከተቋርጠም 15 ደቂቃዎች አልፈዋል ።
* ጨዋታው ከተቋረጠ ከ 10 በላይ ደቂቃዎች አልፈዋል ። ዳኞች አሰልጣኞች እና የጨዋታው ኮምሽነር እየተነጋገሩ ይገኛሉ ። ተጨዋቾችም ሜዳ ላይ እየተንቀሳቀሱ ነው ።
54′ ፓውዛዎቹ እስካሁን ተመልሰው መብራት አልቻሉም ። ጨዋታውም ተቋርጧል !
52′ ከመስመር የተሻማውን ኳስ ምንተስኖት በግንባሩ ለማስቆጠር ሞክሮ አልተሳካም ። ኳስ መሬት ከወረደች በኋላም ጊዮርጊሶች በድጋሜ ከመሞከራቸው በፊት የሲዳማ ተከላካዮች ተረባርበው አውጥተውታል ።
50′ የስታድየሙ ፓውዛዎች ጠፍተዋል ። ጨዋታው ባለው ብርሀን እንደቀጠለ ነው ።
48′ አበባው ቡጣቆ ከሲዳማ የግብ ክልል በቀኝ በኩል የተሰጠውን የማዕዘን ምት ሲያሻማለት ሳላዲን ሰይድ በግንባሩ ሞክሮ ወደላይ ወጥቶበታል ። አስደንጋጭ ሙከራ !
47′ ሀይቲያዊው አማካይ ሳውሪል ኦርሊሽ ከረጅም ርቀት የተሰጠውን የቅጣት ምት በቀጥታ ሞክሯል ። የሁለተኛው አጋማሽ የመጀመሪያ ኢላማውን ያልጠበቀ ሙከራ !
46′ በሁለቱም በኩል የተጨዋች ለውጥ አልተደረገም ።
46′ ላኪ ሳኒ ሁለተኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ አስጀምሯል ።
የመጀመሪያው አጋማሽ ያለግብ ተጠናቋል ።
45′ ጭማሪ ደቂቃ 1 !
40′ የሊጉ መሪዎች የሆኑት የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ እጅጉን ተቀዛቅዟል ። የሁለቱም ቡድኖች የኋላ መስመር ጥንካሬ ለተቃራኒ ቡድን ዕድል የሚፈጥር አልሆነም ። የፊት መስመር ተሰላፊዎችም በተደጋጋሚ ከጫወታ ውጪ እየሆኑ ነው ።
35′ ትርታዬ ደመቀ ከላኪ ሳኒ የተቀበለውን ኳስ ከቀኝ መስመር በረጅሙ ለማስቆጠር ቢሞክርም በርቀት ወደውጪ ወጥቶበታል ።
34′ ከመጀመሪያው በተሻለ ሁለቱ ቡድኖች ፈጠን ባለ እንቅስቃሴ ወደጎል እየቀረቡ ይገኛሉ ።
33′ አዲስ ግደይ የቢጫ ካርድ ተመልክቷል ። ፈጣኑ የመስመር አጥቂ ኳስ በእጅ በመንካቱ ነበር የማስጠንቀቂያ ካርዱን የተመለከተው ።
32′ ምንተስኖት አዳነ ከሳላዲን ሰይድ ጋር በአስገራሚ ሁኔታ አንድ ሁለት ተቀባብሎ ይሞክረው ግሩም ኳስ ከጫወታ ውጪ ሆኖበታል ።
28′ ጊዮርጊሶች በሲዳማ ሜዳ ላይ ኳስ ለመያዝ ዕድሎች ቢያገኙም በተሳሳቱ ቅብብሎች እያባከኗቸው ይገኛሉ ። የወትሮው አስፈሪ የመስመር ጥቃታቸውም እስካሁን ተቀዛቅዟል ።
24′ ሲዳማዎች ወደመሀል ሜዳ ተጠግቶ ካለው የቅዱስ ጊዮርጊስ ተከላካይ መስመር ጀርባ ያለውን ሰፊ ክፍተት ለመጠቀም በተደጋጋሚ ረጃጅም ኳሶችን እየላኩ ነው ሆኖም ከጫወታ ውጪ እየሆኑ እንዳሰቡት ወደ ግብ መድረስ አልቻሉም ።
20′ በጨዋታው እስካሁን በሁለቱም በኩል ያለቀላቸው የግብ ዕድሎች እየተፈጠሩ አይደለም ። አስቻለው ታመነ በአዲስ ግደይ ላይ ከሳጥን ውጪ ጥፋት ቢሰራም እንቅስቃሴው ከጨዋታ ውጪ በመሆኑ ጨዋታው በመልስ ምት ቀጥሏል ።
15′ እስካሁን ድረስ ሁለቱ ቡድኖች ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ እያደረጉ ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊሶች ሲዳማዎች በራሳቸው ሜዳ ላይ ኳስ ማደራጀት እንዳይችሉ ጫና እየፈጠሩ ለመጫወት እየሞከሩ ነው ። ሲዳማዎች በበኩላቸው ከሜዳቸው መውጣት በቻሉባቸው አጋጣሚዎች በፍጥነት ወደ ጊዮርጊሶች የግብ ክልል ለመድረስ እየሞከሩ ይገኛሉ ።
11′ ፕሪንስ ከግራ መስመር ያሳለፈለትን ኳስ ተጠቅሞ ሳላዲን ሰይድ ከለአለም ጋር አንድ ለ አንድ ተገናኝቶ ሲሞክር ከፍ ብሎ ወደውጪ ወጥቶበታል ።
8′ ፕሪንስ ላይ በቀኝ መስመር በተሰራው ጥፋት ምክንያት የተሰጠውን ቅጣት ምት አበባው ሲያሻማ ሳላዲን በግንባሩ ሞክሮ ሲዳማዎች ተደርበው አውጥተውበታል ። ጨዋታው በማዕዘን ምት ቀጥሎም ከግብ ቅርብ ርቀት ላይ ተስፋዬ ያገኘውን ኳስ አክርሮ መቶ ወደላይ ተነስቶበታል ።
4′ ላኪ ሳኒ በቀኝ መስመር ጠርዝ ላይ ወደውስጥ ብቻውን ይገኝ ለነበረው አዲስ ነጋሽ የላከውን ኳስ ሮበርት በቀላሉ ይዞበታል ።
2′ አብዱልከርም ኒኪማ ከረጅም ርቀት የመታው ኳስ በለአለም ግራ በኩል ወደውጪ ወጥቷል ።
1′ ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊሱ ሳላዲን ሰይድ አማካይነት ተጀምሯል ።
የተጨዋቾች አሰላለፍ
ቅዱስ ጊዮርጊስ
30 ሮበርት ኦዶንካራ
2 ፍሬዘር ካሳ – 15 አስቻለው ታመነ – 12 ደጉ ደበበ – 4 አበባው ቡታቆ
27 አብዱልከሪም ኒኪማ – 21 ተስፋዬ አለባቸው – 23 ምንተስኖት አዳነ
18 አቡበከር ሳኒ – 7 ሳላዲን ሰኢድ – 11 ፕሪንስ ሲቬሪንሆ
ተጠባባቂዎች
22 ዘሪሁን ታደለ
20 ዘካሪያስ ቱጂ
19 አዳነ ግርማ
24 ያስር ሙገርዋ
19 ራምኬል ሎክ
13 ሳላዲን ባርጌቾ
ሲዳማ ቡና
24. ለአለም ብርሃኑ
12 ግሩም አሰፋ– 32 ሳንደይ ሙቱኩ – 21 አበበ ጥላሁን – 4 አንተነህ ተስፋዬ
15 ሳውሬል ኦልርሺ – 20 ሙሉአለም መስፍን
8 ትርታዬ ደመቀ – 5 ፍፁም ተፈሪ– 14 አዲስ ግደይ
27 ላኪ ሳኒ
ተጠባባቂዎች
1 ፍቅሩ ወዴሳ
23 ሙጃኢድ መሀመድ
19 አዲስአለም ደበበ
13 ኤሪክ ሙራንዳ
84 ኃይለየሱስ መልካ
22 ወሰኑ ማዜ
እርስ በእርስ ግንኙነት እና እውነታዎች
ሁለቱ ክለቦች እስካሁን 15 ጊዜ በሊጉ ሲገናኙ ቅዱስ ጊዮርጊስ 10 ድል በማስመዝገብ የበላይ ነው፡፡ 5 ጊዜ አቻ ሲለያዩ ሲዳማ ቡና በፕሪምየር ሊጉ በታሪኩ ቅዱስ ጊዮርስን አሸንፎ አያውቅም፡፡
– ሁለቱ ቡድኖች 5 ጊዜ አቻ ሲለያዩ በሁሉም ግብ አልተቆጠረም(0-0)
– በተገናኙባቸው 15 ጨዋታዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ 24 ጎሎች ሲያስቆጥር ሲዳማ ቡና 6 አስቆጥሯል፡፡
– አዲስ አበባ ላይ ሁለቱ ቡድኖች 7 ጊዜ ተገናኝተው 5 ጨዋታዎች በቅዱስ ጊዮርጊስ አሸናፊነት ሲጠናቀቁ 2 ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተፈጽመዋል፡፡
– ቅዱስ ጊዮርጊስ አአ ስታድየም ላይ ሲዳማ ቡናን በተከታታይ 5 ጨዋታዎች አሸንፏል፡፡
– በሁለቱ ቡድኖች መካከል ከፍተኛው ውጤት የተመዘገበው በ2008 ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ 5-1 ማሸነፍ ችሎ ነበር፡፡
– ሲዳማ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ካስቆጠራቸው 6 ግቦች መካከል 5ቱን ያስቆጠረው በአስገሳሚ ሁኔታ አአ ላይ ነው፡፡
– ቅዱስ ጊዮርጊስ በሲዳማ መረብ ላይ ካስቆጠራቸው 24 ጎሎች 16ቱ አአ ላይ ያስቆጠራቸው ናቸው፡፡
ደረጃ
ሲዳማ ቡና በ36 ነጥቦች ሲመራ ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ35 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
ያለፉት 3 ጨዋታዎች አቋም
ቅዱስ ጊዮርጊስ | አሸነፈ | ተሸነፈ | ተሸነፈ
ሲዳማ ቡና | አሸነፈ | አቻ | አሸነፈ
ሰላም ክቡራት እና ክቡራን !
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 21ኛ ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሲዳማ ቡና የሚያደርጉት የሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታድየም ላይ በ11:30 ይካሄዳል፡፡ ሶከር ኢትዮጵያም የጨዋታውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ወደ እናንተ የምታደርስ ይሆናል፡፡
መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር!